እራስዎን እና ማህበረሰብዎን ለመጠበቅ በ WA Notify አማካኝነት የ COVID-19 ተጋላጭነት ማስታወቂያዎችን ስለተጠቀሙ እናመሰግናለን። የተጋላጭነት ማስታወቂያዎች በ COVID-19 ወረርሽኝ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ ጉዳዮችን የተከላከሉ ሲሆን ሰዎች የ COVID-19 ስርጭትን ለመከላከል እርምጃ እንዲወስዱ አስችሏቸዋል።
በ ዋሽንግተን ግዛት ውስጥ ብቻ፣ ከ 235,000 በላይ ሰዎች ለ COVID-19 ሊጋለጡ የሚችሉትን ሌሎች ሰዎችን ስም ሳይጠቀስ ለማስጠንቀቅ፣ ከ 2.5 ሚሊዮን በላይ የተጋላጭነት ማስታወቂያዎችን በመስጠት፣ WA Notify ተጠቅመዋል።
የህዝብ ጤና ድንገተኛ ሁኔታ ሲያበቃ፣ ከፍተኛ የሆኑ የክትባት ደረጃዎች፣ የተስፋፋው የህዝብ መከላከያ፣ እና የቀረቡ ህክምናዎች ከባድ የ COVID-19 በሽታ፣ ሆስፒታል የመግባት፣ እና የሞት ስጋትን በእጅጉ ቀንሰዋል።
WA Notify እና የተጋላጭነት ማስታወቂያዎች በሜይ 11፣ 2023 የሚቋረጡ ይሆናል። ከ ሜይ 11 ጀምሮ፣ የ COVID-19 ፖዝቲቭ የምርመራ ውጤት ያለው ሰው አጠገብ ከነበሩ ስልክዎ ከዚህ በኋላ አያሳውቅዎትም። የእርስዎ ግላዊነት የተጠበቀ ነው፣ እንዲሁም ምንም አይነት የ GPS ቦታ ወይም በግል ሊለይ የሚችል መረጃ አልተሰበሰበም ወይም አልተከማቸም ነበር።
የ COVID-19 ስርጭትን ለመቀነስ እባክዎ የህዝብ ጤና መመሪያዎች መከተልዎን ይቀጥሉ። በክትባት፣ በምርመራ፣ በህክምና፣ እና መመሪያ ላይ ተጨማሪ መረጃ በ ዋሽንግተን ግዛት የጤና መምሪያ የ COVID-19 የመመሪያ ድረገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
WA Notify (WA ማሳወቂያ (በተጨማሪም የዋሺንግተን የተጋላጭነት ማሳወቂያ/Washington Exposure Notifications) ለኮቪድ-19 የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ለሆኑ ተጠቃሚዎች ተገቢውን ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ በስማርት ስልክዎ ላይ ሊያካትቱት የሚችሉት ነጻ መገልገያ ነው። ሙሉ በሙሉ ግላዊ ነወ፣ ማናቸውንም የግል መረጃ የማይሰበስብ ወይም የማያጋራ ሲሆን የሚሄዱበትን ቦታ አይከታተልም።
WA Notify ን በስልኬ ላይ እንዴት ማከል እችላለሁ?

በ iPhone ላይ፣ በቅንብሮች/በሴቲንግስ ውስጥ የተጋላጭነት ማሳወቂያዎችን (Exposure Notifications) ያንቁ/ያብሩ፦
- ወደ Settings (ቅንብሮች) ይሂዱ
- ወደ Exposure Notifications (የተጋላጭነት ማሳወቂያዎች) ወደታች ዝቅ ያድርጉ
- “Turn on Exposure Notifications (የተጋላጭነት ማሳወቂያዎች ያብሩ)” ጠቅ ያድርጉ
- United States (ዩናይትድ ስቴትስ)ን ይምረጡ
- Washington ን ይምረጡ
ለአንድሮይድ ወይም አይፎን፣ QR ኮዱን ስካን ያድርጉ ወይም ተንቀሳቃሽ መሳርያ የሚጠቀሙ ከሆነ WA Notify ስልክዎ ላይ ይጫኑ።

የሚሰራው እንዴት ነው?
የእርስዎን WA Notify፣ ሲያበሩ ስልክዎ በአቅራቢያዎ ካሉ የራሳቸውን WA Notify ካበሩ ሰዎች ስልኮች ጋር እንዲሁ የዘፈቀደ፣ የማይታወቁ ኮዶች ይለዋወጣል። ስርዓቱ ስለእርስዎ ማናቸውንም መረጃ ሳያሳውቅ እነዚህን ኮዶች ለመለዋወጥ ግላዊ መረጃን የሚጠብቅ Low Energy Bluetooth ቴክኖሎጂን ይጠቀማል። በቅርቡ ያገኙት አንድ ሌላ የ WA Notify ተጠቃሚ ባደረገው ምርምራ በኮቪድ-19 መያዙን ካረጋገጠ እና ማንነቱ ሳይገለጽ ለሌሎች የሚገለጽበትን ደረጃዎች የተከተለ ከሆነ፣ የማንቂያ መልእክት ይደርስዎታል። ይህ በፍጥነት የሚያስፈልግዎትን እንክብካቤ እንዲያገኙ ያስችልዎታል እንዲሁም COVID-19 ን በአካባቢዎ ላሉት ሰዎች እንዳያዛምቱ ያግዝዎታል።
ማስጠንቀቂያ ከማያስፈልጋቸው ደህንነቱ በተጠበቀ ርቀት ወይም አጭር ከሆነ COVID-19 ሊያስተላልፉ የሚችሉ ክስተቶችን ለመለየት አንድ ስልተ ቀመር ሂሳብን ይሠራል። WA Notify ተጋልጠው ከሆነ ብቻ ያሳውቀዎታል። ስለዚህ ማንቂያ አለመቀበል ጥሩ ዜና ነው።
በተጨማሪም WA Notify ከ30 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ይገኛል።

ግላዊነቴ እንዴት ይጠበቃል?
