የምርመራ ኪቶችን ማግኘት
- የ COVID-19 ምርመራ የት ማግኘት እችላለሁ?
-
እባክዎን የሚከተሉትን አማራጮች ይሞክሩ፡ -
- አቅራቦቶች እያሉ፣ ነጻ የምርመራ ኪት ከ አዎ ይበሉ! ይዘዙ COVID Test (በእንግሊዘኛ) ወይም የቋንቋ እርዳታ ለማግኘት በ 1-800-525-0127 ይደውሉ እና # ን ይጫኑ። ትዕዛዙን ለአንድ ቤት አንድ በማድረግ ይወስኑ።
- ከፌደራሉ ፕሮግራም ነጻ የምርመራ ኪት በ COVIDTests.gov (በእንግሊዘኛ) ይዘዙ። ትዕዛዙን ለአንድ ቤት አንድ በማድረግ ይወስኑ።
- የቤት ውስጥ መመርመሪያን በአካባቢ ቸርቻሪዎች እና ፋርማሲዎች ይግዙ።
- የጤና መድህን ካለዎት በመድን እቅድዎ ስር ለታቀፈ ለእያንዳንዱ ሰው፣ አብዛኞቹ መድን ሰጪዎች በየወሩ እስከ 8 የሚደርሱ የቤት ውስጥ መመርመሪያዎችን ዋጋ መመለስ ጀምረዋል። የበለጠ መረጃ እዚህ (በእንግሊዝኛ) ያንብቡ።
- ከእርስዎ አጠገብ ባለው የምርመራ ቦታ (በእንግሊዘኛ) ላይ ምርመራ ያግኙ።
በአቅራቢያዎ ያለ የምርመራ ጣቢያ ለማግኘት እገዛ ከፈለጉ ከ የአከባቢዎ የጤና መምሪያ ወይም ወረዳ (በእንግሊዝኛ) ጋር ያረጋግጡ። እንዲሁም 1-800-525-0127 በመደወል # ን መጫን ይችላሉ። ሲያነሱት፣ የአስተርጓሚ አገልግሎቶችን ለማግኘት ቋንቋዎን ይናገሩ።
- የበይነመረብ አገልግሎት የማገኝበት የለኝም / ድር ጣቢያው በቋንቋዬ አይገኝም። WA ውስጥ ነጻ ኪት እንዴት ነው የማዝዘው?
-
እባክዎን በ 1-800-525-0127 ይደውሉ፣ በመቀጠል # ን ይጫኑ። የቋንቋ ድጋፍን ማግኘት ይቻላል። የጥሪ ማዕከሉ እርስዎን ወክሎ በWA እና በፌደራል የመስመር ፖርታሎች በኩል ማዘዝ ይችላል።
- ስለ Say Yes! COVID Test የኦንላይን ፖርታል ማወቅ ያለብኝ ምንድን ነው?
-
ይህ ፕሮግራም በ Washington መንግስት እና በ National Institutes of Health (ብሄራዊ የጤና ተቋማት) እና Centers for Disease Control and Prevention (የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከያ ማዕከል) መካከል የሚደረግ የትብብር ጥረት ነው። አቅርቦቶች በሚቆዩበት ጊዜ፣ በ Washington አካባቢ ያሉ ሰዎች ሁለት ፈጣን የ COVID-19 ኪቶችን በማዘዝ በቀጥታ በአማዞን ወደ ቤታቸው ይደርስላቸዋል።
በቤተሰብ/የመኖሪያ አድራሻ፣ በየወሩ፣ ሁለት ትዕዛዞች ብቻ ነው የሚደረገው እና እያንዳንዱ ትዕዛዝ ከ 5 ፈጣን ምርመራዎች ጋር ይመጣል። ሁሉም ትዕዛዞች እና መላኪያዎች ነጻ ናቸው።
ስለራሱ ስለምርመራው እና እንዴት እንደሚተገበር በተያያዘ ለሚነሱ ጥያቄዎች፣ Say Yes! COVID Test ዲጅታል ረዳት ን ይጎብኙ ወይም በ 1-833-784-2588 ይደውሉ።
- ሁለቱንም የ Say YES! COVID Test ከ DOH እና ከፌደራል መመርመሪያ ኪት ማዘዝ ይችላሉ?
