WA Notify የግላዊነት ፖሊሲ

ይህ የግላዊነት ፖሊሲ ለ WA Notify (የዋሺንግተን የተጋላጭነት ማሳወቂያ)፣ የ Washington ግዛት ይፋዊ የተጋላጭነት ማሳወቂያ ቴክኖሎጂ፣ ተግባራዊ ይሆናል። WA Notify የተፈጠረው በ Washington ግዛት Department of Health (DOH፣ የጤና መምሪያ) ሀላፊነት እና ድጋፍ ነው።

የምንሰበስበው እና የምንጠቀመው መረጃ ምንድነው?

ስለሚከተሉት ኩነቶች ማንነትን የማይገልጽ ውሂብ በ WA Notify ሊሰበሰብ ይችላል፦

 • WA Notify ን ማውረድ ወይም ማስቻል።
 • የተጋላጭነት ማሳወቂያ መቀበል።
 • የማረጋገጫ ኮድ ወይም የማረጋገጫ ሊንክ ማስገባት።
 • ሌሎችን ለማሳወቅ ለመረጡ ፖዘቲቭ የሆኑ ተጠቃሚዎች በዘፈቀደ የተመረጡ ኮዶችን መጫን።
 • መተግበሪያውን በተመለከተ ቴክኒካዊ ችግሮች ሲገጥሙ (የምርመራ ውሂብ፣ የመተግበሪያ ብቃት ቁጥሮችን ጨምሮ)።

DOH WA Notify እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ለመረዳት ከላይ ያለውን የኩነት መረጃ ይጠቀማል። ይህ ውሂብ ከ DOH፣ የህብረተሰብ ጤና ተቋማት፣ ወይም ፍቃድ ካላቸው የጤና ባለስልጣናት ጋር ሊጋራ ይችላል። በተጨማሪም ለቁጥር መረጃ ጥናት ወይም ሳይንሳዊ ጥናታዊ ጽሁፍ አላማ በድምር ቅጽ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ይህ መረጃ ማንኛውንም የግል ወይም የቦታ መረጃን አያካትትም ወይም ማንኛውምንም።

WA Notify የተጠቃሚውን ግላዊነት መጠበቅን እንደ ከፍተኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር አድርጎ ተዘጋጅቷል፣ ይህም ከ Google እና Apple ፍላጎት ጋር ይስማማል። WA Notify መሳሪያውን የሚጠቀም ማንኛውንም ሰው መለየት የሚችሉ ውሂቦችን ያልያዙ የሚከተሉትን የውሂብ ክፍሎች ይፈጥራል፦

በዘፈቀደ የተመረጡ ኮዶች

 • በዘፈቀደ የተመረጡ ኮዶች በ Bluetooth በኩል በ WA Notify ተጠቃሚ ስማርት ስልኮች መካከል ሲቀራረቡ ይጋራሉ።
 • በዘፈቀደ የተመረጡ ኮዶች የሚመነጩት እና የሚቀመጡት በእርስዎ ስማርት ስልክ ላይ እንጂ በ WA Notify አይደለም።
 • በዘፈቀደ የተመረጡ ኮዶች ጥቅም ላይ የሚውሉት WA Notify እና ስማርት ስልክዎ የ COVID-19 ተጋላጭነቶች ካሉ እንዲፈትሹ ብቻ ነው፡፡
 • በዘፈቀደ የተመረጡ ኮዶች ቢበዛ ለ 14 ቀናት ይቀመጣሉ፡፡

