ራስን የማግለል እና የኳራንቲን ማስያ

This page is being reviewed for updates. The Washington State Department of Health has updated its guidance for what to do if you are sick with COVID-19 or were exposed to COVID-19. This page may have content that is inconsistent with the new guidance.

ለ COVID-19 ማግለያ እና ኳራንቲን የዋሺንግተን ግዛት ጤና መምሪያ (እንግሊዝኛ ብቻ)

የእርስዎን ራስን ማግለያ ወይም የኳራንቲን ጊዜ እንዴት እንደሚያሰሉ እባክዎን ከታች ይመልከቱ። ራስን በማግለል ወቅት ምን እንደሚደረግ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት COVID-19 ምርመራዎ አዎንታዊ ከሆነ ምን መደረግ አለበት (PDF) ን ይመልከቱ። COVID-19 ከያዘው ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ከነበርዎት ምን ማድረግ እንዳለብዎት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎን COVID-19 ላለበት ሰው ከተጋለጡ ምን ማድረግ እንዳለብዎት (PDF) ን ይመልከቱ።

በሽታ የመከላከል አቅምዎ ከተጎዳ ወይም በ COVID-19 በጠና ከታመሙ፣ እነዚህ ማስያዎች (ካልኩሌተሮች) በእርስዎ ሁኔታ ላይ አይተገበሩም። ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት COVID-19 ምርመራዎ አዎንታዊ ከሆነ ምን መደረግ አለበት(PDF) ን ይመልከቱ።

ከፍተኛ ተጋላጭነት ባለበት ሁኔታ ውስጥ የሚቆዩ ወይም የሚሰሩ ከሆነ እነዚህ ካልኩሌተሮች በእርስዎ ሁኔታ ላይ ላይተገበሩ ይችላሉ። ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው ቦታዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡- የጤና እንክብካቤ መስጫ ተቋማት፣ ማረሚያ ተቋማት፣ ማቆያ ተቋማት፣ ቤት አልባ ለሆኑ መጠለያዎች፣ የሽግግር መኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ የባህር ዳርቻዎች (ለምሳሌ የንግድ የባህር ምግብ መርከብ፣ የጭነት መርከብ፣ የጉብኝት መርከብ)፣ ጊዜያዊ ሰራተኛ መኖሪያ ቤት፣ ወይም የተጨናነቀ የስራ ቦታዎች አካላዊ ርቀት መጠበቅ የማያስችሉ የስራ ባህሪ ያላቸው (ለምሳሌ መጋዘኖች፣ ፋብሪካዎች፣ እና የምግብ ማሸጊያ እና የስጋ ማዘጋጃ ተቋማት)። ራስዎን ስለማግለል መረጃ ለማግኘት እባክዎን የ COVID-19 ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ካልዎት ምን ያደርጋሉ(PDF) እና ኳራንቲን ስለማድረግ መረጃ ለማግኘት እባክዎን በ COVID-19 ለተያዘ ሰው ተጋላጭ ከነበሩ ምን ያደርጋሉ(PDF) የሚሉትን ሰነዶች ይመልከቱ።

አዎንታዊ ውጤት እና ምልክቶች አሉኝ ወይም ነበሩኝ፦ ራስን የመለየት ጊዜዬን አስላ

5 ቀን ራስን ማግለል

የ 5 ቀን ራስን ማግለል በሚከተሉት ተገቢ ነው፦

  • የእርስዎ ምልክቶች ከተሻሻሉ፣ እና
  • ትኩሳት ከነበርዎት እና ትኩሳትን የሚቀንስ መድሃኒት ከተጠቀሙ 24 ሰዓታት ካለፉ፣ እና
  • ከሌሎች አጠገብ በደምብ የሚሆን ጭምብል ማድረግ ከቻሉ

እነዚህ መስፈርቶች ከተተገበሩ፣ የመጨረሻ የመለየት ቀንዎ፦ ነው
መለየትዎ የሚያበቃው በ፡- ነው

ከሌሎች ሰዎች ጋር ለተጨማሪ 5 ቀናት (እስከ ) ድረስ ጭንብል መልበስዎን ያረጋግጡ እና ጭምብል ማድረግ ከማይችሉባቸው እንቅስቃሴዎች ይቆጠቡ። እንዲሁም እስከ ድረስ ከፍተኛ ተጋላጭ ከሆኑ ሰዎች ጋር ከመሆን መቆጠብ አለብዎት። ጉዞን በተመለከተ መረጃ ለማግኘት ጉዞ | CDC (እንግሊዘኛ ብቻ) ይመልከቱ።

የአንቲጂን ምርመራ ማግኘት ከቻሉ በተገለሉበት በ5ኛው ቀን ምርመራ በማድረግ ሌሎችን የመበከል አደጋን መቀነስ ይችላሉ። ምርመራዎ አሉታዊ ከሆነ፣ ከ5ኛው ቀን በኋላ ራስዎን ማግለል ማቆም ይችላሉ፣ ነገር ግን ከሌሎች ሰዎች ጋር ሲሆኑ ለተጨማሪ 5 ቀናት (እስከ ) ድረስ ጭምብል ማድረግዎን ይቀጥሉ። የምርመራዎ ውጤት አዎንታዊ ከሆነ እስከ ድረስ ራስዎን ማግለል መቀጠል አለብዎት።

