በ COVID-19 ክትባት ላይ መተማመን ሊኖርዎት ይችላል!
በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ አብዛኛዎቹ ሰዎች የ COVID-19 ክትባት ለመውሰድ አቅደዋል፣ ግን አንዳንዶቹ ክትባት ከመውሰዳቸው በፊት ተጨማሪ መረጃ ሊፈልጉ ይችላሉ። ይህ ፍጹም የተለመደ ነው። ሕይወታችንን የሚመለከት ማንኛውንም ውሳኔ ለማድረግ ሁላችንም በራስ የምንተማመን መሆን እንፈልጋለን።
በራስ ለመተማመን፣ ከታመኑ ምንጮች መረጃ እንፈልጋለን። የ COVID-19 ክትባትን በተመለከተ ባልተረጋገጡ ወሬዎች እና እውነታዎች መካከል ያለውን ልዩነት እንዲለዩ ጓደኞችዎን እና ቤተሰብዎን ይርዷቸው።
ሠዎች ለመከተብ በሚያደርጉት ውሳኔ በራስ መተማመን እንዲኖራቸው መርዳት ይችላሉ። የሚከተሉትን በማድረግ ይህንን ማሳካት ይችላሉ፦
- የጓደኛዎን ወይም የቤተሰብዎን ስጋቶች ለማዳመጥ ጊዜ በመውሰድ። ስለ ክትባቶች ውይይት እንዴት እንደሚደረግ ጠቃሚ ምክሮች ለማግኘት ስለ ክትባቶች መመሪያ ማውራት (በእንግሊዝኛ ብቻ) ይህንን ይመልከቱ።
- ጥያቄዎቻቸውን መመለስ። መልሱን የማያውቁት ከሆነ ከጤና እንክብካቤ አቅራቢው ጋር እንዲነጋገሩ ሊጠቁሙ ይችላሉ።
- ክትባት ለመውሰድ ሲወስኑ፣ የወሰኑበትን ምክንያቶች ለሌሎች ያጋሩ። የግል ታሪክዎ በቤተሰብዎ እና በማህበረሰብዎ ላይ ኃይለኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
በሚናገሩት እና በሚያደርጉት ነገር በዙሪያዎ ያሉት ላይ ተጽዕኖ የማድረግ ችሎታ አለዎት። እነዚህን ምክሮች በ COVID-19 ክትባቶች ዙርያ እንዴት ከጓደኞችዎ እና ከቤተሰብ ጋር መነጋገር እንዳለቦት (በእንግሊዝኛ ብቻ) ላይ ይመልከቱ።
ከዚህ በታች የክትባቱን እውነታዎች ይመልከቱ እና ለሚያውቋቸው ሰዎች ያጋሩ። በታዋቂ ርዕሶች ከፋፍለን አዘጋጅተነዋል፡፡
ደህንነት እና ውጤታማነት
የኮቪድ -19 ክትባት መወሰዴ ወይም አለመውሰዴ ምን ለውጥ ያመጣል?
የ COVID -19 ክትባትን መውሰድ ፍፁም የእርስዎ ምርጫ ነው፣ ግን ይህንን ወረርሽኝ ለመግታት በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎች ይህንን ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ ያስፈልገናል። በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ብዙ ሰዎች በሽታውን – በክትባትም ሆነ በቅርብ ኢንፌክሽን – መከላከል ሲችሉ ለ COVID-19 ቫይረስ መስፋፋት ከባድ ይሆናል። የክትባታችን መጠን ከፍ ባለ መጠን፣ የኢንፌክሽን መጠኑ ይቀንሳል።
ክትባት ያልወሰዱ ሰዎች አሁንም በቫይረሱ በመያዝ ወደ ሌሎች ሊያስተላልፉ ይችላሉ። አንዳንድ ሰዎች በሕክምና ምክንያቶች ክትባቱን መውሰድ አይችሉም፣ ይህ ደግሞ በተለይ ለ COVID-19 ተጋላጭ ያደርጋቸዋል። ክትባት ካልወሰዱ፣ እርስዎም በከፍተኛ ሁኔታ በ የ COVID-19 ተለዋዋጭ ዝርያ (እንግሊዝኛ ብቻ) የተነሳ ሆስፒታል የመተኛት ወይም ለሞት ተጋላጭ ኖት፡፡ ክትባት መውሰድ እርስዎን ብቻ ሳይሆን ቤተሰብዎን፣ ጎረቤቶችዎን እና ማህበረሰብዎን ይጠብቃል።
ብዙ ሰዎች ቫይረሱን የሚቋቋሙት ከሆነ የ COVID-19 ክትባትን መውሰድ ለምን ያስፈልገኛል?
