ይዘቱ ለመጨረሻ ጊዜ የተዘመነው ኤፕሪል 19፣ 2023 ነበር።

እድሜያቸው 6 ወር እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች የ COVID-19 ክትባት ይገኛል።
አብሮ የተገነባውን ማጣሪያ በመጠቀም ለልጆች ክትባት የሚሰጡ ክሊኒኮችን ለማሳየት፣ ቀጠሮ ለማግኘት እና ለማስቀጠር Vaccine Locator (ክትባት ፈልጎ ማግኛ) ይጎብኙ።
ቤት ውስጥ ይቆያሉና የ COVID-19 ክትባት ያስፈልጎታል? እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው ቤት ውስጥ የሚቆይ ከሆነ እንድናውቅ ደህንነቱ የተጠበቀ ኦንላይን ቅጽ ይሙሉ። ምላሾችዎ ግለሰቦችን ከካውንቲ እና/ወይም የግዛት ሞባይል ክትባት ቡድኖች ጋር እንድናገናኝ ያስችለናል
እርዳታ ይፈልጋሉ? ወደ 1-833-VAX-HELP (833-829-4357) ይደውሉ፣ ከዛ # ይጫኑ። የቋንቋ እርዳታ አለ። አቅራቢያዎ ያሉ የክትባት ቦታዎችን ለማግኘት ዚፕ ኮድዎን ለ 438-829 (GET VAX) ወይም ለ 822-862 (VACUNA) ይላኩ።
የክትባት ደህንነት እና ውጤታማነት
ልጅዎን ከ COVID-19 ማስከተብ የሚከተሉትን ያደርጋል፡-
- በ COVID-19 የመያዝ የስጋትቸውን ለመቀነስ ይረዳል
- በ COVID-19 ከተጠቁ እንኳን፣ በጠና የመታመም እድላቸውን ይቀንሳል
- ከ COVID-19 የተነሳ የመሞት ስጋታቸውን ለመቀነስ እና ሆስፒታል የመተኛት እድላቸውን ይቀንሳል
- በ COVID-19 ተለዋጭ እንዳይጠቁ በመከላከል ይረዳቸዋል
- በ COVID-19 ከመያዝ የተጠበቁ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ቁጥር ይጨምራል — በሽታውን ለመሰራጨት ከባድ ያደርገዋል
- COVID-19 በማህበረሰብ ውስጥ የሚኖረውን ስርጭትን ለመግታት በአካል በመማር እና በእንቅስቃሴ ላይ ያሉ መስተጓጎሎችን ይቀንሳል

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች ለወላጆች እና አሳዳጊዎች
- ልጄ COVID-19 እንዳይይዘው ለምን እሰጋለሁ?
-
ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ በአሜሪካ ውስጥ ከ 15 ሚሊዮን በላይ ህጻናት በ COVID-19 ተይዘዋል። አዳዲሶቹ የ COVID-19 ዝርያዎች ከመጀመሪያው እና ብዙ ሰዎችን ለሆስፒታል ከዳረገው የ COVID-19 ቫይረስ የበለጠ ለወጣቶች በጣም አደገኛ እና በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጩ ናቸው።
COVID-19 ብዙውን ጊዜ በልጆች ላይ ከአዋቂዎች የበለጠ ቀላል ቢሆንም፣ ህጻናት በጣም ሊታመሙ እና የበሽታ መከላከል አቅማቸው ደካማ ለሆነ ወይም ተጋላጭ ለሆኑ ጓደኞቻቸው እና ቤተሰባቸው በሌሎች መንገዶች ሊያስተላልፉት ይችላሉ።
በ COVID-19 የተጠቁ ህፃናት “ረዥም COVID-19” ወይም የማያቋርጥ ምልክቶች ሊያዳብሩ ይችላሉ ይህም ብዙውን ጊዜ የአእምሮ ብዥታ፣ ድካም፣ ራስ ምታት፣ ማዞር እና የትንፋሽ ማጠርን ያጠቃልላሉ። ክትባት የልጆችን ጤንነት እና ደህንነት ለመጠበቅ ምርጡ መንገድ ነው።
በ COVID-19 የተጠቁ ህፃናት ለ Multisystem Inflammatory Syndrome (MIS-C) (ድረ ገጹ በእንግሊዘኛ ብቻ) የበለጠ ስጋት ላይ ሊሆኑ ይችላሉ። MIS-C ልብን፣ ሳንባን፣ ኩላሊትን፣ አእምሮን፣ ቆዳን፣ አይንን ወይም የጨጓራና አንጀት አካላትን ጨምሮ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በማቃጠል ህመም ሊሰማ የሚችልበት ሁኔታ ነው። የ MIS-C መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን ባይታወቅም፣ MIS-C ያለባቸው ብዙ ህፃናት COVID-19 ነበረባቸው፣ ወይም በ COVID-19 ከተጠቃ ሰው ጋር ግንኙነት ነበራቸው። MIS-C ከባድ፣ እንዲሁም ለሞት የሚዳርግ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በዚህ በሽታ የተያዙ አብዛኛዎቹ ህጻናት በህክምና አገልግሎት የተሻሉ ሆነዋል።
- ክትባቶቹ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ለልጆች ውጤታማ መሆናቸውን እንዴት እናውቃለን?