10 ቀን ራስን ማግለል

ከላይ ያሉት መመዘኛዎች ለእርስዎ የማይተገበሩ ከሆነ ለ 10 ቀናት ራስዎን ማግለል አለብዎት።

ለ 10 ቀናት ተለይተው ከቆዩ፣ የመገለል የመጨረሻዎ ሙሉ ቀን፡- ነው
ራስዎን ማግለል የሚያበቃው በ፡- ነው

የህመም ምልክቶችዎ ካልተሻሻሉ ወይም ትኩሳት መኖሩ ከቀጠለ (ወይንም ትኩሳትን የሚቀንሱ መድኃኒቶችን የሚፈልጉ ከሆነ)፣ ምልክቶችዎ እስኪሻሻሉ ድረስ እና ትኩሳትን የሚቀንሱ መድኃኒቶችን ሳይጠቀሙ ለ 24 ሰዓታት ያህል ትኩሳት እስኪቆም ድረስ ራስዎን ማግለል ለማቆም ይጠብቁ።

አዎንታዊ ውጤት አለኝ ግን ምልክቶች አልነበሩኝም፦ ራስን የማግለል ጊዜዬን አስላ

5 ቀን ራስን ማግለል

የ 5 ቀን ራስን ማግለል በሚከተሉት ተገቢ ነው፦

  • ከሌሎች አጠገብ በደምብ የሚሆን ጭምብል ማድረግ ከቻሉ

የበሽታ ምልክቶች ታይተው የማያውቁ ከሆነ እና በደንብ የሚሆን ጭንብል ከሌሎች ሰዎች አጠገብ ማድረግስ ከቻሉ፣ የእርስዎ የመጨረሻ ሙሉ ራስን የማግለል ቀን፦ ነው።
መለየትዎ የሚያበቃው በ፡- ነው

ከሌሎች ሰዎች ጋር ለተጨማሪ 5 ቀናት (እስከ ) ድረስ ጭንብል መልበስዎን ያረጋግጡ እና ጭምብል ማድረግ ከማይችሉባቸው እንቅስቃሴዎች ይቆጠቡ። እንዲሁም እስከ ድረስ ከፍተኛ ተጋላጭ ከሆኑ ሰዎች ጋር ከመሆን መቆጠብ አለብዎት። ጉዞን በተመለከተ መረጃ ለማግኘት ጉዞ | CDC (እንግሊዘኛ ብቻ) ይመልከቱ።

የአንቲጂን ምርመራ ማግኘት ከቻሉ በተገለሉበት በ5ኛው ቀን ምርመራ በማድረግ ሌሎችን የመበከል አደጋን መቀነስ ይችላሉ። ምርመራዎ አሉታዊ ከሆነ፣ ከ5ኛው ቀን በኋላ ራስዎን ማግለል ማቆም ይችላሉ፣ ነገር ግን ከሌሎች ሰዎች ጋር ሲሆኑ ለተጨማሪ 5 ቀናት (እስከ ) ድረስ ጭምብል ማድረግዎን ይቀጥሉ። የምርመራዎ ውጤት አዎንታዊ ከሆነ እስከ ድረስ ራስዎን ማግለል መቀጠል አለብዎት።

10 ቀን ራስን ማግለል

ከላይ ያሉት መመዘኛዎች ለእርስዎ የማይተገበሩ ከሆነ ለ 10 ቀናት ራስዎን ማግለል አለብዎት።

ለ 10 ቀናት ተለይተው ከቆዩ፣ የመገለል የመጨረሻዎ ሙሉ ቀን፡- ነው
ራስዎን ማግለል የሚያበቃው በ፡- ነው

ለ COVID-19 (እንደ የቅርብ ግንኙነት ተለይቼ) ተጋላጭ ነበርኩ፡ የኳራንቲን ጊዜዬን አስላ

ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ከተደረገለት ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ነበርዎት፣ ግን ምንም ምልክቶች የሉዎትም።.

በ COVID-19 ክትባቶች ላይ ወቅታዊ መሆንዎን ለማወቅ የ Centers for Disease Control and Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከላት) ን መመሪያ (እንግሊዝኛ ብቻ) ይመልከቱ። በ COVID-19 ክትባቶች ላይ ወቅታዊ ካልሆኑ፣ ቤት መቆየት እና ኳራንቲን ማድረግ አለብዎት።