ብዙ በ COVID-19 የተጠቁ ሰዎች መለስተኛ ምልክቶች ብቻ ይታይባቸዋል። ሆኖም ግን፣ ቫይረሱ እጅግ ሊገመት የማይችል ነው፣ እና አንዳንድ የ COVID-19 ተለዋዋጭ ዝርያዎች የተለያዩ ምልክቶችን በማሳየት ሊያሳምሙዎት ይችላሉ። ሥር የሰደደ የጤና ችግር የሌለባቸውም ወጣቶች እንኳን ቢሆኑ፣ አንዳንድ ሰዎች በ COVID-19 በጣም ሊታመሙ ወይም ሊሞቱ ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ፣ “የ COVID ረዥም- ተጓዥች” በመባል የሚታወቁት ለወራት የሚቆዩ ምልክቶችን በማሳየት የሕይወታቸውን ጥራት ሊያስተጓጉሉ ይችላሉ። አዲስ ቫይረስ እንደ መሆኑ መጠን የ COVID-19 የረጅም ጊዜ ጉዳቶችን ገና አላውቅንም። ክትባት መውሰድ ከቫይረሱ ለመከላከል ከሁሉ የተሻለው መከላከያችን ነው።
ክትባቶቹ በእርግጥ አስተማማኝ ወይም ውጤታማ ናቸው?
አዎ፣ የ COVID-19 ክትባቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ውጤታማ ናቸው። የሳይንስ ሊቃውንት ክትባቱን በሕክምና ሙከራዎች ውስጥ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ላይ ሞክረዋል። ክትባቶቹ የ U.S. Food and Drug Administration (FDA፣ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር) የአስቸኳይ ጊዜ አጠቃቀምን ፈቃድ ለማግኘት የሚያስፈልገውን የደህንነት፣ ውጤታማነት እና የማምረቻ ጥራት መለኪያዎች ያሟሉ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ሰዎችን በ COVID-19 ከመታመም በመከላከል ረገድ ሁሉም በጣም ጥሩ ሆነው ተገኝተዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እነዚህ ክትባቶች በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች በጥንቃቄ ተሰጥተዋል።
ስለ COVID-19 ክትባቶች እንዴት እንደሚሠሩ የበለጠ ለማወቅ እነዚህን ተንቀሳቃሽ ምስሎች ይመልከቱ፦
ክትባቱ ለልጄ ጤንነት አስተማማኝ ነው?
አዎ። የ Pfizer ክትባት በሺዎች በሚቆጠሩ ታዳጊዎች እና ወጣቶች ላይ ተሞክሮ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው። እንዲሁም በጣም ውጤታማ ነበር - ክትባቱን ከወሰዱ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች መካከል አንዳቸውም በ COVID-19 አልተጠቁም። የ Centers for Disease Control and Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከላት) የ COVID -19 ክትባትን ለሁሉም 6 ወር ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆናቸው (በእንግሊዘኛ ብቻ) ይመክራል።
ክትባቶቹ ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን እንዴት ማመን እችላለሁ?
የ COVID-19 ክትባቶች ደሕንነታቸዉ የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ Centers for Disease Control & Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል) የሀገሪቱን የክትባት ደሕንነት የመቆጣጠር አቅምን አስፋፍቷል፣ አጠናክሯል። በዚህ ምክንያት፣ የክትባት ደሕንነት ባለሙያዎች የ COVID-19 ክሊኒካል ሙከራ ግዜ ላይ ላይታዩ የሚችሉ ጉዳዮችን ሊቆጣጠር እና ሊያዉቁ ይችላሉ።
ከ COVID-19 ክትባት COVID-19 ሊይዘኝ ይችላል?