WA Notify የተጠቃሚውን ግላዊነት ለመጠበቅ በተዘጋጀው በ Google Apple ተጋላጭነት ማሳወቂያ ቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረተ ነው። ማናቸውንም መገኛ ቦታ ወይም የግል መረጃ ሳይሰበስብ ወይም ሳያሳውቅ ከኋላ መስራት ይችላል። WA Notify በትክክል ለመስራት እርስዎ ማን እንደሆኑ ወይም የት እንዳሉ ማወቅ አያፈልገውም። የብሉቱዝ ጥቃቅን ፍንዳታዎችን ብቻ በመጠቀም፣ የእርስዎ ባትሪ ምንም አይሆንም።
ተሳትፎዎ ሙሉ በሙሉ በፈቃደኝነት ነው። ተጠቃሚዎች በማንኛውም ጊዜ መርጠው መግባት ወይም መውጣት ይችላሉ። ስለተጠቃሚ የግል መረጃ ጥበቃ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ WA Notify የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲን ይመልከቱ።
ማሳወቂያዎቹ ምን ይመስላሉ?
ሊደርስዎት የሚችሉ ሁለት አይነት ማሳወቂያዎች አሉ። በምርመራ ፖዘቲቭ የሆኑት የማረጋገጫ ሊንክ የጽሁፍ መልእክት እና/ወይም ብቅ የሚል ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል። ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ የ WA Notify ተጠቃሚዎች የተጋላጭነት ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል። ስለ እነዚህ ማሳወቂያዎች የበለጠ ይወቁ እና ምን እንደሚመስሉ ይመልከቱ።
WA Notify የሚያግዘው እንዴት ነው?
የተጋላጭነት ማሳወቂያዎችን የሚጠቀሙ ሰዎች በበዙ ቁጥር ጥቅሙ እየጨመረ እንደሚመጣ ጥናቶች አረጋጠዋል። በዋሽንግተን ግዛት በሶስት አውራጃዎች ላይ የተመሰረቱ ሞዴሎች እንደሚያሳዩት እዚያ WA Notify የሚጠቀሙ ጥቂት ሰዎች እንኳን ኢንፌክሽኖችን እና ሞትን እንደሚቀንሱ ያሳያሉ። ክትባት ስንወስድ እና የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ሲጠቀሙ፣ የብዙ ሰዎችን ህይወት መታደግ ይችላሉ። በአካል የምንገኝባቸው ፕሮግራሞች ላይ መሳተፋችንን ስንቀጥል፣ WA Notify አንዱ ተጨማሪ የመከላከያ መሳሪያ ነው። እራስዎን እና በዙርያዎ ያሉ ሰዎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ሊያደርጉ የሚችሉት አንድ ተጨማሪ ነገር ነው።
በግ ምርመራ በኮቪድ-19 መያዝዎን ካረጋገጡ፣ ሌሎችን እንዴት ያሳውቃሉ
የግል መመርመርያ መሳያ (በተጨማሪም የቤት ውስጥ መመርመርያ መሳርያ እየተባ የሚታወቁትን) የተጠቀሙ እና በምርመራው በኮቪድ-19 መያዛቸውን ያረጋገጡ የWA Notify ተጠቃሚዎች ለሌሎች የWA Notify ተጠቃሚዎች ለኮቪድ-19 ተጋልጠው ሊሆን እንደሚችል ማንነታቸው ሳይገለጽ ለማሳወቅ የማረጋገጫ ኮድ እንዲሰጣቸው መጠየቅ ይችላሉ።

በ iPhone ላይ፦
- ወደ Settings (ቅንብሮች) ይሂዱ እና Exposure Notifications (የተጋላጭነት ማሳወቂያዎች)ይክፈቱ።
- “Share a COVID-19 Diagnosis (የ COVID-19 ምርመራን ያጋሩ)" የሚለውን ይምረጡ።
- “Continue (ቀጥል)” የሚለውን ይምረጡ።
- ኮዱን የሚያስገቡበት አንድ አማራጭ ካዩ፣ “ኮድ አላገኙም? “Didn’t get a code (ኮድ አላገኙም)? የሚለውን ይምረጡ። Visit WA State Dept. of Health Website (የዋሺንግተን ግዛት የጤና መምሪያ ድር ጣቢያን ይጎብኙ)።" የእርስዎን ኮድ የሚያስገቡበት አንድ አማራጭ ካላዩ፣ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ይሂዱ።
- WA Notify የሚጠቀመውን መሳሪያዎን ስልክ ቁጥር እና አወንታዊ የ COVID-19 ምርመራ ውጤት ያገኙበትን ቀን ያስገቡ።
- “Continue (ቀጥል)” የሚለውን ይምረጡ።

በ Android ስልክ ላይ፦
- WA Notify ን ይክፈቱ እና "Share your test result to help stop the spread of COVID-19 (የCOVID-19 ስርጭትን ለማስቆም የምርመራ ውጤትዎን ያጋሩ)" የሚለውን ይምረጡ።
- “Continue (ቀጥል)” የሚለውን ከዚያ “I need a code (ኮድ እፈልጋለሁ)” የሚለውን ይምረጡ።
- WA Notify የሚጠቀመውን መሳሪያዎን ስልክ ቁጥር እና አወንታዊ የ COVID-19 ምርመራ ውጤት ያገኙበትን ቀን ያስገቡ።
- “Send Code (ኮድ ላክ)” የሚለውን ይምረጡ።
ለአንድሮይድ ወይም አይፎን፣ QR ኮዱን ስካን ያድርጉ ወይም ተንቀሳቃሽ መሳርያ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ የማረጋገጫ ኮድ ይጠይቁ።

የማረጋገጫ ሊንክ ብቅ የሚል ማሳወቂያ እና የጽሁፍ መልእክት ይደርስዎታል። ማንነትዎን ሳያሳውቁ ሌሎች ተጠቃሚዎችን ሊከሰት ለሚችል ተጋላጭነት ለማንቃት ማሳወቂያን መንካት ወይም በጽሁፍ መልእክቱ ውስጥ ያለውን ሊንክ መጫን እና WA Notify ውስጥ ያሉ ደረጃዎችን መከተል ብቻ ያስፈልግዎታል።