-
የ COVID-19 ክትባቶች ደሕንነታቸዉ የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ Centers for Disease Control & Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል) የሀገሪቱን የክትባት ደሕንነት የመቆጣጠር አቅምን አስፋፍቷል፣ አጠናክሯል። በዚህ ምክንያት፣ የክትባት ደሕንነት ባለሙያዎች የ COVID-19 ክሊኒካል ሙከራ ግዜ ላይ ላይታዩ የሚችሉ ጉዳዮችን ሊቆጣጠር እና ሊያዉቁ ይችላሉ።
Emergency Use Authorization (EUA፣ የአደጋ ጊዜ አጠቃቀም ፍቃድ) ምንድን ነው?
EUA የ Food and Drug Administration (FDA፣ የምግብ እና መድሃኒት አስተዳደር) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ለአንድ ምርት ሙሉ ፍቃድ ከመሰጠቱ በፊት የሚገኝ እንዲሆን ያስችለዋል። የአደጋ ጊዜ አጠቃቀም ፍቃድ አላማ ሰዎች ከረጅም ጊዜ የውሂብ ትንተና በፊት የህይወት አድን ክትባቶችን ማግኘት እንደሚችሉ ማረጋገጥ ነው። ሆኖም EUA ክሊኒካዊ መረጃን በጥልቀት መመርመርን ይጠይቃል—ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ።በ Food & Drug Administration (FDA፣ የምግብ እና መድሐኒት አስተዳደር) የተሰጠ ማንኛውም EUA በ Centers for Disease Control and Prevention (የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከያ ማዕከላት) Advisory Committee on Immunization Practices (በክትባት ተግባራት ላይ አማካሪ ኮሚቴ) ተጨማሪ ምርመራ ይደረግበታል።
- አንድ ክትባት የ FDA ፈቃድ አለው ሲባል ምን ማለት ነው?
-
Department of Health (የጤና መምሪያ) ሳይሆን የ Washington State Board of Health (የዋሽንግተን ግዛት የጤና ቦርድ) ከ K-12 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ላሉ ልጆች የክትባት መስፈርቶችን የማውጣት ስልጣን አለው Revised Code of Washington (RCW፣ የተሻሻለው የዋሽግተን ኮድ) 28A.210.140 ። በአሁኑ ሰዓት ለትምህርት ቤት ወይም ለህጻናት እንክብካቤ የ COVID-19 የክትባት መስፈርት አልተቀመጠም።
- ለክትባቱ መክፈል ይጠበቅብኛል?
-
አይ። ልጅዎ ለእርስዎ ምንም ወጪ ሳይሆን ክትባቱን ያገኛል። የፌዴራሉ መንግሥት የክትባቱን ሙሉ ወጪ ይከፍላል።
የሕዝብ ወይም የግል የጤና ኢንሹራንስ ካልዎት፣ የክትባት አቅራቢዎ ለክትባት አስተዳደር ክፍያ ክፍያውን ሊከፍላቸው ይችላል። ዋስትና ከሌልዎት፣ የፌደራል መንግስቱ አቅራቢዎ ክትባትዎን እንዲያስተዳድር የሚከፍል ፕሮግራም አቅርቧል።
ከኪስዎ ወጪ ወይም ለ COVID-19 ክትባትዎ የአስተዳደር ክፍያ ከአቅራቢዎ ክፍያ መቀበል የለባችሁም። ይህ የግል መድህን፣ Apple Health (Medicaid)፣ Medicare ያላቸው ሰዎች ወይም የጤና መድን ሽፋን የሌላቸውም ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል።
- የ COVID-19 ክትባት የተለመዱ የጎንዮሽ ጉዳቶች በህፃናት ላይ ምንድን ናቸው?