የማረጋገጫ ኮዶች እና ሊንኮች

 • የ WA Notify ተጠቃሚዎች ለ COVID-19 ተጋልጠው ሊሆን እንደሚችል በፍጥነት እና ምስጢራዊ በሆነ መንገድ ለማሳወቅ፣ DOH ለ DOH ሪፖርት ከተደረገ ፖዘቲቭ የ COVID-19 ምርመራ ውጤት ጋር ተያያዥ ለሆኑ ሁሉም የስልክ ቁጥሮች ማሳወቂያ እና/ወይም የፅሁፍ መልዕክት ከማረጋገጫ ሊንክ ጋር ይልካል።
  • ማሳወቂያውን መንካት ወይም የማሳወቂያ ሊንኩን ጠቅ ማድረግ በዘፈቀደ የተመረጡት የእርስዎ ኮዶች እንዲጋሩ ያስችላል፣ ይህም ሌሎች እርስዎ በአቅራቢያቸው የነበሩ የ WA Notify ተጠቃሚዎች ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ ማንነትዎ ሳይታወቅ ያነቃቸዋል።
  • DOH ለሁሉም ለ COVID-19 ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ላላቸው ሰዎች የጽሁፍ መልዕክት ከማረጋገጫ ሊንክ ጋር ይልካል ምክንያቱም WA Notify ን ማን እንደሚጠቀም አናውቅም። WA Notify የማይጠቀሙ ከሆነ፣ WA Notify ን ስልክዎ ላይ መጨመር ወይም ጽሁፉን ችላ ማለት ይችላሉ።
  • ሌሎች የ WA Notify ተጠቃሚዎችን ማንነትዎ ሳይታወቅ ለማንቃት ማሳወቂያውን ለመንካት ወይም የማረጋገጫ ሊንኩን ለመጫን እርስዎ ይወስናሉ።
 • የ COVID-19 ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ካልዎት፣ የአካባቢዎ የህብረተሰብ ጤና ባለስልጣን ሊያናግሮት፣ እና WA Notify እየተጠቀሙ መሆንዎን ሊጠይቆት ይችላል። ተጠቃሚ ከሆኑ እና ከወዲሁ የማረጋገጫ የጽሑፍ መልዕክት ካልደረስዎት፣ ወደ WA Notify እንዲያስገቡ የማረጋገጫ ኮድ ወይም ሊንክ ይሰጥዎታል።

የአጠቃቀም መመዝገቢያዎች

 • እንደማንኛውም መተግበሪያ ወይም የኢንተርኔት አገልግሎት ሁሉ፣ WA Notify አገልግሎቱን ሲጠቀሙ መዝገቦችን በራስ-ሰር ያመነጫል። እነዚህ መመዝገቢያዎች ስለ ስማርት ስልክዎ የተወሰነ መረጃን ያካትታሉ። በ WA Notify ችግሮችን ለመፍታት ይህንን መረጃ እንጠቀማለን።
 • እነዚህ መመዝገቢያዎች በዘፈቀደ የተመረጡ ኮዶችን ወይም የማረጋገጫ ሊንክ ወይም ኮዶችን አያካትቱም እንዲሁም ከሁለት አንዱን የኮድ አይነት ወደ እርስዎ ወይም ወደ ስማርት ስልክዎ ለማገናኘት ጥቅም ላይ አይውሉም።
 • እነዚህ መመዝገቢያዎች ከተፈጠሩ ከ 14 ቀናት በኋላ በራስ-ሰር ይሰረዛሉ፡፡

የትንታኔ ውሂብ

 • ተጨማሪ ትንታኔዎችን ለማሰራት ከመረጡ፣ መተግበሪያውን ለማሻሻል ውስን ድምር ውሂብ ለ DOH ይጋራል።
 • ይህ መረጃ መተግበሪያው እንዴት ጥቅም ላይ እንደዋለ ስታትስቲክስን ያካትታል። እርስዎን ለመለየት የሚያገለግል ማንኛውንም መረጃ አያካትትም።
 • በመተግበሪያው ውስጥ የትንታኔ ማጋራትን በማጥፋት ይህንን ውሂብ ላለማጋራት መምረጥ ይችላሉ።
 • በአሰራሩ መሰረት፣ WA Notify ከስማርት ስልክዎ የአካባቢ መረጃን አይሰበስብም፣ እርስዎ ወይም መሣሪያዎ ከሚያመነጩት የዘፈቀደ ኮዶች ወይም የማረጋገጫ ኮዶች ጋር የሚያያይዙ መረጃዎችን አይሰበስብም ወይም አያጋራም።

የምርመራ ውሂብ

 • እንደ ማንኛውም መተግበሪያ ወይም የኢንተርኔት አገልግሎት፣ WA Notify አገልግሎቱን ሲጠቀሙ በራስ ሰር የምርመራ ውሂብ ያወጣል።
 • የ Android WA Notify መተግበሪያ እንደ ሌሎች ተመሳሳይ የ Apple/Google ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀሙ መተግበሪያዎች የተሰራው በ Google ነው።
 • Google የ WA Notify እና የሌሎች ተመሳሳይ የ Apple/Google ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ መተግበሪያዎችን ችግር ለመመርመር ይህን መረጃ ይጠቀማል።
 • ይህ የምርመራ መረጃ ማንኛውንም ዓይነት ግላዊ ወይም የቦታ መረጃ አያካትትም ወይም ማንኛውንም የ WA Notify ተጠቃሚ ለመለየት ጥቅም ላይ አይውልም።