በ WA Notify ውስጥ የማረጋገጫ ኮድ መጠየቅ ካልቻሉ የግዛቱን ኮቪድ-19 ነጻ የስልክ መስመር መደወል አለባችሁ፣ 1-800-525-0127፣ በመቀጠል # ን ይጫኑ እና እርስዎ የ WA Notify ተጠቃሚ መሆንዎን ለቀጥታ መስመር ሰራተኞች ያሳውቁ። የቀጥታ የስልክ መስመሩ ሰራተኞች ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች የ WA Notify ተጠቃሚዎችን እንዲያነቁ መጠቀም የሚችሉትን የማረጋገጫ ሊንክ ሊሰጡዎች ይችላሉ።
በግል በሚደረግ የኮቪድ-19 ምርመራ በበሽታው መያዝዎን የሚገልጹ የምርመራ ውጤቶችን እንዴት ሪፖርት ያደርጋሉ።
የግል የመመርመርያ መሳርያ (በተጨማሪም የቤት ውስጥ መመርመርያ መሳርያዎች ተብለው የሚታወቁትን) የሚጠቀሙ እና በኮቪድ-19 መያዛቸውን በምርመራ ያረጋገጡ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን የሚገልጹ ውጤቶችን ከWA Notify መተግበርያ ውጪ ለጤና መምሪያ Department of Health (DOH፣ ከዋሺንግተን ግዛት ጤና መምሪያ) ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። በበሽታው መያዝን የሚገልጹ የምርመራ ውጤቶችን ሪፖርት ስለሚያደርጉበት ሁኔታ ያለውን ወቅታዊ መመርያ ለማግኘት refer to the DOH Testing for COVID-19 page ይመልከቱ።
ነጻ ግላዊ የመመርመርያ መሳርያዎችን ከሚከተለው ማግኘት ይቻላል፥ Say Yes! (አዎ በል!) COVID Test (የኮቪድ ምርመራ)።
ተጨማሪ መመርያዎችን DOH በኮቪድ-19 መያዝዎን በምርመራ ካረጋገጡ ምን ማድረግ አለብዎት ከሚለው መረጃ ማግኘት ይቻላል።
እባክዎ ያስታውሱ፦ WA Notify የተጋላጭነት ማሳወቂያ መሳሪያ ነው። ተጠቃሚዎች የምርመራ ውጤታቸውን ለ DOH ሪፖርት እንዲያደርጉ ታስቦ የተዘጋጀ አልነበረም። ውጤቶች ለDOH ሪፖርት የሚደረጉት ከWA Notify የመተግበርያ ስርዓት ውጪ ነው።
ሁለቱንም የግንኙነት ፍለጋ/ፈለግ እና WA Notifyን ለምን እንፈልጋለን?
የግንኙነት ፍለጋ ለአስርተ ዓመታት ውጤታማ የህዝብ ጤና ጣልቃ ገብነት ሆኗል። WA Notify ይህንን ስራ በማይታወቅ መልኩ ይደግፋል። ምሳሌ ይኸውልዎት፦ ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ፣ የሕዝብ ጤና ጥበቃ ባለሥልጣኖች ደውለው የቅርብ ጊዜ ቅርብ ግንኙነቶችዎን እንዲያጋሩ ሊጠይቁዎት ይችላሉ። በአውቶብስ ውስጥ አጠገቡ የተቀመጡትን እንግዳ ሰው ስም መጥቀስ አይችሉም። ሁለታችሁም WA Notify የምትጠቀሙ ከሆነ፣ አውቶቡሱ ውስጥ የነበረው እንግዳ ተጋላጭነት ሊኖረው እንደሚችል በስውር ማሳወቂያ ይደርሰዋል እናም COVID-19 ለጓደኞቻቸው እና ለቤተሰቦቻቸው እንዳይዛመት ለመከላከል እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ። እንደ ክትባት እና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ሁሉ እያንዳንዳቸው የኮቪደ-19 ስርጭትን ለመግታት ያግዛል፣ በአንድነት ጥቅም ላይ ሲውሉ ደግሞ ይበልጥ ውጤታማ ናቸው።
WA Notify ን መጠቀሜን መቀጠል ይኖርብኛል ወይስ አሁን ልዘጋው እችላለሁ?
ማንኛውም ሰው WA Notifyን በስልኩ ላይ እንዳስነሳው እንዲቆይ እና እንዳይዘጋው እናበረታታለን። ገደቦች እየላሉ በመምጣታቸው እና ስራዎች ወይም እንቅስቃሴዎች ተመልሰው የቀጠሉ በመሆኑ፤ WA Notify ከራዎ ጋር ተጨማሪ መከላከያ ይዘው ሊንቀሳቀሱ የሚችሉበት ቀላሉ መንገድ ነው።
ተከትቤ ከነበረ WA Notify ያስፈልገኛል?
አዎ። የዋሺንግተን ግዛት ለተወሰነ ጊዜ ኮቪድ-19ን እየተቆጣጠረ ይቀጥላል። ስለቫይረሱ እስካሁን ድረስ በርካታ ነገሮችን እያወቅን ነው፣ ለምሳሌ ክትባቶች ለምን ያህል ጊዜ ውጤታማ እንደሚሆኑ እና ክትባቶች ከአዳዲስ የኮቪድ-19 ዝርያዎች ምን ያህል በአግባቡ ሊከላከሉን እንደሚችሉ እያወቅን ነው። ምንም እንኳን ክትባት ለወሰዱ ሰዎች ስጋቱ አነስተኛ ቢሆንም፤ ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ግለሰቦች አሁንም በኮቪድ-19 ሊያዙ እና ወደሌሎች ሰዎች ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ እናውቃለን። በተጨማሪም እስካሁን ድረስም ያልተከተቡ ግለሰቦች እንዳሉ እናውቃለን። በነዚህ ሁሉ ምክንያቶች የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት ድጋፍ ለማድረግ ሁሉም የዋሺንግተን ነዋሪዎች WA Notifyን በስልካቸው ላይ እንዲያስነሱ እናበረታታለን።
ስለ WA Notify መረጃ ማሰራጨት ይፈልጋሉ?
ለማህበራዊ ሚዲያ መልዕክቶች፣ ፖስተሮች፣ ለናሙና የሬዲዮ እና የቲቪ ማስታወቂያዎች የእኛን የ WA Notify የመገልገያ መሳሪያ ይመልከቱ። በተጨማሪም ለጓደኞችዎ እና ለቤተሰብዎ ይንገሩ። WA Notify ን የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር በጨመረ ቁጥር፣ እርስዎን እና ማህበረሰብዎን ለመከላከል በመርዳት ረገድ የተሻለ እየሆነ ይመጣል።
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ሌሎች ጥያቄዎች
- በ WA Notify ላይ ተጋላጭ ልሆን የቻልኩበትን ቀን እንዴት ማግኘት እችላለሁ?
