የ WA Notify የጽሁፍ መልእክቶች

Washington State Department of Health (DOH፣ ከዋሺንግተን ግዛት ጤና መምሪያ) የጽሁፍ መልእክት ወይም የስልክ ማሳወቂያ ደርሶዎት ነበር?

በስልክዎ ሊደርሱዎት የሚችሉ ሁለት ዓይነት የጽሁፍ መልእክቶች/ማሳወቂያዎች አሉ።

የ COVID-19 ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ማሳወቂያ፦

DOH ለ DOH ሪፖርት ከተደረገ ፖዘቲቭ የ COVID-19 ምርመራ ውጤት ጋር ተያያዥ ለሆኑ ሁሉም የስልክ ቁጥሮች ማሳወቂያ እና/ወይም የፅሁፍ መልዕክት ከማረጋገጫ ሊንክ ጋር ይልካል። ይህ ማሳወቂያ ለሌሎች የ WA Notify (WA ማሳወቂያ) ተጠቃሚዎች ለ COVID-19 ተጋልጠው ሊሆን እንደሚችል ማንነትዎ ሳይገለጽ እንዴት ሊያሳውቋቸው እንደሚችሉ መረጃ ይሰጣል።

እርስዎ የWA Notify ተጠቃሚ ከሆኑ፣ ማንነትዎ ሳይገለጽ ሊኖር ስለሚችል ተጋልጦ ለሌሎች ተጠቃሚዎች ለማሳወቅ ማድረግ ያለብዎት ብቸኛው ነገር ማሳወቂያውን መጫን ወይም በአጭር የጽሁፍ መልእክት ውስጥ ያለው ማስፈንጠርያ ላይ ክሊክ ማድረግ እና በ WA ማሳወቂያ (WA Notify) ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ደረጃዎች መከተል ነው።

የ WA Notify ተጠቃሚ ካልሆኑ፣ ፅሁፉን ችላ ማለት ይችላሉ። ወደ ስልክዎ እንዴት እንደሚያስገቡት ጨምሮ፣ ስለ WA Notify የበለጠ ማወቅ ከፈለጉ፣ WANotify.org ን ይጎብኙ

የግል መመርመርያ (በተጨማሪም የቤት ውስጥ ምርመራዎች እየተባሉ የሚታወቁትን) የሚጠቀሙ እና በ COVID-19 መያዛቸውን በምርመራ ያረጋገጡ የWA Notify ተጠቃሚዎች ማንነታቸው ሳይታወቅ ለሌሎች የWA Notify ተጠቃሚዎች ለ COVID-19 ተጋልጠው ሊሆን እንደሚችል ለማሳወቅ የማረጋገጫ ኮድ መጠየቅ ይችላሉ። በ WANotify.org ላይ “በግል ምርመራ በ COVID-19 መያዝዎን ካረጋገጡ ለሌሎች እንዴት ማሳወቅ ይችላሉ” የሚለውን ክፍል ይጎብኙ።

ያልተረጋገጠ የ COVID-19 ተጋላጭነት ማሳወቂያ፦

ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ የ WA Notify ተጠቃሚዎች የተጋላጭነት ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል።

የጽሁፍ መልእክቶቹ እና ማሳወቂያዎቹ ምን ይመስላሉ?

የ COVID-19 ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ማሳወቂያ፦

የጽሁፍ መልእክቱ እና ማሳወቂያው ምስል

pop up notification screenshot

 

የማሳወቂያው እና የጽሁፍ መልእክቱ ይዘት

የእርስዎን የኮቪድ-19 ምርመራ ያጋሩ

ማንነትዎ ሳይገለጽ ሌሎች COVID-19 ተጋልጠው ሊሆን እንደሚችል ለማሳወቅ እዚህ ጋር ነካ ያድርጉ። የማኅበረሰብዎ ደህንነት እንዲጠበቅ ለመርዳት ቅደም ተከተሎቹን ይከተሉ። ግላዊ መረጃዎ አይጋራም።

የጽሁፍ መልእክቱ እና ማሳወቂያው ምስል

text message screenshot

 