የማረጋገጫ ኮድ ሲጠይቁ ምን ይፈጠራል፦

በቤት ውስጥ በሚደረግ የ COVID-19 ምርመራ ፖዘቲቭ ውጤት የሚኖራቸው የ WA Notify ተጠቃሚዎች ሌሎች የ WA Notify ተጠቃሚዎችን ማንነታቸው ሳይታወቅ ሊከሰት ስለሚችል ተጋላጭነት ለማንቃት በ WA Notify የማረጋገጫ ኮድ ሊጠይቁ ይችላሉ። የማረጋገጫ ኮድ ለመቀበል፣ የ WA Notify ተጠቃሚዎች ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ያገኙበትን ቀን እና የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥራቸውን ማስገባት አለባቸው። ሌሎች የ WA Notify ተጠቃሚዎችን ሊከሰት ስለሚችል ተጋላጭነት ማንነታቸው ሳይታወቅ ለማንቃት ኮድ ለመጠየቅ ጥቅም ላይ የዋለው ተመሳሳይ መሳሪያ የማረጋገጫ ኮዱን ለማስገባት ወይም የማረጋገጫ ሊንኩን ጠቅ ለማድረግ ጥቅም ላይ መዋል አለበት።

የተመሳሳይ የምርመራ ውጤት ተደጋጋሚ ሪፖርቶችን ለመከላከል፣ WA Notify ኮድ ለመጠየቅ ጥቅም ላይ የዋለውን የተመሰጠረ ስልክ ቁጥር እስከ 30 ቀናት ድረስ በጊዜያዊነት ያከማቻል። ይህ መረጃ ማንኛውንም የግል ወይም የቦታ መረጃ አያካትትም ወይም ማንኛውንም የ WA Notify ተጠቃሚ ለመለየት ጥቅም ላይ አይውልም።

መረጃዎን መቼ ነው የምናጋራው?

እርስዎ የማረጋገጫ ኮዱን ለማስገባት ወይም የማረጋገጫ ሊንኩን ጠቅ ለማድረግ እስኪመርጡ ድረስ፣ ማንኛውንም የእርስዎን መረጃ በገዛ ፈቃዳችን አንሰበስብም ወይም ከማንም ጋር አናጋራም። ይህን ካደረጉ፣ WA Notify የዘፈቀደ ኮዶችዎን ከስማርት ስልክዎ አጠገብ ለነበሩ ሌሎች ስማርት ስልኮች ያጋራል፡፡ የማረጋገቻ ኮዱ ወይም ሊንኩ የስማርስ ስልክዎን ማግኘት በማይችል ሰው ተመልሶ ወደ እርስዎ ሊገናኝ አይችልም። በ WA Notify ውስጥ ምን አይነት መረጃ እንደሚሰበሰብ እና ጥቅም ላይ እንደሚውል የበለጠ ለማወቅ በዚህ ገጽ የላይኛው ክፍል ላይ “የምንሰበስበው እና የምንጠቀመው መረጃ ምንድነው?” የሚለውን ክፍል ይመልከቱ።

መረጃዎን እንዴት ነው የምንጠብቀው?

WA Notify የ Google እና Apple የተጋላጭነት ማሳወቂያ ማዕቀፍን በመጠቀም የዘፈቀደ ኮዶችን ይከላከላል፣ ይህም እንዴት ማመስጠር እና ማስተላለፍ እንደሚቻል በጣም የተወሰኑ መስፈርቶችን ያካትታል፡፡ WA Notify የዘፈቀደ ኮዶችዎን አያከማችም ወይም አያመነጭም - የእርስዎ ስማርት ስልክ ያደርገዋል።

በመረጃዎ ላይ ያሉ መብቶችዎ

የማረጋገጫ ኮዶቹ እና የማመልከቻ መመዝገቢያዎቹ ያለ ስማርት ስልክዎ ወደ እርስዎ ሊያያዙ ስለማይችሉ፣ ስለዚህ DOH ይህን መረጃ ለማግኘት ምንም መንገድ የለውም። በዚህም ምክንያት፣ DOH እርስዎ በሚጠይቁበት ጊዜ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ይህን መረጃ ማቅረብ ወይም መሰረዝ አይችልም። የ WA Notify አጠቃቀምን ይቆጣጠራሉ፡፡ ስማርት ስልክዎ የተጋላጭነት ማሳወቂያዎችን እንዲያጠፉ ወይም በማንኛውም ጊዜ በስማርት ስልክዎ ላይ የተከማቸውን የተጋላጭነት መመዝገቢያዎች እንዲሰርዙ መፍቀድ አለበት። በተጨማሪም፣ በማንኛውም ጊዜ WA Notify ን ማራገፍ ይችላሉ፡፡ ይህን ካደረጉ፣ የተከማቹ የዘፈቀደ ኮዶች በሙሉ ይወገዳሉ።