-
አዎ፣ በ Washington ሃገር የሚኖሩ ከሆነ፣ የቤት ውስጥ ፈጣን የ COVID-19 መመርመሪያ ኪቶች ለመቀበል በሁለቱም የ Say YES! COVID Test ድህረ ገጽ እና በ ፌደራል ድህረ ገጽ ትዕዛዝዎን ማስቀመጥ ይችላሉ።
- ተጨማሪ ጥያቄዎች ካሉኝ ወዴት መሄድ እችላለሁ?
-
ስለ DOH Say Yes! COVID Test (የጤና መምሪያ አዎ ይበሉ! የኮቪድ ምርመራ)ፕሮግራም ተጨማሪ ጥያቄዎች ካልዎት፣ በተደጋጋሚ የተጠየቁ ጥያቄዎች ገጽ ን ይጎብኙ ወይም ለ የ DOH COVID-19 የስልክ መስመር በ 1-800-525-0127 ይደውሉ (የቋንቋ እርዳታ ያገኛሉ)። ስለ ፌደራል የምርመራ ፕሮግራም ለሚነሱ ጥያቄዎች፣ በተደጋጋሚ የተጠየቁ ጥያቄዎች ገጽ የሚለውን ይጎብኙ።
- ነፃ ምርመራዎቼን መቼ ነው የማገኘው?
-
በሁለቱም ፕሮግራሞች የተጠየቁ ምርመራዎች (Say YES!COVID Test (አዎ ይበሉ! የ COVID ምርመራ) ወይም Federal Program (ፌደራል ፕሮግራም)) ብዙ ጊዜ በታዘዙ 1-2 ሳምንት ውስጥ ይደርሳሉ።
- ሁሉንም የሚመከሩ የምርመራ አማራጮችን ከተከተልኩ በኋላ፣ አሁንም የትም ቦታ ምርመራ ማግኘት አልቻልኩም። COVID-19 እንዳለብኝ ካሰብኩ ምን ማድረግ አለብኝ?
-
የ COVID-19 ምርመራን ለማግኘት እየተቸገሩ ስለሆነ እናዝናለን፣ በአሁኑ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ አቅርቦት ውስን መሆኑን እናውቃለን።
የ COVID-19 ምልክቶች ግጥሞት ከሆነ ወይም ለ COVID-19 ከተጋለጡ እና ሊያዙ ይችላሉ የሚል ስጋት ካለዎት የሚከተሉትን እንመክራለን፦
- ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ተመሳሳይ መመሪያ ይከተሉ።
- ራስዎን ማግለል ካልቻሉ፣ የሚከተሉትን ማድረግ አለብዎት፦
- ከቤትዎ ውጭ ባሉ ሌሎች ሰዎች (በተቻለ መጠን KN95፣ KF-94፣ ወይም ባለ 3-ድርብ የቀዶ ጥገና የፊት መሸፈኛ ጭምብል፣ ከተቻለ) በማንኛውም ጊዜ አፍንጫዎን እና አፍዎን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ የሚሸፍን ጭንብል ያድርጉ።
- ከሌሎች ሰዎች ቢያንስ 6 ጫማ/2 ሜትር ርቀት ይኑርዎት።
- እጆችዎን በተደጋግሚ ይታጠቡ።
- ብዙ ሰዎች የሉበትን እና ትልቅ ስብሰባዎችን ያስወግዱ።
- በቤቴ ውስጥ ከአራት በላይ ቤተሰብ አሉ። ለሁሉም የቤተሰብ አባሎቼ እንዴት ምርመራ ማግኘት እችላለሁ?
-
- በ Washington የ Say YES! COVID Test ድህረ ገጽ በኩል በወር ሁለት የመመርመሪያ ኪቶችን (እስከ 5 ምርመራዎችን ጨምሮ) ማግኘት ይችላሉ።
- በ COVIDtests.gov ከፌደራል ፕሮግራም ሁለት ተጨማሪ የመመርመሪያ ኪቶችን (4 ምርመራዎችን ጨምሮ) ማግኘት ይችላሉ።
- ተጨማሪ የቤት ውስጥ ምርመራዎችን በአቅራቢያዎ ወይም በኦንላይን ላይ ከቸርቻሪዎች እና ከፋርማሲዎች መግዛት ይችላሉ።
- በአቅራቢያዎ ካለ የመመርመሪያ ቦታ የ PCR ምርመራ ማግኘት ይችላሉ። እዚህ አንዱን ያግኙ።
- የእኔን የመመርመሪያ ኪት የምጠቀመው እንዴት ነው?
