ወጣትን መከተብ

ይዘቱ ለመጨረሻ ጊዜ የዘመነው በታህሳስ 9፣ 2022 ነበር።

Decorative

የክትባት ደህንነት እና ውጤታማነት

ልጅዎን ከ COVID-19 ማስከተብ የሚከተሉትን ያደርጋል፡-

  • በ COVID-19 የመያዝ የስጋትቸውን ለመቀነስ ይረዳል
  • በ COVID-19 ከተጠቁ እንኳን፣ በጠና የመታመም እድላቸውን ይቀንሳል
  • ከ COVID-19 የተነሳ የመሞት ስጋታቸውን ለመቀነስ እና ሆስፒታል የመተኛት እድላቸውን ይቀንሳል
  • በ COVID-19 ተለዋጭ እንዳይጠቁ በመከላከል ይረዳቸዋል
  • በ COVID-19 ከመያዝ የተጠበቁ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ቁጥር ይጨምራል — በሽታውን ለመሰራጨት ከባድ ያደርገዋል
  • COVID-19 በማህበረሰብ ውስጥ የሚኖረውን ስርጭትን ለመግታት በአካል በመማር እና በእንቅስቃሴ ላይ ያሉ መስተጓጎሎችን ይቀንሳል
Decorative

የክትባት ፍቃድ

የ Pfizer ክትባት እድሜያቸው ከ ከ 6 ወር- -11 ለሆኑ ልጆች በ Emergency Use Authorization (EUA፣ አደጋ ጊዜ አጠቃቀም ፍቃድ) መሰረት ማግኘት ይችላሉ፤ እንዲሁም እድሜያቸው ከ12 በላይ ለሆኑ ሙሉ በሙሉ ጸድቋል። በ Emergency Use Authorization (EUA፣ የድንገተኛ አጠቃቀም ፍቃድ) ስር የ Moderna ክትባት ከ 6 ወር– 17 አመት ላሉ ልጆች ይገኛል። በ Emergency Use Authorization (EUA፣ የድንገተኛ አጠቃቀም ፍቃድ) ስር ዕድሜያቸው ከ 12 ዓመት በላይ ለሆኑ የ Novavax ክትባት አለ።

EUA የ Food and Drug Administration (FDA፣ የምግብ እና መድሃኒት አስተዳደር) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ለአንድ ምርት ሙሉ ፍቃድ ከመሰጠቱ በፊት የሚገኝ እንዲሆን ያስችለዋል። የአደጋ ጊዜ አጠቃቀም ፍቃድ አላማ ሰዎች ከረጅም ጊዜ የውሂብ ትንተና በፊት የህይወት አድን ክትባቶችን ማግኘት እንደሚችሉ ማረጋገጥ ነው። ሆኖም EUA ክሊኒካዊ መረጃን በጥልቀት መመርመርን ይጠይቃል—ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ።

 

በ FDA የተሰጠ ማንኛውም EUA በ Centers for Disease Control and Prevention (CDC, በበሽታ ቁጥጥር እና መከላከያ ማዕከላት) የ Advisory Committee on Immunization Practices (የክትባት ተግባራት አማካሪ ኮሚቴ) (እንግሊዝኛ ብቻ) እና በ Western States Scientific Safety Review Workgroup (ምዕራባዊ ግዛቶች ሳይንሳዊ ደህንነት ግምገማ የስራ ቡድን) ተጨማሪ ማጣሪያ ይደረግለታል።

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች ለወላጆች እና አሳዳጊዎች

ልጄ COVID-19 እንዳይይዘው ለምን እሰጋለሁ?

ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ በአሜሪካ ውስጥ ከ 15 ሚሊዮን በላይ ህጻናት በ COVID-19 ተይዘዋል። አዳዲሶቹ የ COVID-19 ዝርያዎች ከመጀመሪያው እና ብዙ ሰዎችን ለሆስፒታል ከዳረገው የ COVID-19 ቫይረስ የበለጠ ለወጣቶች በጣም አደገኛ እና በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጩ ናቸው።

COVID-19 ብዙውን ጊዜ በልጆች ላይ ከአዋቂዎች የበለጠ ቀላል ቢሆንም፣ ህጻናት በጣም ሊታመሙ እና የበሽታ መከላከል አቅማቸው ደካማ ለሆነ ወይም ተጋላጭ ለሆኑ ጓደኞቻቸው እና ቤተሰባቸው በሌሎች መንገዶች ሊያስተላልፉት ይችላሉ።

በ COVID-19 የተጠቁ ህፃናት “ረዥም COVID-19” ወይም የማያቋርጥ ምልክቶች ሊያዳብሩ ይችላሉ ይህም ብዙውን ጊዜ የአእምሮ ብዥታ፣ ድካም፣ ራስ ምታት፣ ማዞር እና የትንፋሽ ማጠርን ያጠቃልላሉ። ክትባት የልጆችን ጤንነት እና ደህንነት ለመጠበቅ ምርጡ መንገድ ነው።

በ COVID-19 የተጠቁ ህፃናት ለ Multisystem Inflammatory Syndrome (MIS-C) (ድረ ገጹ በእንግሊዘኛ ብቻ) የበለጠ ስጋት ላይ ሊሆኑ ይችላሉ። MIS-C ልብን፣ ሳንባን፣ ኩላሊትን፣ አእምሮን፣ ቆዳን፣ አይንን ወይም የጨጓራና አንጀት አካላትን ጨምሮ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በማቃጠል ህመም ሊሰማ የሚችልበት ሁኔታ ነው። የ MIS-C መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን ባይታወቅም፣ MIS-C ያለባቸው ብዙ ህፃናት COVID-19 ነበረባቸው፣ ወይም በ COVID-19 ከተጠቃ ሰው ጋር ግንኙነት ነበራቸው። MIS-C ከባድ፣ እንዲሁም ለሞት የሚዳርግ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በዚህ በሽታ የተያዙ አብዛኛዎቹ ህጻናት በህክምና አገልግሎት የተሻሉ ሆነዋል።

ክትባቱ ለ K-12 ትምህርት ቤት መግቢያ አስፈላጊ ነው?

Department of Health (የጤና መምሪያ) ሳይሆን የ Washington State Board of Health (የዋሽንግተን ግዛት የጤና ቦርድ) ከ K-12 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ላሉ ልጆች የክትባት መስፈርቶችን የማውጣት ስልጣን አለው Revised Code of Washington (RCW፣ የተሻሻለው የዋሽግተን ኮድ) 28A.210.140 ። በአሁኑ ሰዓት ለትምህርት ቤት ወይም ለህጻናት እንክብካቤ የ COVID-19 የክትባት መስፈርት አልተቀመጠም።

ለክትባቱ መክፈል ይጠበቅብኛል?

አይ። ልጅዎ ለእርስዎ ምንም ወጪ ሳይሆን ክትባቱን ያገኛል። የፌዴራሉ መንግሥት የክትባቱን ሙሉ ወጪ ይከፍላል።

የሕዝብ ወይም የግል የጤና ኢንሹራንስ ካልዎት፣ የክትባት አቅራቢዎ ለክትባት አስተዳደር ክፍያ ክፍያውን ሊከፍላቸው ይችላል። ዋስትና ከሌልዎት፣ የፌደራል መንግስቱ አቅራቢዎ ክትባትዎን እንዲያስተዳድር የሚከፍል ፕሮግራም አቅርቧል።

ከኪስዎ ወጪ ወይም ለ COVID-19 ክትባትዎ የአስተዳደር ክፍያ ከአቅራቢዎ ክፍያ መቀበል የለባችሁም። ይህ የግል መድህን፣ Apple Health (Medicaid)፣ Medicare ያላቸው ሰዎች ወይም የጤና መድን ሽፋን የሌላቸውም ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል።

የ COVID-19 ክትባት የተለመዱ የጎንዮሽ ጉዳቶች በህፃናት ላይ ምንድን ናቸው?