የ 5 ቀን ኳራንቲን

የ 5 ቀን ኳራንቲን በሚከተሉት ተገቢ ነው፦

  • በ COVID-19 ክትባቶች ላይ ወቅታዊ አይደሉም፣ እና
  • ከሌሎች አጠገብ በደምብ የሚሆን ጭምብል ማድረግ ከቻሉ

ቤት ውስጥ መቆየት እና ቢያንስ ለ 5 ሙሉ ቀናት ኳራንትን መግባት አለብዎት (ምንም እንኳን በዚህ ጊዜ አሉታዊ ምርመራ ቢያደርጉም)። የመጨረሻ የኳራንቲን ሙሉ ቀንዎ፦ ነው
ኳራንቲንዎ የሚያበቃው በ፦ ነው

ከሌሎች ሰዎች ጋር በሚሆኑበት ጊዜ በደምብ የሚሆንዎትን ጭምብል (እንግሊዝኛ ብቻ) ያድርጉ፣ ጭንብል ማድረግ የማይችሉባቸውን እንቅስቃሴዎች ያስወግዱ እና ለተጨማሪ 5 ቀናት (እስከ ) ድረስ ለከባድ በሽታ ተጋላጭ ከሆኑ ሰዎች ጋር ከመቅረብ ይቆጠቡ። በጉዞ ላይ መረጃ ለማግኘት ጉዞ | CDC (እንግሊዝኛ ብቻ) ን ይመልከቱ።

አዎን፣ ምልክቶች ባያዳብሩም ጭምር መመርመር አለብዎት። COVID-19 ከያዘው ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካደረጉበት ቢያንስ ከ 5 ቀናት በኋላ ይመርመሩ። (በ ወይም ከዚያ በኋላ)። ምርመራዎ አዎንታዊ ከሆነ፣ ቤት ውስጥ መቆየት እና ራስዎን ከሌሎች ማግለል አለብዎት (ራስን በማግለል ላይ ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ከተገኘ ምን ማድረግ እንዳለብዎ (PDF)) ይመልከቱ።

የ 10 ቀን ኳራንቲን

የ 10 ቀን ኳራንቲን የሚከተሉት ከሆነ ተገቢ ነው፦

  • በ COVID-19 ክትባቶች ላይ ወቅታዊ አይደሉም፣ እና
  • ከሌሎች አጠገብ በደምብ የሚሆን ጭምብል ማድረግ ካልቻሉ

ቤት ውስጥ መቆየት እና ቢያንስ ለ 10 ሙሉ ቀናት ኳራንትን መግባት አለብዎት (ምንም እንኳን በዚህ ጊዜ አሉታዊ ምርመራ ቢያደርጉም)። የመጨረሻ የኳራንቲን ሙሉ ቀንዎ፦ ነው
ኳራንቲንዎ የሚያበቃው በ፦ ነው

በዚህ ቀን፣ የተለመዱ እንቅስቃሴዎችዎን መቀጠል ይችላሉ ነገር ግን አሁንም የመጋለጥዎን አደጋ ለመቀነስ እርምጃዎችን መውሰድ አለብዎት (ለምሳሌ፣ የ COVID-19 ክትባቶችን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ ያግኙ (እንግሊዘኛ ብቻ)፣ ከምክሮቹ እና/ወይም መስፈርቶቹ ጋር በተዛመደ መልኩ የፊት ጭምብል ያድርጉ፣ በቂ የአየር ዝውውር በሌለባቸው ቦታዎች ላይ አይገኙ፣ እና አዘውትረው እጅዎን ይታጠቡ፤ ለተጨማሪ መረጃ እራስዎን እና ሌሎችን እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል | CDC (እንግሊዘኛ ብቻ) ይመልከቱ)።

ኳራንቲን አይኖርም/የለም

በ COVID-19 ክትባቶች ላይ ወቅታዊ ከሆኑ፣ ምልክቶች ካላዳበሩ በስተቀር ቤት መቆየት አያስፈልግዎትም። ምልክቶች ባያዳብሩም በሌሎች ሰዎች አቅራቢያ በደምብ የሚሆንዎትን ማስክ እስከ ድረስ ማድረግ እና መመርመር አለብዎት። COVID-19 ከያዘው ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካደረጉበት ቢያንስ ከ 5 ቀናት በኋላ ይመርመሩ። (በ ወይም ከዚያ በኋላ)።

ባለፉት 90 ቀናት ውስጥ COVID-19 ይዞት ከነበረ (በ የቫይረስ ምርመራ (እንግሊዝኛ ብቻ) በመጠቀም አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ)፣ ምልክቶች እስካላዳበሩ ድረስ ቤት ውስጥ መቆየት አያስፈልግዎትም። እስከ ድረስ በደንብ የሚሆን ጭንብል እና COVID-19 ከያዘው ሰው ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ከተገናኙ ቢያንስ ከ5 ቀናት በኋላ አንቲጂን ምርመራ (የ PCR ምርመራ አይደለም) (በ ላይ ወይም በኋላ) ማድረግ አለብዎት።

ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ከተደረገለት ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ከነበርዎት እና እርስዎ ምልክቶች ካሉዎት፣ እባክዎን COVID-19 ከተያዘ ሰው ጋር ተጋልጠው ከሆነ ምን ማድረግ እንዳለብዎት (PDF) ይመልከቱ።