የ COVID-19 ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት

የ COVID-19 ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ካልዎት፣ የራስዎን እና የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ መውስድ የሚችሉት እርምጃዎች መኖራቸው መልካሙ ዜና ነው።

ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ካልዎት ምን ያደርጋሉ

ቤትዎ ውስጥ ሆነው ከሌሎች ሰዎች ርቀው ይቆዩ ከ Centers for Disease Control and Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል) እና Washington State Department of Health (DOH፣ የጤና መምሪያ) የሚሰጠውን አዲሱን የለይቶ ማቆያ መመሪያ (በእንግሊዘኛ ብቻ የሚገኝ ድረገጽ) ይከተሉ። ተለይተው በሚቆዩበት ጊዜ ድጋፍ የሚያስፈልግዎ ከህነ፣ ከ Care Connect Washington (በእንግሊዘኛ) እርዳታ ሊያገኙ ይችላሉ።

  • በቤትዎ ውስጥ ራስዎን ከሌሎች ይለዩ። የሚችሉ ከሆነ፣ አብረዎት ከሚኖሩት ሰዎች ርቀው በተለየ ክፍል ይቆዩ እንዲሁም የተለየ መጸዳጃ ቤት ይጠቀሙ።

ምልክትዎን ይከታተሉ። ምልክቶችዎ እየባሱ የሚሄዱ ከሆነ፣ ወይም እያስጨነቅዎ ያለ አዳዲስ ምልክቶች ካልዎት፣ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያነጋግሩ። የሚከተሉትን የ COVID-19 ድንገተኛ የጥንቃቄ ምልክቶች ካስተዋሉ ለ 9–1–1 ይደውሉ፦

  • የመተንፈስ ችግር
  • ቋሚ የደረት ህመም ወይም ግፊት
  • በድንገት መደናገር
  • መልስ መስጠት አለመቻል
  • በቆዳ ቀለም ላይ በመመርኮዝ ፈዛዛ፣ ግራጫ ወይም ሰማያዊ ቀለም ያለው ቆዳ፣ ከንፈር ወይም የጥፍር

በቤትዎ ውስጥም ቢሆን ከሌሎች ጋር መሆን ካስፈለግዎ አፍንጫዎን እና አፍዎን የሚሸፍን ማስክ ያድርጉ። ቤቱ ውስጥ ያሉ ሌሎች ሰዎችም ማስኮችን ማድረግ አለባቸው።

ስርጭቱን ለመግታት ሌሎችን ያሳውቁ። የእርስዎን የቅርብ ንክኪዎች (በእንግሊዘኛ) ያግኙ እንዲሁም ለ COVID-19 ተጋልጠው ሊሆን እንደሚችል ያሳውቋቸው። የታመመ ሰው ምልክቶች ከማሳየቱ በፊትም COVID-19 ን ሊያስተላልፍ ይችላል። የቅርብ ንክኪዎችዎን በሚያሳውቁበት ጊዜ፣ መመርመር እንዲሁም ቫይረሱ ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳይሰራጭ ለማድረግ አስፈላጊ ከሆነ ካራንታይን ወይም ተለይቶ መቆየት ይችላሉ።

  • የቤት ውስጥ ምርመራን ከተጠቀሙ፣ ፖዘቲቭ ውጤትዎን ለ Washington የ COVID-19 ነጻ መስመር በ 1–800–525–0127 ሪፖርት ያድርጉ። ይህ የንክኪ ፍለጋ ጥረቶች ን (በእንግሊዘኛ) ይደግፋል እንዲሁም በሽታው በማህበረሰባችን ውስጥ ተጨማሪ እናድይሰራጭ ይከላከላል። የስልክ መስመሩ ሰኞ ከ 6 a.m. እስከ 10 p.m.፣ እና ከማክሰኞ እስከ እሁድ ደና የሚከበሩ በዓላት) ከ 6 a.m. እስከ 6 p.m. ክፍት ነው። የቋንቋ ድጋፍ ይገኛል።
  • የቤት ውስጥ ምርመራ ከተጠቀሙ፣ተጋልጠው ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች የ WA Notify (በእንግሊዘኛ) ተጠቃሚዎችን በምስጢር ለማሳወቅ በ WA Notify (የዋሺንግተን ማሳወቂያ) በኩል የማረጋገጫ ኮድ ይጠይቁ ።

የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያነጋግሩ — አቅራቢ ካልዎት — ወይም ለህክምና ምክር የአካባቢዎን የጤና ክሊኒክ ያነጋግሩ። በሚያገግሙበት ጊዜ እንዴት በምቾት እንደሚቆዩ የተወሰኑ ምክሮችን ሊሰጡዎት ይችላሉ። በጥንቃቄ መከታተል ስላለብዎት የከባድ ህመም ምልክቶች ይነግሩዎታል፤ ስለዚህ የሚያስፈልግዎ ከሆነ ተጨማሪ እንክብካቤ ማግኘት ይችላሉ።

በሚችሉት መጠን በቦታዎ አየር እንዲገባ ያድርጉ። የሚቻል ከሆነ፣ መስኮቶችን ይክፈቱ፤ ማራገቢያዎን ከፍ አድርገው ያስጀምሩት፤ የ HVAC ማጣሪያዎን ይለውጡ፤ ወይም የ HEPA አየር ማጣሪያ ይጠቀሙ።

ከ COVID-19 ቢያገግሙ እና የተለይቶ መቆያ ጊዜዎን ማጠናቀቅ ቢችሉም እንኳን፣ ራስዎን እና ሌሎችን መጠበቅ መቀጠልዎ አስፈላጊ ነው። የእርስዎን የ COVID-19 ክትባት  ይውሰዱ እና ማጠናከሪያ  በመውሰድ፣ ህዝብ በሚሰበሰብበት ቦታ ማስክ በማድረግ፣ ትልልቅ መሰባሰቦችን በመተው፣ እጆችዎን በመታጠብ እና በስማርት ስልክዎ ላይ WA Notify (በእንግሊዘኛ)  ን በማንቃት ይህንን ማድረግ ይችላሉ።