አይ፣ ከክትባቱ COVID-19 ሊይዝዎት አይችልም። የ COVID-19 ክትባቶች COVID-19 ን የሚያመጣውን ቫይረስ አይዙም።
ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል የ COVID-19 ክትባቶች በሰውነትዎ ውስጥ እንዴት እንደሚሠሩ የበለጠ ያብራራል፦
ከዚህ ቀድሞ COVID-19 ከነበረብኝ ክትባቱን መውሰድ አለብኝ?
አዎ፣ እርስዎ ቀድሞውኑ COVID-19 ከነበረብዎት አሁንም ክትባት መውሰድ አለብዎት። ውሂቡ በበሽታው ከተያዙ በኋላ ባሉት 90 ቀናት ውስጥ በ COVID-19 እንደገና መያዝ ያልተለመደ መሆኑን ያሳያል። ይህም ማለት ለትንሽ ጊዜ ከ COVID-19 የተወሰነ ጥበቃ (ተፈጥሯዊ በሽታ የመከላከል አቅም ይባላል) ሊኖርዎት ይችላል ማለት ነው። ሆኖም፣ ተፈጥሯዊ በሽታ የመከላከያ አቅም ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ አናውቅም። ለምን አሁንም የ COVID-19 ክትባት መውሰድ እንዳለብዎት (በእንግሊዘኛ ብቻ) የበለጠ ይወቁ።
በክትባት እና በሽታ የመከላከል አቅም መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?
ከኢንፌክሽን የሚመጣ ተፈጥሯዊ በሽታ የመከላከል አቅም መልሶ ከመያዝ የተወሰነ የመከላከል አቅም ሊሰጥ ይችላል ነገር ግን ባልተከተቡ ሰዎች መካከል የመጀመሪያው ኢንፌክሽን የከባድ በሽታ፣ ሆስፒታል የመተኛት፣ ወይም የሞት ስጋትን ይጨምራል። ከ COVID-19 ኢንፌክሽን በኋላ አንዳንዶች አንቲቦዲዎችን ሲያጎለብቱ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ አያጎለብቱም። ከኢንፌክሽን በኋላ በሽታን የመከላከል አቅም ለሚያጎለብቱ፣ ጥበቃው ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነ፣ ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ወይም ከየትኛው ዝርያ እንደሚከላከል መናገር እንኳን ቢሆንአይቻልም።
ምክንያቱም በ COVID-19 መልሶ መያዝን ወይም ከባድ ህመምን ለመከላከል ተፈጥሯዊ በሽታ የመከላከል አቅም ላይ ጥገኛ መሆን አንችልም፣ የ SARS-COV-2 ኢንፌክሽኖችን፣ ከዚህ ጋር የተያያዙ ውስብስብ ሁኔታዎችን፣ እንዲሁም ቀጣይ ስርጭትን ለመከላከል ምርጡ ጥበቃ እና የመጀመሪያው ስልት ክትባቶች ላይ ወቅታዎ መሆን ይሆናል።
የስነ ተዋልዶ ጤና
የ COVID-19 ክትባት ከወሰድኩ ልጅ መውለድ እችላለሁ?
አዎ። ስነ ተዋልዶ እና ክትባት ላይ ያሉዎትን ፍርሀቶች እንረዳዎታለን። እኛ የምናውቀውን ነገር እነሆ፦ ክትባቶች መካንነት ወይም ስንፈተ-ወሲብ እንደሚያስከትሉ ሳይንሳዊ ማስረጃዎች የሉም። ክትባቱ ወደ ሰውነትዎ ሲገባ፣ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ጸረ እንግዳ አካሎችን ለመስራት ከበሽታ የመከላከል ስርአትዎ ጋር ይሰራል። ይህ ሂደት የመራቢያ አካላትዎ ላይ ጣልቃ አይገባም።
የ American College of Obstetricians and Gynecologists (ACOG፣ የአሜሪካ የጽንስ እና የማህፀን ስፔሻሊስቶች ኮሌጅ) ወደፊት ማርገዝ ለሚፈልግ ሰው ወይም በአሁኑ ጊዜ እርጉዝ ለሆነች ወይም ጡት ለምታጠባ ሴት የ COVID-19 ክትባትን ይመክራል። የ COVID-19 ክትባትን የወሰዱ ብዙ ሰዎች ከዚያ በኋላ እርጉዝ ሆነዋል ወይም ጤናማ ሕፃናትን ወልደዋል።
በእርግዝና እና በጡት ማጥባት ወቅት የ COVID-19 ን ከትባት ስለመዉሰድ ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት እባክዎ አንድ ክትባት፣ ሁለት ህይወቶች የሚለው ድህረ ገፅ ላይ ወቅታዊ መረጃ ይመልከቱ።
ነፍሰ ጡር ለሆኑ ሴቶች ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ ነውን?
