የ COVID-19 ክትባት በብዙ የንግድ ስራዎች፣ ኩነቶች እና አሰሪዎች ይጠየቃል። የሚከተሉት አይነት ማረጋገጫዎች በ Washington ተቀባይነት አላቸው። የተወሰኑ ቦታዎች ከታች ከተዘረዘሩት አንድ የተለየ አይነት ብቻ ሊቀበሉ ይችላሉ።
የ CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከላት) የ COVID-19 የክትባት መረጃ ካርድ
በተንቀሳቃሽ መሣሪያ ላይ ያሉ ኦሪጅናሎች፣ ቅጂዎች ወይም ፎቶግራፎች ተቀባይነት አላቸው።

የ COVID-19 ክትባት ምስክር ወረቀት ወይም QR ኮዶች

ናሙና C፦
ድጋፍ ባለው አጋር የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ላይ የሚታይ QR ኮድ። (መተግበሪያዎቹ ሊለያዩ ይችላሉ)
የ WA ግዛት የክትባት መረጃ ስርዓት እትም
- በ Washington State Immunization Information System የታተሙ የ Certificate of Immunization Status (CIS፣ የክትባት ሁኔታ ምስክር ወረቀት) ቅጾች።
- በሕክምና አገልግሎት አቅራቢ ካልተፈረመ በስተቀር በእጅ የተጻፉ መግቢያዎች ትክክለኛ እንደሆኑ አይቆጠሩም።

ሌላ ምን እንደ ይፋዊ የ COVID-19 ክትባት መረጃ ይቆጠራል?
- ከሕክምና አገልግሎት አቅራቢ የተረጋገጠ የኤሌክትሮኒክ የሕክምና መረጃ እትም