-
በ iPhone ላይ፦
-
ወደ Settings (ቅንብሮች) ይሂዱ
- Exposure Notifications (የተጋላጭነት ማሳወቂያዎች) ይምረጡ ወይም Exposure Notifications (የተጋላጭነት ማሳወቂያዎች) በመፈለጊያው ላይ ያስገቡ
- እርስዎ ለቫይረሱ ተጋላጭ ሊሆኑ የቻሉበት ግምታዊ ቀን “You may have been exposed to COVID-19” (“ለኮቪድ-19 ተጋልጠው ሊሆን ይችላል”) በሚለው ስር ይታያል።
በ Android ላይ፦
-
የ WA Notify መተግበሪያን ይክፈቱ
- እባክዎን በ “Possible exposure reported (ሪፖርት የተደረጉ የመጋለጥ ዕድሎች) ” ስር See Details (ዝርዝሮችን ይመልከቱ) የሚለውን ይምረጡ
- እርስዎ ለቫይረሱ የተጋለጡበት ግምታዊ ቀን “Possible Exposure Date” (“ሊሆን የሚችል የተጋላጭነት ቀን”) የሚለው ስር ይታያል።
-
- ከ Washington State Department of Health (DOH፣ የዋሺንግተን ግዛት የጤና መምሪያ) ማሳወቂያ እና/ወይም የጽሑፍ መልዕክት ደርሶኛል። ለምን?
-
DOH ለ COVID-19 ምርመራ በቅርቡ ፖዘቲቭ የሆኑ ሰዎች ለሚጠቀሙባቸው ስልክ ቁጥሮች የጽሁፍ መልእክት እና/ወይም ብቅ የሚል ማሳወቂያ ይልካል፣ ይህን የሚያደርገው የ WA Notify ተጠቃሚዎች ሊፈጠር ስለሚችል መጋለጥ በፍጠነት እና ማንነታቸውን ሳይገልጹ ለሌሎች ማሳወቅ እንዲችሉ ለማድረግ ነው። ስለ እነዚህ ማሳወቂያዎች የበለጠ ይወቁ እና ምን እንደሚመስሉ ይመልከቱ።
የጽሁፍ መልእክት እና ማሳወቂያ ሁለቱም ከደረሰዎት፣ ማንነትዎን ሳያሳውቁ ለሌሎች ተጠቃሚዎች ሊኖራቸው የሚችለውን ተጋልጦ ለማሳወቅ ማሳወቂያውን መንካት ወይም በጽሁፍ መልእክቱ ውስጥ ያለውን ማስፈንጠርያ መጫን እና በ WA Notify ውስጥ ያሉትን ደረጃዎች መከተል ብቻ ነው የሚያስፈልግዎት።
- የእኔን የ WA Notify ውሂብ ለሕዝብ ጤና ስለ ማበርከት የተመለከተ ማሳወቂያ ደርሶኛል። ለምን?
-
ጤና መምሪያ (DOH) WA Notify ምን ያህል በአግባቡ እንደሚሰራ ማወቅ ይፈልጋል፣ በዚህም ለመሳያው የሚያስፈልጉትን ማናቸውንም ማሻሻያዎች ማድረግ እንችላለን። የእርስዎን የ WA Notify ውሂብ እንድናጋራ የሚስማሙ ከሆነ፣ የእርስዎ ግላዊነት አሁንም ድረስ ቢሆን ሙሉ በሙሉ ጥበቃ የሚደረግለት ይሆናል። ምንም ዓይነት የግል መረጃ አይሰበሰብም ወይም ለሌሎች አይጋራም እንዲሁም እርስዎን ለይቶ ማወቅ የሚያስችል ምንም መንገድ የለም። DOH ብቻ ይህን ውሂብ በግዛት ደረጃ ብቻ ሊደርስበት ይችላል።
- የ WA Notify ተጠቃሚዎች የእነርሱ ውሂብ እንዲጋራ ከተስማሙ፣ የሚሰበሰበው መረጃ ምንድን ነው?
-
የእርስዎ ውሂብ እንዲጋራ የሚስማሙ ከሆነ፣ የእርስዎ ግላዊነት አሁንም ድረስ ቢሆን ሙሉ በሙሉ ጥበቃ የሚደረግለት ይሆናል። ምንም ዓይነት የግል መረጃ አይሰበሰብም ወይም ለሌሎች አይጋራም በመሆኑም እርስዎን ለይቶ ማወቅ የሚያስችል ምንም መንገድ የለም። የሚከተሉትን የሚያካትተውን ይህን ግዛት አቀፍ መረጃ ማየት የሚችለው ጤና መምሪያ DOH ብቻ ነው፡
- በእነርሱ WA Notify ውስጥ ያለው ውሂባቸው እንዲጋራ የተስማሙ ሰዎች ብዛት። ይህ የእኛ ናሙና ምን ያክል ሁሉንም ወካይ እንደሆነ እንድናውቅ ያስችለናል።
- የ WA Notify ተጠቃሚዎች የተቀበሉት የተጋላጭነት ማሳወቂያዎች ብዛት። ይህ የ COVID-19 ስርጭትን አካሄድ እንድናይ ያግዘናል።
- በተጋላጭነት ማሳወቂያ ላይ ጠቅ ያደረጉ ሰዎች ብዛት። ይህ ሰዎች ምን ያክል የሕዝብ ጤና ምክሮችን ለመስማት ፈቃደኛ እንደሆኑ እንድንረዳ ያግዘናል።
- የ COVID-19 ምርመራ ውጤታቸው አዎንታዊ ከሆነ ሰው አጠገብ የነበሩ ሰዎች ሆኖም ግን ተጋላጭ እንደሆኑ ማሳወቂያ እንዳይላክላቸው ያን ያክል ያልተቀራረቡ ወይም ለረዥም ጊዜ ያልቆዩ ሰዎች ብዛት። ይህ በ WA Notify ያለው የተጋላጭነት ማሳወቂያ ቀመር መስተካከል እንዳለበት ወይም እንደሌለበት እንድንወስን ያግዘናል።
- በእኔ iPhone ላይ WA Notify ን ሳሠራው፣ "Availability Alerts (የተገኝነት ማንቂያዎች)"ን ማብራት ወይም ማጥፋት አለብኝ?
