ምርመራ በትምህርት ቤቶች ውስጥ

ለምን ምርመራ?

ክትባት፣ የአፍ መሸፈኛ እና የማህበራዊ ርቀት ከመሳሰሉ ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎች ጋር፣ ምርመራ የ COVID-19 ስርጭትን የሚገድብ ጠቃሚ እና የተረጋገጠ መሳሪያ ነው።

አጋርነቶች ትምህርት ቤቶች ላይ ያሉ ጫናዎችን ያነሳሉ

የ Washington State Department of Health (የዋሺንግተን ግዛት ጤና መምሪያ) በ Learn to Return program (ለመመለስ ይማሩ ፕሮግራም) አማካኝነት ደህንነቱ የተጠበቀ የአካላዊ ትምህርት ከባቢን ለመፍጠር እንዲረዳ ከአጋሮች ጋር እየሰራ ነው። Learn to Return (እንግሊዘኛ ብቻ) ትምህርት ቤቶች በቦታው ላሉ ተማሪዎች ቀላል የ COVID-19 ምርመራ እንዲያቀርቡ ይረዳል።

DOH Learn to Return ን ከ 300 ለሚበልጡ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች፣ በግዛቱ ያሉ የግል፣ የማዕቀፍ፣ እና የብሄር የምትህርት ቤት ዲስትሪክቶችን ጨምሮ፣ ለማምጣት ከ Washington Office of the Superintendent of Public Instruction (OSPI፣ የህዝብ መመሪያ ተቆጣጣሪ የዋሺንግተን ቢሮ) እና ለትርፍ ካልተቋቋመው Health Commons Project ጋር በአጋርነት እየሰራ ነው።

ለትምህርት ቤቶች

Learn to Return:

የበለጠ ለማወቅ፣ የትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች እና ሰራተኞች የ Learn to Return የትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች እና ሰራተኞች ገጽ (በእንግሊዘኛ ብቻ) መጎብኘት ይችላሉ።

ምዝገባ የጀመረ የምትህርት ቤት ዲስትሪክትዎን ያግኙ (በእንግሊዘኛ ብቻ)

በሁሉም የ Learn to Return ፕሮግራም ደረጃዎች ላይ ያለ ተደራሽነት በምርመራ የምትህርት ቤቱን ስኬት ለማረጋገጥ ቁልፍ ነው። ተሳትፎን ለማበረታታት፣ የፌደራል Public Readiness and Emergency Preparedness Act (PREP፣ የህዝብ ዝግጅት እና የድንገተኛ ሁኔታ ዝግጁነት አዋጅ - በእንግሊዘኛ ብቻ) የጤና እንክብካቤ ፍቃዶች ከመሳሰሉ የቁጥጥር እክሎች ውጪ ምርመራ እንዲያካሂዱ ለትምህርት ቤቶች ስልጣን ሰጥቷል። በተጨማሪም፣ የ PREP አዋጅ በሰፊ የመከላከል አቅም ጥበቃዎች አማካኝነት ከክስ እና ተጠያቂነት ከህጋዊ ጥርጣሬ እና አደጋ ትምህርት ቤቶችን ይጠብቃል።

ለወላጆች/አሳዳጊዎች እና ተማሪዎች

Learn to Return፡

  • ለቤተሰቦች ያለ ምንም ክፍያ ተዘጋጅቷል
  • በበጎ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው
  • ልጅዎን በትምህርት ቤት ውስጥ ለመጠበቅ ይረዳል
  • ትምህርት ቤቶችን በአካል ለሚሰጥ ትምህርት ክፍት እንዲሆኑ ያደርጋል
  • በስፖርት እና ከስርዓተ ትምህርቱ ተጨማሪ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳትፎ እንዲቀጥል ያስችላል
  • የልጅዎን ማንነት ግላዊ አድርጎ ይይዛል
  • የልጅዎን ምቾት ታሳቢ በማድረግ ቀላል፣ ጥልቅ ያልሆነ የአፍንጫ ናሙና ምርመራዎችን ይጠቀማል

የበለጠ ለማወቅ፣ ወላጆች እና ተማሪዎች የ Learn to Return የወላጆች እና ተማሪዎች ገጽ (በእንግሊዘኛ ብቻ) ን ይጎብኙ።