የማሳወቂያው እና የጽሁፍ መልእክቱ ይዘት

Message from (Mensaje del) WA Dept. of Health:

This number was given for a recent COVID-19 test. If this phone uses WANotify AND belongs to the person tested, please click the link within 24 hours. Follow the steps to anonymously alert others who may have been exposed.

https://us-wa.en.expressly/v?c=8w5io5c38ipo24fc

Se dio este numéro para una prueba reciente de COVID-19. Si este teléfono usa WANotify Y es de quien se hizo la prueba, haga clic en el enlace en las próximas 24 horas. Siga los pasos para alertar anónimamente a quienes tal vez hayan sido expuestos.

NOT the person tested? Need more information? Visit wanotify.org/text

¿NO es quien se hizo la prueba? ¿Desea más información? Visite notificawa.org/texto

የጽሁፍ መልእክቱ እና ማሳወቂያው ምስል

text message screenshot

 

የማሳወቂያው እና የጽሁፍ መልእክቱ ይዘት

Message from WA Dept. of Health:

If this phone uses WANotify AND belongs to the person tested, please click the link within 24 hours. Follow the steps to anonymously alert others who may have been exposed.

https://us-wa.en.expressly/v?c=5b56h13n80q9onll

NOT the person tested? Need more information? Visit wanotify.org/text.

የጽሁፍ መልእክቱ እና ማሳወቂያው ምስል

text message screenshot

 

የማሳወቂያው እና የጽሁፍ መልእክቱ ይዘት

Mensaje del Departamento de Salud del Estado de Washington:

Si este teléfono usa WANotify Y es de quien se hizo la prueba, haga clic en el enlace en las próximas 24 horas. Siga los pasos alertar anónimamente a quienes tal vez hayan sido expuestos.

https://us-wa.en.expressly/v?c=dvo8iije3v33saoj

¿NO es quien se hizo la prueba? ¿Desea más información? Visite notificawa.org/texto.

ያልተረጋገጠ የ COVID-19 ተጋላጭነት ማሳወቂያ፦

የጽሁፍ መልእክቱ እና ማሳወቂያው ምስል

exposure notification screenshot

የማሳወቂያው እና የጽሁፍ መልእክቱ ይዘት

ለ COVID-19 ተጋልጠው ሊሆን ይችላል

አዎንታዊ የ COVID-19 ምርመራ ውጤት የነበረው ሰው አቅራቢያ ነበሩ። ቀጥለው የሚያደርጉት ወሳኝ ነው እና እኛ በዚህ ልንረዳዎት አለን። የበለጠ ለማወቅ ነካ ያድርጉ።

የጽሁፍ መልእክት ወይም ማሳወቂያ ከደረሰኝ ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ?

የWA Notify ተጠቃሚዎች ማንነታቸው ሳይታወቅ ውጤታቸውን በዚህ መተግበርያ ላይ ለማረጋገጥ በጽሁፍ መልእክቱ ውስጥ ያለው ማስፈንጠርያ ላይ ክሊክ ማድረግ ወይም ማሳወቂያውን መጫን እና ሁሉንም ደረጃዎች መከተል አለባቸው። ይህም በቅርቡ በአቅራቢያው ለነበሩ ሌሎች የWA Notify ተጠቃሚዎች ሊኖር ስለሚችል የኮቪድ-19 ተጋልጦ ማንነትን ሳያሳውቅ እንዲነቁ ወይም እንዲያውቁ ያደርጋቸዋል። የ WA Notify ተጠቃሚዎች ውጤታቸውን ማንነታቸውን ሳያሳውቁ እንዲያረጋግጡ ማስቻሉ የ COVID-19 ስርጭትን በተሻለ ፍጥነት ይከላከላል። የህብረተሰብ ጤና አሁንም መድረስ እና በህመምተኛ ምርመራ ሂደት ጊዜ የማረጋገጫ ሊንክ ወይም ኮድ ሊሰጥ ይችላል።