አዎ፣ ነፍሰ ጡር ሴቶች ክትባቱን መውሰድ ይችላሉ፣ እና የ American College of Obstetricians and Gynecologists (ACOG) (በእንግሊዘኛ ብቻ) ለነፍሰ ጡር ሴቶች ክትባቱን ይመክራል። COVID-19 በእርግዝና፣ በልጅዎ እድገት፣ በወሊድ ወይም የመውለድ አቅም ላይ ማንኛውንም ችግር እንደሚፈጥር ምንም ማስረጃ የለም።
በእርግዝና እና በጡት ማጥባት ወቅት የ COVID-19 ን ከትባት ስለመዉሰድ ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት እባክዎ አንድ ክትባት፣ ሁለት ህይወቶች የሚለው ድህረ ገፅ ላይ ወቅታዊ መረጃ ይመልከቱ።
ጡት ለሚያጠቡ ሰዎች ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?
አዎ፣ ጡት እያጠቡም ከሆነ ክትባቱን መውሰድ ይችላሉ። ክትባት መውሰድ ከፈለጉ ልጅ ማጥባትዎን ማቆም አያስፈልግዎትም። በእውነቱ፣ መጀመሪያ የነበሩ ሪፖርቶች ክትባቱ በእናት ጡት ወተት አማካኝነት ሰውነትዎ ጸረ እንግዳ አካላትን ወደ ልጅዎ ሊያስተላልፍ ይችላል ብለው ይመክራሉ። ተጨማሪ ጥናቶች ያስፈልጋሉ፤ ነገር ግን ይህ ከተረጋገጠ፣ ልጅዎን ከ COVID-19 ለመጠበቅ ይረዳዎታል።
የ COVID-19 ክትባት እናቶችን እና አዲስ የተወለዱ ሕፃናትን እንዴት እንደሚጠብቃቸው (በእንግሊዝኛ ብቻ) የበለጠ ያንብቡ።
ክትባቱ የወር አበባ ዑደቴን ይለውጣል?
አንዳንድ ሰዎች ክትባት ከወሰዱ በኋላ በወር አበባ ዑደቶቻቸው ላይ ለውጦችን ሪፖርት አድርገዋል፣ ግን እነዚህ የረጅም ጊዜ ውጤቶች መሆናቸውን የሚጠቁም ምንም መረጃ የለም። እንደ ውጥረት ባሉ ብዙ የተለያዩ ነገሮች ምክንያት የወር አበባ ዑደቶች ሊለወጡ ይችላሉ።
ግብዓቶች
ክትባቶቹ ውስጥ ምን አይነት ግብዓቶች አሉ?
በኦንላይን ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ውስጥ አንዳንድ ወሬዎችን እና ከእውነት የራቁ የተዘረዘሩ ንጥረ ነገሮችን ሊያዩ ይችላሉ። እነዚህ በአጠቃላይ አፈ ታሪኮች ናቸው። የ COVID-19 ክትባቶች ውስጥ ያሉት ንጥረ ነገሮች (በእንግሊዝኛ ብቻ) ለክትባቶች በጣም አይነተኛ ናቸው። እነሱ የ mRNA ንቁውን ንጥረ ነገር የሚከላከሉ፣ በሰውነት ውስጥ በተሻለ ሁኔታ እንዲሠሩ የሚያግዙ እና በማከማቸት እና በማጓጓዝ ጊዜ ክትባቱን የሚከላከሉ የተቀየረ አድኖቫይረስ ንቁ ንጥረ ነገርን ቅባት፣ ጨዎች እና ስኳሮች ከመሳሰሉ ሌሎች ንጥረ ነገሮች ጋር ይዘዋል።
Novavax የ COVID-19 ክትባት ተጨማሪን፣ ከስቦች እና ስኳር ጋር አብሮ የያዘ የፕሮቲን ንዑስ ላይ የተመሰረተ ክትባት ነው። ይህ ክትባት mRNA አይጠቀምም።
ያሉትን ሙሉ ንጥረ ነገር ዝርዝሮች በ Pfizer (በእንግሊዝኛ ብቻ)፣ Moderna (በእንግሊዝኛ ብቻ) የ Novavax COVID-19 ክትባት እና Johnson & Johnson (በእንግሊዝኛ ብቻ) የመረጃ ወረቀቶች ላይ ይመልከቱ።
የ Johnson & Johnson ክትባት የፅንስ ሕብረ ሕዋስ አለው?