ህጻናት በ COVID-19 ከተያዙ የሚኖሩት የጤና ስጋቶች ከክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳቶች ጋር ሲነፃጸር የበለጠ ከፍ ያለ ነው።

ልክ እንደ ሌሎች ክትባቶች፣ በጣም የተለመዱት የጎንዮሽ ጉዳቶች የእጅ ህመም፣ ድካም፣ ራስ ምታት እና የጡንቻ ህመም ናቸው። እነዚህ ምልክቶች ብዙውን ጊዜ ቀላል ናቸው።

በክሊኒካዊ ሙከራዎች ላይ (እንግሊዝኛ ብቻ) ብዙ ህፃናት ከመጀመሪያው መጠን ይልቅ ከሁለተኛው መጠን በኋላ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሪፖርት አድርገዋል። የጎንዮሽ ጉዳቶች በአጠቃላይ በክብደት ደረጃ ቀላል እና መካከለኛ ሲሆኑ ከክትባት በኋላ ባሉት ሁለት ቀናት ውስጥ ተከስተዋል፣ እንዲሁም አብዛኛዎቹ ከአንድ እስከ ሁለት ባሉት ቀናት ውስጥ ጠፍተዋል።

በ mRNA ክትባት ውስጥ ምን ዓይነት ንጥረ ነገሮች አሉ?

በ mRNAr ክትባት ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮች ለክትባት የተለመዱ ናቸው። ክትባቱ የ mRNA ንጥረ ነገሮችን እንደ ስብ፣ ጨው እና ስኳር ካሉ ሌሎች ንጥረ ነገሮች ጋር በመሆን ንቁውን ንጥረ ነገር የሚከላከሉ፣ በሰውነት ውስጥ በተሻለ ሁኔታ እንዲሰሩ እና በማከማቻ እና በማጓጓዝ ወቅት ክትባቱን የሚከላከሉ ናቸው።

የ mRNA ክትባት የሰው ስነ ህዋሳትን (የፅንስ ስነ ህዋሳትን ጨምሮ)፣ የ COVID-19 ቫይረስን፣ ላቲክስን፣ መጠበቅያዎችን፣ ወይም የአሳማ ምርቶችን ወይም ጄልቲንን ጨምሮ ማንኛውንም የእንስሳት ተረፈ ምርቶችን አያካትትም። ክትባቶቹ በእንቁላል ውስጥ አያድጉም እና ምንም አይነት የእንቁላል ውጤቶችን አይዙም

ስለ ንጥረ ነገሮቹ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህንን ጥያቄ እና መልስ፤ ከ Children's Hospital of Philadelphia (የፊላዴልፊያ ህፃናት ሆስፒታል) ድረ ገፅ (በእንግሊዝኛ ብቻ) ይመልከቱ።

ልጄ የትኛውን የክትባት ምርት ሊወስድ ይችላል?

በዚህ ጊዜ፣ የ Pfizer-BioNTech (Pfizer) ክትባት እና የ Moderna የ COVID-19 ክትባት ስሪቶች እድሜያቸው 6 ወር እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ህጻናት ተፈቅዷል። በ Emergency Use Authorization (EUA፣ የድንገተኛ አጠቃቀም ፍቃድ) ስር ዕድሜያቸው ከ 12 ዓመት በላይ ለሆኑ የ Novavax ክትባት አለ።

ልጄ የማጠናከሪያ መጠን (ዶዝ) ያስፈልገዋል?