-
ማጥፋት ችግር የለውም። ሆኖም ግን ከዋሽንግተን ግዛት ለረዥም ጊዜ ርቀው የሚጓዙ ከሆነ ቢያበሩት ይመከራል። Availability Alerts (የመገኘት/የመኖር ማንቂያ) ክፍት በሚሆንበት ጊዜ፣ ልክ እንደ WA Notify የተጋላጭነት ማሳወቂያ መሳርያ ወደሚሰጥ ወደሌላ ቦታ በሚጓዙበት ጊዜ ማሳወቂያ ሊደርስዎ ይችላል። አይፎን ካለዎት፣ በርካታ ክልሎችን ሊያካትቱ ይችላሉ፣ ነገር ግን በአንድ ጊዜ ሊነሳ የሚችለው አንድ ክልል ብቻ ነው። አዲስ ቦታ እንዲሠራ ለማድረግ ክልልን ማስወገድ አያስፈልግዎትም። አንድሮይድ ስልክ ካለዎት፣ ከተለያዩ ግዛቶች እንደ WA Notify ያሉ የተጋላጭነት ማሳወቂያ መተግበርያዎችን ከበርካታ ግዛቶች ኢንስቶል ማድረግ ይችላሉ፣ ነገር ግን በአንድ ጊዜ ሊነሳ ወይም ሊሰራ የሚችለው ከ WA Notify ጋር የሚናበብ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም አንድ መተግበርያ ብቻ ነው።
- WA Notify ለመጠቀም መርጬ መግባት አለብኝ?
-
አዎ። WA Notifyን የሚጠቀሙት በነጻ እና በፈቃደኝነት ነው። በማንኛውም ጊዜ መርጠው መውጣት ይችላሉ። ይህን ለማድረግ በአይፎን ላይ በቀላሉ ዝጋ የሚለውን መክፈት ወይም መተግርያውን ከአንድሮይድ ስልክ ላይ ይሰርዙ ወይም ያጥፉ። መጠቀምዎን ሲያቋርጡ፣ ስልኩ ከሌሎች በቅርበት ካሉ ተጠቃሚዎች የሰበሰባቸው ኮዶች በሙሉ የሚሰረዙ ሲሆን እነዚህን ኮዶች መልሶ ማግኘት አይቻልም።
- WA Notify የእውቂያ ፍለጋ መተግበሪያ ነው?
-
አይ። WA Notify ከእርስዎ ጋር በቅርበት የተገናኙ ሰዎችን አይከታተልም ወይም ስለነሱ መረጃ አይሰበስብም፣ በመሆኑም “የግንኙነት ክትትል” አይሰራም። እውቂያ ፍለጋ ለ COVID-19 ፖዘቲቭ የሆነን ወይም የተጋለጠን ማንኛውንም ሰው ይለያል። መሳሪያው ግላዊ መረጃን አይሰበስብም ወይም አይለዋወጥም፣ ስለዚህ ማንም ሰው እርስዎ ከማን ጋር እንደተገናኙ ሊያውቅ አይችልም።
- "ተጋላጭነት" ምንድነው?
-
ተጋላጭነት የሚከሰተው በኋላ ላይ ባደረገው ምርመራ በ COVID-19 መያዙን ካረጋገጠ ሌላ የWA Notify ተጠቃሚ ጋር ለተወሰነ ጊዜ በቅርበት ሲያሳልፉ ነው። ተጋላጭነትን ለመወሰን፣ WA Notify ደህንነቱ ከተጠበቀ ርቀት ወይም ማስጠንቀቂያ ከማያስፈልገው አጭር ርቀት ላይ ካሉ ሰዎች COVID-19 ን ሊያስተላልፉ የሚችሉ ኩነቶችን የሚለይ ስልትን ይጠቀማል። WA Notify ከሌላ ተጠቃሚ ጋይ ያልዎት መስተጋብር በቂ የሆነ አጭር ወይም ረዥም ከሆነ ይህም DOH የ COVID-19 ስርጭት ከፍተኛ ስጋት አለ ብሎ የሚያምንበትን ሁኔታዎች ሲያሟላ ብቻ የተጋላጭነት ማሳወቂያ ይልክልዎታል። ይህ የስሌት ስልት በማህበረሰብ ጤና ኃላፊዎች ሊስተካከል ይችላል።
- WA Notify ተጋላጭ እንደሆንኩ ቢነግረኝ ምን ይፈጠራል?
-
የ WA Notify እርስዎ የተጋለጡ ሊሆኑ እንደሚችሉ ካወቀ፣ በስልክዎ ላይ ያለው ማሳወቂያ ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለብዎት መረጃ ወዳለው ድረ-ገጽ ይመራዎታል። ይህ እንዴት እና የት መመርመር እንዳለብዎት፣ እራስዎን እና በቅርብዎ ያሉትን ደህንነት ስለመጠበቅ መረጃ፣ እና ለጥያቄዎችዎ መልስ የሚሆኑ መርጃዎችን ያጠቃልላል። በድረ-ገጹ ላይ ያሉትን መመሪያዎች በጥንቃቄ ማንበብ እና መከተል አስፈላጊ ነው።
- ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ካደረግኩ ሰዎች ያውቃሉ?
-
አይ። WA Notify ስለ እርስዎ ማንኛውንም መረጃ ለማንም ሰው አያጋራም። አንድ ሰው ሊኖር ስለሚችለው ተጋልጦ ማሳወቂያ ሲደርሰው፣ ሊያውቀው የሚችለው ነገር በቅርቡ በቅርበት አብሮት የነበረ ሰው በኮቪድ-19 መያዙን በምርመራ ማረጋገጡን ብቻ ነው። ግለሰቡ ማን እንደሆነ ወይም ተጋልጦው የተከሰተው የት እንደሆነ አያውቁም።
- ለ WA Notify መክፈል አለብኝ?
-
አይ። WA Notify ነፃ ነው።
- WA Notify ለዋሽንግተን ግዛት እንዴት ይረዳል?