የሚከተሉት ከሆኑ የመጀመሪያ እንክብካቤ ሰጪ ዶክተርዎን ወይም የምርመራ አቅራቢዎን እባክዎ ያነጋግሩ፦

  • የጽሁፍ መልእክት እና/ወይም ማሳወቂያ ተቀብለው፣ ነገር ግን ይፋዊ የምርመራ ውጤቶችዎን ካልተቀበሉ፣ ወይም
  • ስለ ምርመራ ውጤቶችዎ ጥያቂዎች ካልዎት

የተለመዱ ጥያቄዎች

WA Notify ማን እንደሆንኩ የማያውቅ ከሆነ፣ የጽሁፍ መልእክት እና/ወይም ማሳወቂያ እንዴት ይደርሰኛል?

የጽሁፍ መልእክቶቹ እና ማሳወቂያዎቹ የሚላኩት በ DOH ነው፣ በ WA Notify አይደለም። DOH ለሁሉም የ COVID-19 ምርመራ ውጤቱ ፖዘቲቭ ለሆነ ሰው የጽሁፍ መልእክት እና/ወይም ማሳወቂያ ይልካል ምክንያቱም WA Notify ን ማን እንደሚጠቀም አናውቅም።WA Notify እየተጠቀሙ ካልሆነ፣ የጽሁፍ መልእክት እና ማሳወቂያውን ችላ ማለት ይችላሉ።

የጤና መምሪያ (DOH) የጽሁፍ መልእክት ወይም ማሳወቂያ ለማን መላክ እንዳለበት የሚያውቀው እንዴት ነው?

በህግ መሰረት፣ ብዙ የኢንፌክሸስ በሽታዎች ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤቶች ከመገኛ መረጃ ጋር ለግዛቱ ሪፖርት መደረግ አለባቸው። ጤና መምሪያ (DOH) ይህን መረጃ የሚጠቀመው የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የጉዳይ ምርመራዎችን ለማድረግ እና ንክኪን ለመከታተል (እንግሊዘኛ ብቻ) ነው። ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤቶች ያላቸውን ሁሉንም ሰዎች ማሳወቅ የ WA Notify ተጠቃሚዎች በፍጥነት እርምጃ እንዲወስዱ እና ማነታቸው ሳይታወቅ ሊሎች ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን እንዲያነቁ ያስችላቸዋል።

እኔ WA Notify ን እየተጠቀምኩ አይደለም። የጽሁፍ መልእክት የላካችሁልኝ ለምንድነው?

DOH ለ COVID-19 ምርመራ በቅርቡ ፖዘቲቭ የሆኑ ሰዎች ለሚጠቀሙባቸው ስልክ ቁጥሮች የጽሁፍ መልእክት እና/ወይም ብቅ የሚል ማሳወቂያ ይልካል።

DOH ብቻ ማን ፖዘቲቭ እንደሆነ ያውቃል –WA Notify ን ማን እንደሚጠቀም አናውቅም። የጽሁፍ መልእክቶች ለሁሉም ሰው በመላክ፣ የ WA Notify ተጠቃሚዎች ማንነታቸው ሳይታወቅ ሊጋለጡ የሚችሉ ሌሎች ሰዎችን በተሻለ ፍጥነት እንዲያነቁ እና ህይወትን እንዲያድኑ ይረዳል።

እርስዎ የ WA Notify ተጠቃሚ ካልሆኑ፣ ምንም ነገር ማድረግ አያስፈልግዎትም። ስልክዎ ላይ እንዴት እንደሚጨምሩት ማወቅን ጨምሮ ስለ WA Notify የበለጠ ለማወቅ የሚፈልጉ ከሆነ፣ WANotify.org ን ይጎብኙ

የጽሁፍ መልእክቱን የሚልከው ስልክ ቁጥር ስንት ነው?

DOH የሚልክበት ቁጥር 1-844-986-3040 ነው።

ማሳወቂያ እና/ወይም የጽሁፍ መልእክት ደርሶኛል ነገር ግን የተመረመረው ሰው የቤተሰብ ወይም የቤት አባል ነበር። ምን ማድረግ አለብኝ?