አዎ፣ የዘመነ ባይቫለንት የ mRNA ማጠናከሪያ እድሚያቸው 6 ወር እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ክትባታቸውን ለማዘመን የመጨረሻውን ዶዝ ከወሰዱ ከ 2 ወራት በኋላ ይመከራል።

ከ 6 ወር-4 አመት ለሆናቸው ህጻናት የ Pfizer COVID-19 ክትባት አሁን ሁለት ሞኖቫለንት የ Pfizer ዶዞችን እና አንድ ባለ ሁለት የ Pfizer ዶዝን ያካትታል።

ባለ 3 ዶዝ የ Pfizer የመጀመሪያ ክትትል ገና ያልጀመሩ ወይም የመጀመሪያ ክትትላቸውን ሶስተኛ ዶዝ ያልተቀበሉ ከ 6 ወር-4 አመት ለሆናቸው ህጻናት አሁን የዘመነውን የ Pfizer ክትትል ያገኛሉ

ባለ 3 ዶዝ Pfizer የመጀመሪያ ክትትልን ያጠናቀቁ ከ 6 ወር-4 አመት የሆናቸው ህጻናት በዚህ ጊዜ ለተጨማሪ ክትባቶች ወይም አጋዦች ብቁ አይሆኑም

ልጄ ምን ያህል መጠኖች (ዶዝ) ያስፈልጉታል?

ሁሉም ልጆች ቢያንስ 2 መጠኖችን እንዲወስዱ ይመከራል።

  • እድሜያቸው ከ 6 ወር- 4 አመት የሆኑ ህጻናት ባለ 3 ዶዝ የ Pfizer የመጀመሪያ ደረጃ ዙር ወይም ባለ 2 ዶዝ የ Moderna የመጀመሪያ ደረጃ ዙር ያገኛሉ
  • እድሜያቸው ከ 5-11 የሆኑ ልጆች ባለ 2 ዶዝ የመጀመሪያ ደረጃ ዙር ያገኛሉ
  • እድሜያቸው ከ 12-17 የሆኑ ልጆች ባለ 2 ዶዝ የመጀመሪያ ደረጃ ዙር ያገኛሉ

ባለ 2-ዶዝ ዙር የተቀበሉ እና መካከለኛ ወይም ሀይለኛ የበሽታ መከላከል ችግር ያለባቸው ህፃናት ከ 2ኛው ክትባት ከ 28 ቀናት በኋላ ተጨማሪ የመጀመሪያ ደረጃ ዶዝ መውሰድ አለባቸው እንዲሁም ሁሉም 6 ወራት+ ህጻናት የማጠናከሪያ ዶዝ ሊወስዱ ይገባል። ለወደፊቱ, ለሌሎች የሰዎች ቡድኖች ተጨማሪ መጠን ሊመከር ይችላል.

በሽታ የመከላከል ችግር ላለባቸዉ ሰዎች እባክዎ የ Centers for Disease Control & Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል) መመርያዎችን ይመልከቱ ወይም የ DOH ን ድህረ ገፅ ይጎብኙ።

ስለ ክትባቱ ጥያቄዎች ካሉኝ ማንን ማነጋገር አለብኝ?

ከልጅዎ የህጻናት ስፔሻሊስት ወይም ሌላ ታማኝ የሕክምና አገልግሎት አቅራቢ ጋር ይነጋገሩ፣ ከማህበረሰብ ጤና ሰራተኛ ጋር ይነጋገሩ ወይም መረጃ www.CovidVaccineWA.org ላይ ያንብቡ።

ልጄን ለማስከተብ የት ልወስደው እችላለሁ?

የዋሽንግተን ግዛት ሁሉንም የሚመከሩ ክትባቶችን ያለ ምንም ወጪ ከ 18 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት ይሰጣል። የልጅዎን የሕፃናት ሐኪም ወይም መደበኛ ክሊኒክ የ COVID-19 ክትባት እንዳላቸው ይጠይቁ።

የጤና እንክብካቤ አቅራቢ የሌላቸው ቤተሰቦች፣ የጤና እንክብካቤ አቅራቢ፣ ክሊኒክ ወይም ሌሎች የጤና መርጃዎች ለማግኘት ወደ Help Me Grow WA ነጻ መስመር በስልክ ቁጥር 1-800-322-2588 መደወል ወይም ParentHelp123.org የሚለውን ድረ ገጽ (በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽ ቋንቋዎች ብቻ) መጎብኘት ይችላሉ። ይህ አገልግሎት ነፃ ነው እንዲሁም የቋንቋ እርዳታ አለ።