-
አንድ በUniversity of Washington የተሰራ ጥናት (እንግሊዘኛ ብቻ) የተጋላጭነት ማሳወቂያ የሚጠቀሙ ሰዎች ብዛት በጨመረ ቁጥሩ ጥቅሙ ከፍተኛ እየሆነ እንደሚመጣ ደርሶበታል። WA Notify ጥቅም ላይ በዋለባቸው የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ላይ በግምት ከ 40 እስከ 115 የሚሆኑ ሰዎችን ህይወት እንዳዳነ እና ወደ 5,500 አካባቢ የ COVID-19 ጉዳዮችን እንደተከላከለ ውጤቶች አሳይተዋል። WA Notify የሚጠቀሙ ጥቂት ሰዎች እንኳን የ COVID-19 ኢንፌክሽኖችን እና ሞትን እንደሚቀንሱ የመረጃ ሞዴሎች ያሳያሉ፣ ይህም WA Notify የ COVID-19 ስርጭትን ለመከላከል ወሳኝ መሳሪያ እንደሆነ ያሳያል።
- ከግዛት ውጭ ከተጓዝኩ WA Notify ለስራዬ ያሳውቃል?
-
አዎ። ተመሳሳይ የ Google/Apple ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ መተግበሪያዎች (እንግሊዘኛ ብቻ) ወዳሉበት ግዛት የሚጓዙ ከሆነ፣ ስልክዎ በግዛቱ ውስጥ ካሉ ተጠቃሚዎች ጋር የዘፈቀደ ኮዶችን መለዋወጥ ይቀጥላል። በስማርት ስልክዎ ማስተካከያዎች /ሴቲንግስ/ ውስጥ ማናቸውንም ለውጥ ማድረግ አያስፈልግም። ለተራዘመ ጊዜ ከዋሽንግተን ለቀው ከሄዱ፣ የአከባቢን ድጋፍ እና ማስጠንቀቂያ ለማግኘት በአዲሱ ግዛት ውስጥ ያሉትን አማራጮች መገምገም አለብዎት።
- WA Notify ለሌሎች ተጠቃሚዎች ለማሳወቅ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?
-
በሌላ ተጠቃሚ ለ COVID-19 የተጋለጡ ሊሆኑ የሚችሉ ተጠቃሚዎች COVID-ያለበት/የያዘው ተጠቃሚ ሌሎችን የ WA Notify ተጠቃሚዎች ማንነትን ሳይገልጽ ለማሳወቅ በ WA Notify ውስጥ ያሉትን ቅደም ተከተሎች ከተከተለ በኋላ በ 24 ሰዓታት ውስጥ ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል።
- ከ WA Notify ብዙ ማስጠንቀቂያዎችን መቀበል ይቻላል?
-
መያዛቸውን በምርመራ ያረጋገጡ ተጠቃሚዎች፣ ያልተጠበቀ ማሳወቂያ እና የጽሁፍ መልእክት ሁለቱም ይደርሳቸዋል። ለበርካታ ጊዜያት የመጋለጥ ሁኔታ የተከሰተባቸው ተጠቃሚዎች ሰለማንኛውም አዳዲስ የተጋላጭነት አጋጣሚ እንዲያውቁ ይደረጋል።
- ለ COVID አዎንታዊ ምርመራ ካደረግኩ ለ WA Notify እንዴት መናገር እችላለሁ?
-
በበሽታው መያዝዎን በምርመራ ካረጋገጡ እና ከጤና መምሪያ (DOH) ወይም ከአካባቢዎ የማህበረሰብ ጤና ባለስልጣን አንድ ሰው ካናገረዎት፣ WA Notify የሚጠቀሙ መሆኑን ይጠይቁዎታል። የሚጠቀሙ ከሆነ፣ የማረጋገጫ አያያዥ እና/ወይም ማሳወቂያ ይልኩልዎት እና ወደ WA Notify ለመግባት ቅደም ተከተሎቹን እንዲከተሉ ይረዱዎታል። ማሰፈንጠርያው ወይም ማሳወቂያው ከእርስዎ የግል መረጃ ጋር የተያያዘ አይደለም። በተጨማሪም ጤና መምሪያ (DOH) በቅርቡ በኮቪድ-19 መያዛቸውን በምርመራ ያረጋገጡ ሰዎች ሲጠቀሙባቸው ለነበሩ ስልክ ቁጥሮች የጽሁፍ መልእክት እና/ወይም ማሳወቂያ ይልካል።
የጤና መምሪያ (DOH) እርስዎ ደረጃዎቹን በሚከተሉበት ጊዜ የWA Notify የተጋላጭነት ማሳወቂያዎች ለእነማን እንደሚደርሱ የሚያውቅበት መንገድ የለም። የተጋላጭነት ማሳወቂያው ስለ እርስዎ፣ ወይም የት በአቅራቢያዎ እንደነበሩ መረጃን አያካትትም። በ WA Notify በኩል ማንነታቸውን ሳይገልጹ ውጤቶቻቸውን የሚያረጋግጡ ሰዎች በጨመሩ ቁጥር፣ የ COVID-19 ስርጭትን በተሻለ ሁኔታ ልንከላከል እንችላለን።
በበሽታው መያዝዎን በምርመራ ካረጋገጡ እና አሁንም ማንነትዎ ሳይታወቅ ውጤትዎን WA Notify ውስጥ ማረጋገጥ የሚፈልጉ ከሆነ፣ ለሌሎች የ WA Notify ተጠቃሚዎች ሊኖር ስለሚችል ተጋልጦ ማንነትዎ ሳይገለጽ ለማሳወቅ የማረጋገጫ ኮድ ለመጠየቅ ያ ደረጃዎችን ለመከተል በዚህ ገጽ ላይ ከላይ ባለው ክፍል ውስጥ “በግል ምርመራ በኮቪድ-19 መያዝዎን ካረጋገጡ ለሌሎች እንዴት ማሳወቅ ይችላሉ”የሚለውን ክፍል ይመልከቱ።
- WA Notify ን ወደ ስልኬ ካከልኩ በኋላ ማድረግ ያለብኝ ነገር አለ?
