መድልዎ በህግ የተከለከለ ነው
የWashington State Department of Health (DOH፣ የዋሽንግተን ግዛት የጤና መምሪያ) የCivil Rights Act (የሲቪል መብቶች ህግ) ርዕስ VI፣ የAmericans with Disabilities Act (ADA፣ የአካል ጉዳተኛ አሜሪካውያን ህግ) እና ሌሎች ተዛማጅነት ያላቸውን አድሎአዊ ህጎችን ጨምሮ ሁሉንም የሚመለከታቸው የፌደራል ጸረ መድሎ ህጎችን ያከብራል። DOH ዘርን፣ ቀለምን፣ ብሄራዊ አመጣጥን፣ የአካል ጉዳትን ወይም በፌደራል ህግ ስር ጥበቃ የሚደረግለትን ሌላ ባህሪ መሰረት አድርጎ አያደላም።
በተጨማሪ፣ DOH Washington Law Against Discrimination (መድልዎን የሚከለክልን የዋሽንግተን ህግ) (Revised Code of Washington (RCW፣ የተሻሻለው የዋሽንግተን ሕግ) 49.60)የሚያከብር ሲሆን ዘር፣ እምነት፣ ቀለም፣ ብሄራዊ አመጣጥ፣ ዜግነት ወይም የስደተኛ ሁኔታ፣ ጾታ፣ በክብር የተሰናበተ አርበኛ ወይም የውትድርና ሁኔታ፣የጾታ ዝንባሌ፣ የጾታ መለያ፣ የጾታ አገላለጽ፣ ማንኛውም የስሜት፣ የአዕምሮ ወይም አካላዊ እክል፣ ወይም አካል ጉዳተኛ ሰው የሚጠቀመው የሰለጠነ ውሻ መሪ ወይም አገልግሎት የሚሰጥ እንስሳ መሰረት አድርጎ አያደላም።
DOH የመድልዎ ቅሬታ ማቅረብ ወይም በምርመራ ውስጥ መሳተፍ የመሳሰሉ ጥበቃ በሚደረግለቸው ተግባራት ውስጥ በሚሳተፉ ግለሰቦች ላይ የሚደረግ የበቀል እርምጃ እና ማስፈራራትን በጥብቅ ይከለክላል። የCivil Rights & ADA Program (ሲቪል መብቶች እና የADA ፕሮግራም) የ DOH ደንበኞች በ DOH ሰራተኞች እና በአገልግሎት አቅራቢዎቹ ላይ ያቀረቡትን የበቀል እና/ወይም የማስፈራሪያ ቅሬታዎች ይገመግማል።
በ 40 Code of Federal Regulations (C.F.R.፣ የፌዴራል ደንቦች ሕግ) ክፍል 5 እና 7 መሰረት፣ DOH በሚሰራቸው ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ወይም ተግባራት ውስጥ ጾታን መሰረት አድርጎ አያደላም። DOH ማንም ሰው በእነዚህ ባህሪያት ምክንያት አልመገለሉን ወይም በተለየ መንገድ አለመስተናገዱን ያረጋግጣል።
ነጻ እርዳታዎች እና አገልግሎቶች
Washington State Department of Health አካል ጉዳተኛ ሰዎች ከእኛ ጋር በብቃት እንዲገግባቡ ነጻ እርዳታዎች እና አገልግሎቶችን ያቀርባል፣ ለምሳሌ፦
- ብቁ የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚዎች
- በሌሎች ቅርጸቶች የቀረበ የጽሁፍ መረጃ (ትልቅ ህትመት፣ ድምጽ፣ ተደራሽ ኤሌክትሮኒክ ቅርጸቶች፣ ሌሎች ቅርጸቶች)
እንዲሁም Washington State Department of Health የመጀመሪያ ቋንቋቸው እንግሊዘኛ ላልሆኑ ሰዎች ነጻ የቋንቋ አገልግሎቶችን ይሰጣል፣ ለምሳሌ፦
- ብቁ አስተርጓሚዎች
- በሌሎች ቋንቋዎች የተጻፈ መረጃ
በእነዚህ አገልግሎቶች ላይ እገዛ ከፈለጉ፣ Javier Ruizን በሚከተለው አድራሻ ያነጋግሩ፦
DOH Civil Rights & ADA Program
PO Box 47890, Olympia, WA 98504-47890
(833) 428-3703
ለ Civil Rights Program ኢሜይል ይላኩ፦ Civil.Rights@doh.wa.gov
የጸረ መድልዎ አስተባባሪ
DOH የመድልዎ ቅሬታዎች መፍታትን ጨምሮ የ DOH የሲቪል መብቶች ግዴታዎች መከበራቸውን ለማረጋገጥ የ Civil Rights & ADA Program ስራ አስኪያጅ የሆኑትን Javier Ruiz የጸረ መድልዎ አስተባባሪ አድርጎ ሾሟል። ማንኛውም የ DOH ደንበኛ ከ DOH አገልግሎቶች ፍትሃዊ ተደራሽነት እና ከ DOH የሲቨል መብቶች ግዴታዎችን ጋር የሚዛመዱ ጥያቄዎች ካለው Javier Ruizን ማነጋገር ይቻላል።