ከዚህም በተጨማሪ፣ VaccineLocator.doh.wa.gov የሚለውን ድረ ገጽ መጎብኘት እና ማጣሪያውን/ፊልተር ተጠቅመው ለእርስዎ ቅርብ የሆኑ እና የህጻናት ክትባቱ ያላቸውን ቦታዎች ዝርዝር ማየት ይችላሉ።

ልጄ እንደ ጉንፋን ያሉ ሌሎች ክትባቶችን በሚወስድበት ጊዜ የ COVID-19 ክትባትን መውሰድ ይችላል?

አዎ። ልጅዎ ሌሎች ክትባቶችን በሚወስዱበት ተመሳሳይ ጊዜ የ COVID-19 ክትባትን መውሰድ ይችላል።

ለልጅዎ አስፈላጊ የትምህርት ቤት ክትባቶችን (እንግሊዝኛ ብቻ) ወይም ለሌሎች የሚመከሩ ክትባቶች ከ COVID-19 ክትባት የተለየ መርሃ-ግብር ማውጣት አያስፈልግዎትም። የ COVID-19 ክትባት ቀጠሮ ልጅዎ በሌሎች የሚያሰፈልጉት ክትባቶች ሁሉ እንዲከተብ ማድረግያ ሌላው አጋጣሚ ነው።

ልጄ በህጻን እንክብካቤ ወይም የቀን ማቆያዎች ውስጥ እንዲገባ የ COVID-19 ክትባት ያስፈልገዋል?

Washington State Board of Health (በእንግሊዝኛ ብቻ) ለትምህርት ቤቶች እና ለህፃናት እንክብካቤ የትኞቹ ክትባቶች እንደሚያስፈልጉ ይወስናል። በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት የ COVID-19 ክትባት መስፈርትን የሚጠይቅ ትምህርት ቤት ወይም የህጻናት እንክብካቤ የለም።

ለቀን ማቆያዎች፣ መስፈርቶቻቸው ምን እንደሆኑ ለማወቅ ማቆያውን የሚመራው ድርጅት ጋር ያረጋግጡ።

ክትባቶቹ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ለልጆች ውጤታማ መሆናቸውን እንዴት እናውቃለን?

የ COVID-19 ክትባቶች ደሕንነታቸዉ የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ Centers for Disease Control & Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል) የሀገሪቱን የክትባት ደሕንነት የመቆጣጠር አቅምን አስፋፍቷል፣ አጠናክሯል። በዚህ ምክንያት፣ የክትባት ደሕንነት ባለሙያዎች የ COVID-19 ክሊኒካል ሙከራ ግዜ ላይ ላይታዩ የሚችሉ ጉዳዮችን ሊቆጣጠር እና ሊያዉቁ ይችላሉ፦

Pfizer

እድሜያቸው ከ 6 ወር-4 አመት የሆኑ ህጻናት

ከ 6 ወር እስከ 4 አመት የሆኑ 4,500 የሚጠጉ ህጻናት በ Pfizer የ COVID-19 ክትባት ክሊኒካዊ ሙከራዎች ተሳትፈዋል። የዚህ ዕድሜ ተሳታፊዎች ለ 3-ዶዝ ዙር የበሽታ መከላከል ስርአት የሰጠው ምላሽ በዕድሜ የገፉ ተሳታፊዎች የበሽታ መከላከል ስርአት ምላሽ ጋር ተመሳሳይ ነው። በጥናቱ ውስጥ ምንም ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶች አልተታዩም፣ ይህም መካሄዱን ቀጥሏል