የ Johnson & Johnson የ COVID-19 ክትባት እንደ ሌሎች ብዙ ክትባቶች ተመሳሳይ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተፈጠረ ነው። የፅንስ ወይም የፅንስ ህዋሳትን ክፍሎች አልያዘም። የክትባቱ አንዱ ክፍል ከ 35 ዓመታት በፊት በቀጠሮ ከተደረጉ ውርጃዎች ከተገኙ ሕዋሳት በላብራቶሪ ውስጥ እንዲጎለብቱ ከተደረጉ የህዋሳት ቅጂዎች የተሠራ ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ፣ ለእነዚህ ክትባቶች የሚያስፈልጉት የህዋስ አይነቶች ላብራቶሪ ውስጥ ተጠብቀው ቆይተዋል። ሌሎች ተጨማሪ የጽንስ ህዋሳት ምንጮች እነዚህ ክትባቶችን ለመስራት ጥቅም ላይ አልዋሉም። ይህ ለተወሰኑ ሰዎች አዲስ መረጃ ሊሆን ይችላል። ሆኖም፣ የፈንጣጣ፣ ሩቤላ እና ሄፓታይቲስ ኤ ክትባቶች በተመሳሳይ መንገድ የተዘጋጁ ናቸው።
ክትባቶቹ ማይክሮ ቺፕስ ይዘዋል?
አይ፣ ክትባቶቹ ማይክሮ ቺፕ ወይም የመከታተያ መሣሪያ አልያዙም። ሰውነትዎ COVID-19 ን ለመዋጋት ፀረ እንግዳ አካላት እንዲፈጥር የሚያግዙ ንቁ ንጥረ ነገር እንዲሁም ቅባቶችን፣ ጨዎችን እና ስኳርን ብቻ ይይዛሉ።
የ COVID-19 ክትባት መግነጢሳዊ ያደርገኛል?
አይ፣ የኮቪድ -19 ክትባት ከወሰዱ መግነጢሳዊ አይሆኑም። ክትባቶቹ የኤሌክትሮመግነጢሳዊ መስክን ሊያዘጋጁ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችን የያዙ አይደሉም፣ እና ከብረት ነፃ ናቸው። ያሉትን ሙሉ ንጥረ ነገር ዝርዝሮች በ Pfizer (በእንግሊዝኛ ብቻ)፣ Moderna (በእንግሊዝኛ ብቻ) እና Johnson & Johnson (በእንግሊዝኛ ብቻ) የመረጃ ወረቀቶች ላይ ይመልከቱ ለተጨማሪ መረጃ።
ሌሎች የጤና ስጋቶች
ክትባቱን በመውሰዴ የደም መርጋት ሊከሰትብኝ ይችላል?