-
ትክክለኛ ውጤት ለማግኘት በኪቱ ውስጥ ያሉትን ፈጣን የቤት ውስጥ ምርመራዎችን መመሪያዎች መከተል ያስፈልጋል። ለማንኛውም ልዩ ጥያቄዎች የመመርመሪያ አምራቹን (መረጃቸው በሳጥኑ ውስጥ ይገኛል) ያነጋግሩ።
በፈጣን ምርመራዎች የውሸት አሉታዊ ውጤቶች ሊከሰቱ ይችላሉ። አንዳንድ የመመርመሪያ ኪቶች ሁለት ምርመራዎችን ሊያካትቱ ይችላሉ (ለመመርመር በሳጥኑ ላይ ያሉትን መመሪያዎች ይከተሉ)።
አጠቃላይ ምርመራ
- መመርመር ያለበት ማነው?
-
ህመም ከተሰማዎት ይመርመሩ። COVID-19 ሰፋ ያሉ ምልክቶች አሉት፣ ስለዚህ ጥሩ ስሜት የማይሰማዎት ከሆነ፣ በተቻለ ፍጥነት ምርመራ ማድረጉ ተመራጭ ነው።
ለ COVID-19 ፖዘቲቭ ለሆነ ሰው ሲጋለጡ ምርመራ ያድርጉ። ምልክቶችን የሚያሳዩ ከሆነ በአስቸኳይ ምርመራ ያድርጉ። ምልክቶችን የማያሳዩ ከሆነ፣ ከተጋለጡበት ቀን በኋላ ለአምስት ቀናት ይጠብቁ እና ከዚያ ይመርመሩ።
በ Washington ውስጥ ያሉ ቢዝነሶች እና የዝግጅት ቦታዎች ወደ ተቋም ወይም ዝግጅት ከመግባታቸው በፊት የምርመራ እና/ወይም ክትባት መስፈርት ሊኖራቸው ይችላል። ከመጎብኘትዎ በፊት ይደውሉ ወይም ድህረ ገጻቸውን ይመልከቱ።
ከጉዞዎ በፊት እና/ወይም በኋላ መመርመር ሊያስፈልግዎት ይችላል። የ Centers for Disease Control and Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከላት) ን የቅርብ ጊዜ የጉዞ መመሪያ ይመልከቱ።
ከቡድን ሰዎች ጋር፣ በተለይ ለከባድ በሽታ ተጋላጭ ከሆኑ ወይም የ COVID-19 ክትባታቸውን ወቅታዊ ያላደረጉ ሰዎች ጋር በሚሰበሰቡበት ጊዜ።
- አዎንታዊ ምርመራ ካደረግኩኝ ምን ይሆናል?
-
የቅርብ ጊዜውን የ Centers for Disease Control and Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከላት) እና የ DOH መመሪያን ተከተሉ እና በቤት ራስዎን ያግልሉ ይከተሉ፣ ከሌሎች ይራቁ። ሁሉም የቅርብ ግንኙነቶች ኳራንቲን መግባት አለባቸው።
- COVID-19 እንደያዘው የሚያስብ ወይም ያረጋገጠ ሰው በሙሉ ቤቱ በመሆን ራሱን ከሌሎች ሰዎች ቢያንስ ለ 5 ሙሉ ቀናት ማግለል አለበት (ቀን 0 የምልክቶቹ የመጀመሪያ ቀን ወይም ምልክቱ ላልታየባቸው ሰዎች የመጀመሪያው አዎንታዊ ምርመራ ያደረጉበት ቀን ነው)። ለተጨማሪ 5 ቀናት በቤት ከሰዎች ጋር ሲሆኑ እና ከቤት ውጪ ማስክ ማድረግ አለባቸው።
- አንድ ሰው ምርመራ የማድረግ ዕድል ካለው እና ምርመራ ማድረግ ከፈለገ፣ ምርጡ መንገድ የሚሆነው የ 5 ቀኑ ራስ የማግለል ጊዜ መጨረሻ ላይ አንቲጅን ምርመራ ማድረግ ነው። ትኩሳት መቀነሻ መድኃኒት ሳይወስዱ ለ 24 ሰዓታት ከትኩሳት ነፃ ከሆኑና ሌሎቹ ምልክቶችዎ ከተሻሻሉ ብቻ የምርመራ ናሙናውን ይሰብስቡ (ካገገሙ በኋላ ለሳምንታት ወይም ለወራት ጣዕም እና ማሽተት አለመኖር ሊቀጥሉ ስለሚችሉ ራስን ማግለል ማብቂያውን ሊያዘገዩ አይገባም)።
- የምርመራዎ ውጤት አዎንታዊ ከሆነ እስከ 10 ቀን ድረስ ራስዎን ማግለልዎን መቀጠል አለብዎት።
- የምርመራዎ ውጤት አሉታዊ ከሆነ፣ ራስዎን ማግለልን ማቆም ይችላሉ፣ ነገር ግን እስከ 10ኛው ቀን ድረስ በቤት ውስጥ እና ሕዝብ በሚሰበሰብበት በደምብ የሚሆንዎትን የፊት መሸፈኛ ጭምብል ማድረግዎን ይቀጥሉ።
በቤት ውስጥ ለተደረገ የ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ውጤት እና የእንክብካቤ አገልግሎቶችን ለማግኘት፣ እባክዎን ወደ ዋሽንግተን ግዛት የ COVID ነጻ የስልክ መስመር በ 1-800-525-0127 ይደውሉ። የቋንቋ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።
በስማርት ስልክዎ ላይ WA Notify (የዋሺንግተን የተጋላጭነት ማሳወቂያ) ከተጫነ፣ ይህን መሳሪያ በመጠቀም አወንታዊ የምርመራ ውጤትንም ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ።
የበለጠ መረጃ እዚህ መገኘት ይችላልል፦ የምርመራ ውጤቱ አዎንታዊ ከሆነ ምን መደረግ አለበት.