እድሜያቸው ከ 5-11 የሆኑ ህፃናት

  • በግምት 3,100 የሚሆኑ እድሜያቸው ከ 5 እስከ 11 የሆኑ ህፃናት (እንግሊዝኛ ብቻ) የ Pfizer የ COVID-19 ክትባትን በክሊኒካዊ ሙከራዎች ላይ ወስደዋል። በጥናቱ ውስጥ ምንም ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶች አልተታዩም፣ ይህም መካሄዱን ቀጥሏል።
  • ከ 5 እስከ 11 አመት እድሜ ያላቸው ህፃናት የበሽታ መከላከል ምላሾች እድሜያቸው ከ 16 እስከ 25 አመት የሆኑ ግለሰቦች ጋር የሚወዳደር ነው።
  • ክትባቱ ከ 5 እስከ 11 ባሉ ህጻናት ላይ COVID-19 ን በመከላከል ወደ 91% የሚጠጋ ውጤታማነት አለው።

እድሜያቸው ከ12-15 የሆኑ ህፃናት

  • በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እድሜያቸው ከ 12 እስከ 15 ዓመት ለሚሆኑ 2,260 ተሳታፊዎች ቀጣይነት ባለው በዘፈቀደ በተመረጠ፣ በፕላሴቦ-ቁጥጥር በሚደረግለት (መድኃኒትነት የሌለው መድኃኒት) ክሊኒካዊ ሙከራ ውስጥ ተሳትፈዋል።
  • ከእነዚህም ውስጥ፣ 1,131 ጎረምሳ ተሳታፊዎች ክትባቱን ሲወስዱ 1,129 ደግሞ የሳላይን ፕላሴቦ ወስደዋል። ከግማሽ በላይ ለሚሆኑት ተሳታፊዎች ሁለተኛውን መጠን ከወሰዱ በኋላ ቢያንስ ለሁለት ወራት ለደህንነት ሲባል ክትትል ተደርጎላቸዋል።

Moderna

እድሜያቸው ከ 6 ወር- 5 አመት የሆኑ ህጻናት

  • ከ 6 ወር እስከ 6 አመት በታች የሆኑ 6,300 የሚጠጉ ህጻናት በ Moderna የ COVID-19 ክትባት ክሊኒካዊ ሙከራዎች ተሳትፈዋል። ክትባቱ በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኘው ቡድን COVID-19 ን በመከላከል ረገድ 50% ውጤታማ ነበር። በጥናቱ ውስጥ ምንም ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶች አልተታዩም፣ ይህም መካሄዱን ቀጥሏል።

እድሜያቸው ከ 6-11 የሆኑ ህፃናት

  • ከ 6 እስከ 11 አመት የሆኑ 4,000 የሚጠጉ ህጻናት በ Moderna የ COVID-19 ክትባት ክሊኒካዊ ሙከራዎች ተሳትፈዋል። የዚህ እድሜ ቡድን ለክትባቱ የሰጠው ምላሽ ከአዋቂዎች የበሽታ መከላከል ምላሽ ጋር አንፃራዊ ነው። በጥናቱ ውስጥ ምንም ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶች አልተታዩም፣ ይህም መካሄዱን ቀጥሏል።

እድሜያቸው ከ 12-17 የሆኑ ህፃናት

  • ከ 12-17 አመት የሆኑ 3,700 የሚጠጉ ህጻናት በ Moderna የ COVID-19 ክትባት ክሊኒካዊ ሙከራዎች ተሳትፈዋል። ይህ ክትባት በዚህ ቡድን ውስጥ COVID-19 ን በመከላከል ረገድ 93% ውጤታማ ነበር። በጥናቱ ውስጥ ምንም ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶች አልተታዩም፣ ይህም መካሄዱን ቀጥሏል።

Novavax

እድሜያቸው ከ 12-17 የሆኑ ህፃናት

  • ከ 12-17 አመት የሆኑ 2,200 የሚጠጉ ህጻናት በ Novavax የ COVID-19 ክትባት ክሊኒካዊ ሙከራዎች ተሳትፈዋል። ይህ ክትባት በዚህ ቡድን ውስጥ COVID-19 ን በመከላከል ረገድ 78% ውጤታማ ነበር። በጥናቱ ውስጥ ምንም ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶች አልተታዩም፣ ይህም መካሄዱን ቀጥሏል።