-
ህጻናት በ COVID-19 ከተያዙ የሚኖሩት የጤና ስጋቶች ከክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳቶች ጋር ሲነፃጸር የበለጠ ከፍ ያለ ነው።
ልክ እንደ ሌሎች ክትባቶች፣ በጣም የተለመዱት የጎንዮሽ ጉዳቶች የእጅ ህመም፣ ድካም፣ ራስ ምታት እና የጡንቻ ህመም ናቸው። እነዚህ ምልክቶች ብዙውን ጊዜ ቀላል ናቸው።
በክሊኒካዊ ሙከራዎች ላይ (እንግሊዝኛ ብቻ) ብዙ ህፃናት ከመጀመሪያው መጠን ይልቅ ከሁለተኛው መጠን በኋላ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሪፖርት አድርገዋል። የጎንዮሽ ጉዳቶች በአጠቃላይ በክብደት ደረጃ ቀላል እና መካከለኛ ሲሆኑ ከክትባት በኋላ ባሉት ሁለት ቀናት ውስጥ ተከስተዋል፣ እንዲሁም አብዛኛዎቹ ከአንድ እስከ ሁለት ባሉት ቀናት ውስጥ ጠፍተዋል።
- በ mRNA ክትባት ውስጥ ምን ዓይነት ንጥረ ነገሮች አሉ?
-
በ mRNAr ክትባት ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮች ለክትባት የተለመዱ ናቸው። ክትባቱ የ mRNA ንጥረ ነገሮችን እንደ ስብ፣ ጨው እና ስኳር ካሉ ሌሎች ንጥረ ነገሮች ጋር በመሆን ንቁውን ንጥረ ነገር የሚከላከሉ፣ በሰውነት ውስጥ በተሻለ ሁኔታ እንዲሰሩ እና በማከማቻ እና በማጓጓዝ ወቅት ክትባቱን የሚከላከሉ ናቸው።
የ mRNA ክትባት የሰው ስነ ህዋሳትን (የፅንስ ስነ ህዋሳትን ጨምሮ)፣ የ COVID-19 ቫይረስን፣ ላቲክስን፣ መጠበቅያዎችን፣ ወይም የአሳማ ምርቶችን ወይም ጄልቲንን ጨምሮ ማንኛውንም የእንስሳት ተረፈ ምርቶችን አያካትትም። ክትባቶቹ በእንቁላል ውስጥ አያድጉም እና ምንም አይነት የእንቁላል ውጤቶችን አይዙም።
ስለ ንጥረ ነገሮቹ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህንን ጥያቄ እና መልስ፤ ከ Children's Hospital of Philadelphia (የፊላዴልፊያ ህፃናት ሆስፒታል) ድረ ገፅ (በእንግሊዝኛ ብቻ) ይመልከቱ።
- ልጄ የትኛውን የክትባት ምርት ሊወስድ ይችላል?
-
በዚህ ጊዜ፣ የ Pfizer-BioNTech (Pfizer) ክትባት እና የ Moderna የ COVID-19 ክትባት ስሪቶች እድሜያቸው 6 ወር እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ህጻናት ተፈቅዷል። በ Emergency Use Authorization (EUA፣ የድንገተኛ አጠቃቀም ፍቃድ) ስር ዕድሜያቸው ከ 12 ዓመት በላይ ለሆኑ የ Novavax ክትባት አለ።
- ልጄ ከኦርጂናል ተከታታዩ በኋላ የዘመነ ዶዝ ያስፈልገዋል?
-
የ2-ዶዝ ወይም የ3-ዶዝ ሞኖቫለንት የመጀመሪያ ተከታታዮችን ያጠናቀቀ ዕድሜው 6 ወራት እና ከዚያ በላይ የሆነ እያንዳንዱ ሰው የዘመነ ባይቫለንት ዶዝ መውሰድ አለበት።
- ልጄ ምን ያህል መጠኖች (ዶዝ) ያስፈልጉታል?