ፖዘቲቭ የሆነ የ WA Notify ተጠቃሚ ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች ሰዎችን ማንነቱ ሳይታወቅ ለማንቃት ደረጃዎችን መከተል አለበት፣ ስለዚህ ለእርስዎ ያልሆኑ ማንኛውንም መልእክቶች ወይም ማሳወቂያዎች ችላ ማለት አለብዎት።

ቤተሰብዎ ወይም የቤተሰብዎ አባል የWA Notify ተጠቃሚ ከሆነ፣ በበሽታው መያዛቸውን በምርመራ ካረጋገጡ እና አሁንም ውጤታቸውን በWA Notify ውስጥ ማረጋገጥ የሚፈልጉ ከሆነ፣ በ WANotify.org ላይ “በግልምርመራ በኮቪድ-19 መያያዎን ካረጋገጡ ለሌሎች እንዴት ማሳወቅ ይችላሉ”. በሚለው ክፍል ውስጥ ያሉትን ደረጃዎች መከተል ይችላሉ።

ማሳወቂያውን ለመንካት ወይም የማረጋገጫ ሊንኩን ለማንቃት ምን ያክል ጊዜ አለኝ?

WA Notify ውስጥ ሌሎችን ለማሳወቅ እርምጃዎቹን ለመከተል ማሳወቂያው ወይም የጽሁፍ መልእክት ከደረሰዎት በኋላ 24 ሰአት አልዎት። በዚያ ጊዜ ውስጥ ማሳወቂያውን መጫን ወይም የማረጋገጫ ማስፈንጠርያውን ክሊክ ማድረግ ካልቻሉ፣ በዚህ WANotify.org ገጽ ላይ በግል ምርመራ በኮቪድ-19 መያዝዎን ካረጋገጡ ለሌሎች እንዴት ያሳውቃሉ በሚለው ክፍል ውስጥ ያሉትን ደረጃዎች በመከተል በ WA Notify ውስጥ የማረጋገጫ ኮድ ሊጠይቁ ይችላሉ።

WA Notify ውስጥ ያለ የማረጋገጫ ሊንክን ለማንቃት የጽሁፍ መልእክት ወይም ማሳወቂያን ከአንድ ሰው በላይ መጠቀም ይችላል?

የለም። የእርስዎ ቤተሰብ ወይም የቤተሰብ አባል የWA Notify ተጠቃሚ ከሆነ፣ በበሽታው መያዙን በምርመራ ካረጋገጠ እና አሁንም የምርመራ ውጤታቸውን በWA Notify ውስጥ ለማረጋገጥ የሚፈልጉ ከሆነ፣ በ WANotify.org ላይ “በኮቪድ-19 መያዝዎን በግል ምርመራ ካረጋገጡ ለሌሎች እንዴት ማሳወቅ ይችላሉ” የሚለው ክፍል ውስጥ ያሉትን ደረጃዎች መከተል ይችላሉ።

በ WA Notify ላይ ተጋላጭ የሆንኩበትን ቀን እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

በ iPhone ላይ፦

  1. ወደ Settings (ቅንብሮች) ይሂዱ
  2. Exposure Notifications (የተጋላጭነት ማሳወቂያዎች) የሚለውን ይምረጡ ወይም Exposure Notifications ን በፈልግ አሞሌ ውስጥ ያስገቡ
  3. የእርስዎ ሊኖር የሚችል ግምታዊ የተጋልጦ ቀን “You may have been exposed to COVID-19” (“ለኮቪድ-19 ተጋልጠው ሊሆን ይችላል”) ስር ይታያል።

በ Android ላይ፦

  1. የ WA Notify መተግበሪያን ይክፈቱ
  2. በ “Possible exposure reported (ሪፖርት የተደረገ ሊከሰት የሚችል ተጋላጭነት)” ስር See Details (ዝርዝሮችን ይመልከቱ) የሚለውን ይምረጡ
  3. የእርስዎ ሊኖር የሚችል ግምታዊ የተጋልጦ ቀን “Possible Exposure Date” (“ሊሆን የሚችል የተጋልጦ ቀን”) ስር ይታያል።