-
ተጨማሪ እርምጃ የሚያስፈልግው የሚከተሉት ከሆኑ ብቻ ነው፦
- ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ፣ ወይም
- ተጋልጠው ሊሆን እንደሚችል ማሳወቂያ ከደረስዎት ነው።
በበሽታው መያዝዎን በምርመራ ካረጋገጡ እና ከጤና መምሪያ (DOH) ወይም ከአካባቢዎ ማህበረሰብ ጤና ባለስልጣን አንድ ሰው ካናገረዎት፣ WA Notify እየተጠቀሙ ስለመሆኑ ይጠይቅዎታል። የሚጠቀሙ ከሆነ፣ የማረጋገጫ አያያዥ እና/ወይም ማሳወቂያ ይልኩልዎት እና ወደ WA Notify ለመግባት ቅደም ተከተሎቹን እንዲከተሉ ይረዱዎታል። አያያዡ ወይም ማሳወቂያው ከግል መረጃዎ ጋር የተያያዘ አይደለም። ስለ ተጋላጭነታቸው በመተግበሪያው በኩል ማን ማሳወቂያ እንደሚደርሰው DOH የሚያውቅበት መንገድ የለውም። የተጋላጭነት ማሳወቂያው ስለ እርስዎ፣ ወይም የት በአቅራቢያዎ እንደነበሩ መረጃን አያካትትም። በ WA Notify በኩል ማንነታቸውን ሳይገልጹ ውጤቶቻቸውን የሚያረጋግጡ ሰዎች በጨመሩ ቁጥር፣ የ COVID-19 ስርጭትን በተሻለ ሁኔታ ልንከላከል እንችላለን።
በበሽታው መያዝዎን በምርመራ ካረጋገጡ እና የማረጋገጫ ኮድ የሚፈልጉ ከሆነ፣ ሊኖር ስለሚችል ተጋልጦ ለሌሎች የ WA Notify ተጠቃሚዎች ማንነትዎ ሳይገለጽ ለማሳወቅ የማረጋገጫ ኮድ ለመጠየቅ የሚከተሏቸውን ደረጃዎች ለምግኘት በዚህ ገጽ ላይ ከዚህ በላይ “በግ ምርመራ በኮቪድ-19 መያዝዎን ሲያረጋግጡ ለሌሎች እንዴት ያሳውቃሉ” የሚለውን ክፍል ይመልከቱ።
- WA Notify መጠቀም ባትሪዬን ይጨርሳል ወይም ብዙ ዳታ ይጠቀማል?
-
አይ። ቴክኖሎጂ በመጠቀም በእርስዎ መረጃ እና በባትሪ የአገልግሎት ዘመን ላይ አነስተኛ ተጽእኖ እንዲኖረው ተደርጎ የተዘጋጀ ነው።
- WA Notify በጣም ብዙ ባትሪ እየተጠቀመ ያለ የሚመስለው ለምንድን ነው?
-
በርግጥ፣ እንደዚያ ላይሆን ይችላል። እንደ WA Notify ያሉ መተግበሪያዎችን ጨምሮ የእርስዎ ባትሪ በየቀኑ ምን ያክል ጥቅም ላይ እንደዋለ የሚያሳይ መቶኛን በእርስዎ መሣሪያ ላይ ያለው የባትሪ አጠቃቀም ያሳያል። አብዛኛዎቹ መተግበርያዎች እና መሳርያዎች በአንድ ሌሊት አይሰሩም። WA Notify እንደዚያም አያደርግም፣ ነገር ግን በበሽታው ለተያዘ ተጠቃሚ በየተወሰነ ሰዓቱ በተለየ መንገድ ያልተመረጡ ኮዶችን ያጣራል፣ በዚህም ሊኖር ስለሚችል ስለማናቸውም ተጋልጦ የማንቂያ መልእክት ይልክልዎታል። ስለዚህ፣ ለምሳሌ እርስዎ ተኝተው እያለ ሌሎች መተግበሪያዎች የማይሠሩ ያለ ከሆነ፣ WA Notify በዚህ ጊዜ ላይ ከፍተኛ የሆነውን የባትሪ አጠቃቀም መቶኛ ድርሻ ሊወስድ ይችላል። ይህ ማለት WA Notify ባትሪ ብዙ ይጠቀማል ማለት አይደለም - ጥቅም ላይ ከዋለው አነስተኛ ባትሪ ከፍተኛውን መጠን ማለት ነው።
- WA Notify እንዲሰራ ብሉቱዝ በርቶ እንዲቆይ ማድረግ ያስፈልገኛል?
-
አዎ። WA Notify Bluetooth Low Energy ይጠቀማል፣ ስለሆነም ብሉቱዝ በአቅራቢያ ያሉ ሌሎች ተጠቃሚዎችን ለመለየት ሲስተሙ ሁል ጊዜ መብራት አለበት።
- ስልኬ ላይ እንዲሰራ WA Notify መክፈት ያስፈልገኛል?
-
አይ። WA Notify ከበስተጀርባ ይሠራል።
- WA Notify ቆየት ባሉ ስማርት ስልኮች ላይ ሊሠራ ይችላል?
-
iPhone ተጠቃሚዎች የእርስዎ ሥርዓተ ክወና እንደሚከተለው ከሆነ WA Notify ን መጠቀም ይችላሉ፦
- iOS ስሪት 13.7 ወይም ከዚህ በኋላ የመጣ (ለ iPhone 6s፣ 6s Plus፣ SE ወይም የተሻለ አዲስ)
- iOS ስሪት 12.5 (ለ iPhone 6፣ 6 plus፣ 5s)
የ Android ተጠቃሚዎች የእርስዎ Android ስማርት ስልክ ብሉቱዝ ዝቅተኛ ኃይል አጠቃቀምን የሚቀበል ከሆነ እና Android ስሪት 6 (API 23) ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ WA Notify ን መጠቀም ይችላሉ።
- WA Notify ለመጠቀም 18 ዓመት መሆን አለብኝ?
-
አይ። WA Notify ዕድሜዎን አያውቅም ወይም አይፈትሽም።
- ስልኩን ከአንድ ሰው ጋር ከተጋራሁ ይህ ቴክኖሎጂ ይሠራል?
-
WA Notify በተጋላጭነት ጊዜ ስልኩን ማን ሲጠቀምበት እንደነበረ ማወቅ አይችልም፡፡ ስልክ የሚያጋሩ ከሆነ፣ WA Notify ለ COVID-19 ተጋላጭነትን የሚያመለክት ከሆነ ስልኩን የሚጠቀም እያንዳንዱ ሰው የህዝብ ጤና መመሪያዎችን መከተል አለበት፡፡
- ማሳወቂያ እና/ወይም የጽሁፍ መልእክት ደርሶኛል ነገር ግን የተመረመረው ሰው የቤተሰብ ወይም የቤት አባል ነበር። ምን ማድረግ አለብኝ?