- አንድ ሰው ከተጋለጠ በኋላ፣ ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ሊኖረው ይችላል?
-
አንድ ሰው በ COVID-19 ከተያዘ በኋላ፣ ከተጋለጠ በኋላ ለአምስት ቀናት የ PCR ምርመራው የቫይረሱን መኖር ላያሳይ ይችላል። ስለዚህ፣ ሊኖርብዎት ይችላል፣ ግን ለትንሽ ጊዜ ምርመራው ላያሳየው ይችላል። ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ለማግኘት ጊዜ መስጠት ቁልፍ ነገር ነው። ለ COVID-19 ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉበት ሁኔታ እያለ ነገር ግን ካልታመሙ፣ ተጋላጭ የሚሆኑበት የመጨረሻው ቀን ካለቀ ቢያንስ ከ 5 ቀናት በኋላ ምርመራ ቢያደርጉ ተመራጭ ነው። የአንቲጂን ምርመራዎች በአጠቃላይ ምልክት ያላቸው ሰዎች ላይ ትክክለኛ ናቸው ነገር ግን በአንዳንድ ሁኔታዎች ምልክት የሌላቸው ሰዎች ላይም ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።
- ውጤቶቹ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳሉ?
-
በምርመራው አይነት እና ናሙናው ለምርመራ የተላከበት ቦታ ይወሰናል። የአንቲጂን ምርመራ ውጤቶች በ10 ደቂቃ ፍጥነት ሊመለሱ ይችላሉ። የ PCR ምርመራ፣ በርካታ ቀናትን ሊወስድ ይችላል።
- የትኛው ምርመራ መውሰድ የተሻለ ነው?
-
ለእርስዎ ተመራጭ የሆነው ምርመራ መጀመሪያ የሚያገኙት ነው። ይህ ማለት እጅዎ ላይ የቤት ውስጥ መመርመሪያ ካለዎት፣ እርሱን ይጠቀሙ። ለመመርመሪያ የሚሆን ቀጠሮ እንዳሉ ካዩ፣ ይመልከቱት። አንድ የተለየ ሁኔታ ልዩ ለሆነ ሁኔታ (ለምሳሌ ጉዞ) ምርመራ ሲያስፈልግ ነው።
- ምርመራዎችን መግዛት ይኖርብኛል?
-
የተወሰኑ ምርመራዎችን በእጅ መያዝ ጥሩ ሃሳብ ነው። በመንግስት ድህረ ገጾች በኩል ሲገኙ ምርመራዎችን ይዘዙ። ግብይት ላይ ከሆኑ እና ምርመራዎች እንዳሉ ካዩ፣ ጥቂት ይግዙ። ነገር ግን ጥሩ ጎረቤት ይሁኑ እና ምርጥ ፍርድ ይጠቀሙ። ብዙ ምርመራዎችን ማከማቸት ሌሎች ሊያስፈልጋቸው የሚችሉ ሰዎችን ተደራሽነት ይገድባል እንዲሁም እርስዎ መጠቀም ከመቻልዎ በፊት ምርመራዎች የአገልግሎት ጊዜያቸው የማለፍን ስጋት ይጋፈጣሉ።