የደም መርጋት የማጋጠም እድሉ በጣም ዝቅተኛ ነው። የ Johnson & Johnson ክትባትን ከወሰዱ በኋላ የደም መርጋት ያጋጠማቸው ሰዎች ቁጥር ክትባቱን ወስደው የደም መርጋት ካላጋጠማቸው በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ሰዎች ጋር ሲወዳደር በጣም ዝቅተኛ ነው። ለንፅፅር፣ በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች ከሚጠቀሙት የወሊድ መቆጣጠሪያ ይልቅ የማጋጠም እድሉ ዝቅተኛ ነው። ስለ የወሊድ መቆጣጠሪያ እና ስለ Johnson & Johnson የ COVID-19 ክትባት እና ሌሎችም (በእንግሊዘኛ ብቻ) ለሚኖራችሁ ጥያቄዎች መልሶችን ያግኙ።
ስለ ስጋትዎ ከጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ጋር መነጋገር ይችላሉ። ከ Johnson & Johnson ክትባት በኋላ የደም መርጋት የታየው እድሜያቸው ከ 50 ዓመት በታች በሆኑ አዋቂ ሴቶች ላይ ነው። እርስዎ ሴት ሆነው እድሜዎ ከ 18 ዓመት እስከ 50 ዓመት መሃል ባለው ከሆነ፣ ለደም መርጋት ለመጋለጥ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዳሉ እባክዎ ልብ ይበሉ፣ ይህም ወደ ሞት ሊመራ ይችላል። የደም መርጋት አሳሳቢነት ከ Johnson & Johnson የ COVID-19 ክትባት ጋር እንጂ፣ ከ Pfizer ወይም Moderna ክትባቶች ጋር አይገናኝም። የ Johnson & Johnson ክትባትን መውሰድ የሚያሳስብዎት ከሆነ በምትኩ የ Moderna ወይም Pfizer ክትባቶች አቅራቢዎን ይጠይቁ።
ስለ ማዮካርዳይቲስ ወይም ፔሪካርዳይቲስ መጨነቅ አለብኝ?
ከ COVID-19 ክትባት በኋላ የማዮካርዳይቲስ (የልብ ጡንቻ እብጠት) እና የ ፔሪካርዳይቲስ (የልብ ሽፋን እብጠት) ታካሚዎች በጣም ጥቂት ናቸው። ከክትባት በኋላ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ሊያጋጥማቸው ይችላሉ። ለሚያጋጥማቸው ሰዎች፣ አብዛኛዎቹ ታካሚዎች በአሥራዎቹ ዕድሜ እና በወጣት ጎልማሶች ውስጥ ናቸው፣ ምልክቶች በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች መለስተኛ ናቸው፣ እና ሰዎች በተለምዶ በራሳቸው ወይም በአነስተኛ ህክምና ይድናሉ። በ COVID-19 ከታመሙ ማዮካርዳይቲስ እና ፔሪካርዳይቲስ በጣም የተለመዱ ናቸው።
ከጁላይ 30፣ 2021 ጀምሮ፣ ለ Vaccine Adverse Event Reporting System (VAERS፣ የክትባት አሉታዊ ክስተት ሪፖርት ማድረጊያ ስርዓት) ከ 1500 ባነሱ ሪፖርቶች ውስጥ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ 699 ኬዞች ብቻ ተረጋግጠዋል (በእንግሊዘኛ ብቻ)፣ ከ 177 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ቢያንስ አንድ የ የኮቪድ -19 ክትባት ዶዝ ወስደዋል።
ስለ አደጋዎ ከሐኪምዎ ጋር መነጋገር ይችላሉ። ከክትባት በኋላ ምንም ዓይነት ምልክቶች ካልዎት ለ VAERS (በእንግሊዘኛ ብቻ) ማሳወቅ ይችላሉ (እንግሊዝኛ ብቻ)።
ስለ ከ COVID-19 ክትባት በኋላ ስለሚመጡት ማዮካርዳይቲስ እና ፔሪካርዳይቲስ (በእንግሊዘኛ ብቻ) የበለጠ ይወቁ።
ሥር የሰደደ የጤና ችግር ካለብኝ ክትባቱን መውሰድ እችላለሁ?