-
ፖዘቲቭ የሆነ የ WA Notify ተጠቃሚ ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች ሰዎችን ማንነቱ ሳይታወቅ ለማንቃት ደረጃዎችን መከተል አለበት፣ ስለዚህ ለእርስዎ ያልሆኑ ማንኛውንም መልእክቶች ወይም ማሳወቂያዎች ችላ ማለት አለብዎት።
የእርስዎ ቤተሰብ ወይም የቤተሰብ አባል የWA Notify ተጠቃሚ ከሆነ፣ በበሽታው መያዙን በምርመራ ካረጋገጠ እና አሁንም ውጤታቸውን በWA Notify ማረጋገጥ የሚፈልጉ ከሆነ፣ በዚህ ገጽ ውስጥ “በግል ምርመራ በኮቪድ-19 መያዝዎን ካረጋገጡ ለሌሎች እንዴት ያሳውቃሉ” በሚለው ክፍል ውስጥ ያሉትን ደረጃዎች መከተል ይችላ።
- WA Notify እንደ iPads ወይም ስማርት ሰዓቶች ባሉ መሣሪያዎች ላይ ሥራውን ያሳውቃል?
-
አይ። የተጋላጭነት ማሳወቂያ ስርዓቱ በተለየ ሁኔታ ተዘጋጅቶ የነበረው ለስማርት ስልኮች ሲሆን በአይፓድ እና ታብሌቶች ላይ አይሰራም።
- ስማርት ስልኮች ለሌላቸው ሰዎች የዋሽንግተን ግዛት ለዚህ ቴክኖሎጂ ተደራሽነት ምን እያደረገ ነው?
-
WA Notify የ COVID-19 ስርጭትን ለመከላከል የሚረዳ ብቸኛው መሳሪያ አይደለም፡፡ የእውቂያ ፍለጋ/ፈለግ እና ሌሎች ጥረቶች ስማርት ስልክ ባይኖራቸውም ለእያንዳንዱ የዋሺንግተንን ነዋሪ ይጠቅማሉ፡፡ ክትባቶች የ COVID-19 ስርጭትን ለመከላከል ምርጥ መንገዶች ናቸው፣ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎችን ማድረግ፣ አካላዊ ረቀት እና የስብሰባዎችን መጠን መገደብ ሁሉም ሰው ሊያደርጋቸው የሚችል የ COVID-19 ስርጭትን ለማስቆም የሚረዱ ሌሎች መንገዶች ናቸው።
የፌዴራል መንግሥት Lifeline program (የሕይወት መስመር መርሃ-ግብር) ብቁ ለሆኑ ሰዎች ወርሃዊ የስልክ ሂሳብ ብድር ይሰጣል። አንዳንድ ተሳታፊ የገመድ አልባ አገልግሎት አቅራቢዎች ነፃ ስማርትፎንም ሊሰጡ ይችላሉ። ስለ መርሃ-ግብሩ፣ ማን ብቁ እንደሆነ፣ እንዴት ማመልከት እና መሳተፍ እንደሚቻል እና ተሳታፊ የገመድ አልባ አገልግሎት አቅራቢዎች የበለጠ ይወቁ (እንግሊዘኛ ብቻ)።
- ዋሽንግተን WA Notify ን በ 30 ቋንቋዎችን ለቆ ነበረ፣ እና ታዲያ ለምን በ Google Play መደብር ውስጥ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ እንደቀረበ ብቻ ሆኖ ይታየኛል?
-
WA Notify የሚሰራው በተጠቃሚወ ስልክ ላይ በዋናነት እንዲያገለግል በተመረጠው ቋንቋ መሰረት ነው። ያለው አንድ አይነት WA Notify ብቻ ነው፤ ነገር ግን ማናቸውም ያልተጠበቀ ማሳወቂያ - ለምሳሌ አንድ የተጋላጭነት ማሳወቂያ ከ30 በላይ በሆኑት ቋንቋዎች በተጠቃው በተመረጠው ቋንቋ ይመጣለታል።
- ማሳወቂያውን ለመንካት ወይም የማረጋገጫ ሊንኩን ለማንቃት ምን ያክል ጊዜ አለኝ?
-
WA Notify ውስጥ ሌሎችን ለማሳወቅ እርምጃዎቹን ለመከተል ማሳወቂያው ወይም የጽሁፍ መልእክት ከደረሰዎት በኋላ 24 ሰአት አልዎት። በዚያ ጊዜ ውስጥ ማሳወቂያውን መጫን ወይም የማረጋገቻ ማስፈንጠርያውን ክሊክ ማድረግ ካልቻሉ፣ በዚህ ገጽ ላይ ከላይ ባለው “በግል ምርመራ በኮቪድ-19 መያዝዎን ካረጋገጡ ለሌሎች እንዴት ያሳውቃሉ” በሚለው ክፍል ውስጥ ያሉትን ደረጃዎች በመከተል በ WA Notify ውስጥ የማረጋገቻ ኮድ ሊጠይቁ ይችላሉ። በተጨማሪም ስለኮቪድ-19 ምርመራ ውጤቶችዎ ሊጠይቅዎ አንድ ሰው ከጤና መምሪያ (DOH) ወይም ከአካባቢዎ የጤና ባለስልጣን ሲያናግርዎ የማረጋገጫ ማስፈንጠርያ ሊጠይቁ ይችላሉ።
- ዋሽንግተን ይህንን መፍትሄ ለምን መረጠ?
-
ዋሺንግተን የጸጥታ እና የሲቪል ነጻነት ባለሙያዎችን እና የተለያዩ ማህበረሰብ አባላትን ጨምሮ የጎግልን/አፕልን የተጋላጭነት ማሳወቂያ ስርዓት የሚገመግም አንድ የግዛት ተቆጣጣሪ ቡድን አቋቁሟል። ቡደኑ በፕላትፎርሙ/በመደላድሉ የተረጋገጠ አስተማማኝነት፣ ከፍተኛ የመረጃ ጥበቃ እና የሌሎች ግዛቶች አጠቃቀም ላይ በመመስረት ማሰተካከያ እንዲደረግ የውሳኔ ሀሳብ አቅርቧል።