የመድልዎ ቅሬታዎች
DOH እነዚህን አገልግሎቶች እንዳላቀረበ ወይም ዘር፣ ቀለም፣ ብሄራዊ አመጣጥ፣ እድሜ፣ አካል ጉዳት፣ ጾታ ወይም ማንኛውም ሌላ ጥበቃ የሚደረግለት ክፍልን መሰረት አድርጎ መድልዎ እንዳደረገ ካመኑ፣ ክስተቱ በተፈጠረ በ180 ቀናት ውስጥ ለ Civil Rights & ADA Program ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ።
ቅሬታዎች የቅሬታ ቅጽ በመጠቀም በጽሁፍ፣ በኢሜይል፣ በፖስታ፣ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ሊቀርቡ ይችላሉ።
- የመድልዎ ቅሬታ ቅጽ– ዲጂታል ስሪት
- የመድልዎ ቅሬታ ቅጽ– የእትም ወይም የኢሜይል ስሪት (PDF)
- ኢሜይል፦ Civil.Rights@doh.wa.gov
- ፖስታ፦ DOH Civil Rights & ADA Program, PO Box 47890, Olympia, WA 98504-47890
- ስልክ ቁጥር፡- (833) 428-3703
ስለ መድሎ ቅሬታ የአሰራር ሂደት የበለጠ ይወቁ።
ተጨማሪ የቅሬታ አማራጮች
U.S. Department of Health and Human Services (HHS)
የሲቪል መብቶች ቅሬታን ለHHS Office for Civil Rights (ለHHS የዜጎች መብቶች ቢሮ)፣ በ Office for Civil Rights የቅሬታ ፓርታል (በእንግሊዝኛ) ወይም በፖስታ ወይም በስልክ በሚከተለው ማቅረብ ይችላሉ፦
U.S. Department of Health and Human Services (HHS)
200 Independence Avenue SW, Room 509F, HHH Building, Washington, D.C. 20201
1-800-368-1019, 800-537-7697 (TDD)
ለ HHS እንዴት ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችሉ የበለጠ ይወቁ (በእንግሊዝኛ)።
U.S. Environmental Protection Agency (EPA)
አንድ ቅሬታ ከ Environmental Protection Agency (EPA፣ የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ) ገንዘብ ተቀባይ ጋር የተያያዘ ከሆነ፣ ለ EPA በሚከተለው ላይ ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ፦
U.S. Environmental Protection Agency
Office of External Civil Rights Compliance
1200 Pennsylvania Avenue, N.W., Washington, DC 20460
ኢሜይል፦ Title_VI_Complaints@epa.gov
ለ EPA እንዴት ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችሉ የበለጠ ይወቁ።
Washington State Human Rights Commission (WSHRC)
Washington State Human Rights Commission (WSHRC፣ (የዋሽንግተን ግዛት የሰብዓዊ መብት ኰሚሽን) የ Washington Law Against Discrimination፣ ምዕራፍ 49.60 RCW ያስፈጽማል። በ WSHRC የመስመር ላይ ፖርታል (በእንግሊዘኛ እና በስፓኒሽ) ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ ወይም በ፦
Washington State Human Rights Commission
PO Box 42490, Olympia, WA 98504-2490
ኢሜይል፦ frontdesk@hum.wa.gov
ለ WSHRC እንዴት ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችሉ (በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽ) የበለጠ ይወቁ።