ስር የሰደደ የጤና ወይም የህክምና ሁኔታ ያላቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች የ COVID-19 ክትባቶችን ሊያገኙ ይችላሉ። ስለ ሁሉም አለርጂዎችዎ እና የጤና ሁኔታዎ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያሳውቁ። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ብዙ ስር የሰደዱ ሁኔታዎች ለ COVID-19 በሽታ የመጋለጥ እድልዎን ከፍ ያደርጉታል፣ ስለዚህ እንዳይታመሙ ክትባቱ የበለጠ አስፈላጊ ነው።
እነዚህ የተወሰኑ የሰዎች ቡድኖች የ COVID-19 ክትባት ሊወስዱ ይችላሉ፦
- በኤች አይ ቪ የተያዙ ሰዎች እና በሽታ የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች።
- ርስን በሚያጠቃ ህመም የተጠቁ ሰዎች።
- ቀደም ሲል Guillain-Barré syndrome (GBS፣ የጊሊያን-ባሬ ሲንድረም ወይም የአንድ ሰው በሽታ የመከላከያ የራሱን ነርቭ ሲጎዳ የጊሊያን-ባሬ ሲንድረም ይባላል) ያጋጠማቸው ሰዎች።
- ቀደም ሲል የቤል ፓልሲ የነበረባቸው ሰዎች።
የከባድ የአለርጂ ምላሾች ታሪክ ካልዎት ወይም ለክትባት ንጥረ ነገር ከባድ የአለርጂ ምላሽ ሊኖርዎት ይችላል ብለው ካሰቡ፣ የ COVID-19 ክትባቶች አለርጂ ላለባቸው ሰዎች (በእንግሊዘኛ ብቻ) የሚለውን ያንብቡ። ከ COVID -19 ክትባት በኋላ ያለ አናፊላክሲስ (በእንግሊዘኛ ብቻ) አልፎ አልፎ የሚታይ ሲሆን በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በአንድ ሚሊዮን ክትባት ውስጥ በግምት ከ 2 እስከ 5 ሰዎች ውስጥ ተከስቷል።
ይህ መረጃ (በእንግሊዘኛ ብቻ) ከላይ በተጠቀሱት ቡድኖች ውስጥ ያሉ ሰዎች የ COVID-19 ክትባት ስለመቀበል በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ እንዲያደርጉ ለመርዳት ያለመ ነው።
ክትባቶቹ የእኔን DNA ይለውጡ ይሆን?
አይ፣ የ COVID-19 ክትባቶች DNA ዎን አይለውጡም ወይም አይቀይሩትም። ክትባቶቹ COVID-19 ን ከሚያስከትለው ቫይረስ የመከላከል ጥበቃን ለመጀመር ለህዋሶቻችን መመሪያዎችን ይሰጣሉ። ክትባቱ የእኛ DNA የሚቀመጥበት የህዋስ ክፍል ውስጥ አይገባም። ይልቁንም፣ ክትባቶቹ የበሽታ መከላከል አቅምን ለመገንባት ከሰውነታችን ተፈጥሯዊ መከላከያዎች ጋር ይሰራሉ። ስለ COVID-19 ክትባቶች mRNA (በእንግሊዘኛ ብቻ) እና viral vector (በእንግሊዘኛ ብቻ) የበለጠ ይወቁ።
ክትባቱ የረጅም ጊዜ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ያስከትላል?
ለ COVID-19 እና ለሌሎች በሽታዎች ክትባቶች ብዙ ሳይንሳዊ መረጃዎች አሉን። በእነዚያ መረጃዎች ላይ በመመርኮዝ፣ እነዚህ ክትባቶች በጣም ደህና እንደሆኑ ባለሙያዎች እርግጠኞች ናቸው። ለ COVID-19 ሁሉም ግብረመልሶች እንደ ድካም ወይም እንደ የቆሰለ ክንድ ያሉ ቀለል ያሉ እና ለሁለት ቀናት ብቻ የሚቆዩ ናቸው ማለት ይቻላል። ከባድ ወይም የረጅም ጊዜ ግብረ መልሶች እጅግ በጣም አናሳ ናቸው።
ማንኛውም የረጅም ጊዜ የጎንዮሽ ጉዳቶች ብዙውን ጊዜ ክትባት ከተወሰዱ በስምንት ሳምንታት ውስጥ ይከሰታሉ። ለዚህ ነው የክትባቱ አምራቾች ለአሜሪካ የአስቸኳይ ጊዜ አጠቃቀም ፈቃድ ለማግኘት ለ U.S. Food and Drug Administration (FDA፣ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር) ከማመልከታቸው በፊት ክሊኒካዊ ሙከራዎች ከተደረጉ ቢያንስ ስምንት ሳምንታት መጠበቅ ያለባቸው። ባለሙያዎች ለደህንነት ስጋቶች የ COVID -19 ክትባቶችን መከታተላቸውን ቀጥለዋል። FDA ስለ ማንኛውም ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶች ወይም ምላሾች ሪፖርቶችን ይመረምራል።