-
- ዕድሜያቸው ከ 6 ወራት- 4 አመት የሆኑ ልጆች 3 ዶዝ ባይቫለንት የ Pfizer ተከታታዮችን ወይም 2 ዶዝ ባይቫለንት የ Moderna ተከታታዮችን ይወስዳሉ
- ዕድሜያቸው 5 አመት የሆኑ ልጆች ነጠላ ዶዝ ለባይቫለንት Pfizer ክትባት ወይም የ 2 ዶዝ ባይቫለንት Moderna ተከታታዮች ይወስዳሉ
- ዕድሜያቸው 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ልጆች ነጠላ የባይቫለንት ክትባት ይወስዳሉ
ዕድሜያቸው 6 ወራት እና ከዚያ በላይ የሆኑ በመጠኑ ወይም በከፍተኛ ደረጃ የመከላከል አቅማቸው ያነሰ ልጆች ለመጨረሻ ጊዜ ከወሰዱት የዘመነ ዶዝ ቢያንስ ከ2 ወራት በኋላ ተጨማሪ የባይቫለንት ዶዝ ሊያገኙ ይችላሉ። የመከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ ስለሆኑ ሰዎች ለማወቅ እባክዎ የ Centers for Disease Control and Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል) መመሪያዎችን (እንግሊዘኛ ብቻ) ይመልከቱ።
- ስለ ክትባቱ ጥያቄዎች ካሉኝ ማንን ማነጋገር አለብኝ?
-
ከልጅዎ የህጻናት ስፔሻሊስት ወይም ሌላ ታማኝ የሕክምና አገልግሎት አቅራቢ ጋር ይነጋገሩ፣ ከማህበረሰብ ጤና ሰራተኛ ጋር ይነጋገሩ ወይም መረጃ www.CovidVaccineWA.org ላይ ያንብቡ።
- ልጄን ለማስከተብ የት ልወስደው እችላለሁ?
-
የዋሽንግተን ግዛት ሁሉንም የሚመከሩ ክትባቶችን ያለ ምንም ወጪ ከ 18 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት ይሰጣል። የልጅዎን የሕፃናት ሐኪም ወይም መደበኛ ክሊኒክ የ COVID-19 ክትባት እንዳላቸው ይጠይቁ።
የጤና እንክብካቤ አቅራቢ የሌላቸው ቤተሰቦች፣ የጤና እንክብካቤ አቅራቢ፣ ክሊኒክ ወይም ሌሎች የጤና መርጃዎች ለማግኘት ወደ Help Me Grow WA ነጻ መስመር በስልክ ቁጥር 1-800-322-2588 መደወል ወይም ParentHelp123.org የሚለውን ድረ ገጽ (በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽ ቋንቋዎች ብቻ) መጎብኘት ይችላሉ። ይህ አገልግሎት ነፃ ነው እንዲሁም የቋንቋ እርዳታ አለ።
ከዚህም በተጨማሪ፣ VaccineLocator.doh.wa.gov የሚለውን ድረ ገጽ መጎብኘት እና ማጣሪያውን/ፊልተር ተጠቅመው ለእርስዎ ቅርብ የሆኑ እና የህጻናት ክትባቱ ያላቸውን ቦታዎች ዝርዝር ማየት ይችላሉ።
- ልጄ እንደ ጉንፋን ያሉ ሌሎች ክትባቶችን በሚወስድበት ጊዜ የ COVID-19 ክትባትን መውሰድ ይችላል?
-
አዎ። ልጅዎ ሌሎች ክትባቶችን በሚወስዱበት ተመሳሳይ ጊዜ የ COVID-19 ክትባትን መውሰድ ይችላል።
ለልጅዎ አስፈላጊ የትምህርት ቤት ክትባቶችን (እንግሊዝኛ ብቻ) ወይም ለሌሎች የሚመከሩ ክትባቶች ከ COVID-19 ክትባት የተለየ መርሃ-ግብር ማውጣት አያስፈልግዎትም። የ COVID-19 ክትባት ቀጠሮ ልጅዎ በሌሎች የሚያሰፈልጉት ክትባቶች ሁሉ እንዲከተብ ማድረግያ ሌላው አጋጣሚ ነው።
- ልጄ በህጻን እንክብካቤ ወይም የቀን ማቆያዎች ውስጥ እንዲገባ የ COVID-19 ክትባት ያስፈልገዋል?
-
የ Washington State Board of Health (በእንግሊዝኛ ብቻ) ለትምህርት ቤቶች እና ለህፃናት እንክብካቤ የትኞቹ ክትባቶች እንደሚያስፈልጉ ይወስናል። በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት የ COVID-19 ክትባት መስፈርትን የሚጠይቅ ትምህርት ቤት ወይም የህጻናት እንክብካቤ የለም።
ለቀን ማቆያዎች፣ መስፈርቶቻቸው ምን እንደሆኑ ለማወቅ ማቆያውን የሚመራው ድርጅት ጋር ያረጋግጡ።