COVID-19

This page is being reviewed for updates. The Washington State Department of Health has updated its guidance for what to do if you are sick with COVID-19 or were exposed to COVID-19. This page may have content that is inconsistent with the new guidance.

ይጠንቀቁ፣ WA - በ COVID-19 ውስጥ የተሻለ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ህይወት

አሁን COVID-19 ለረጅም ጊዜ ለመቆየት እንደመጣ እንዳለ እናውቃለን። በተቻለ መጠን የእራሳችንን፣ የምንወዳቸውን ሰዎች እና የማህበረሰቡን ደህንነት እየጠበቅን ህይወታችንን እንዴት እንደምንኖር መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው። ያንን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? እስካሁን የተማርናቸውን ቁሳቁሶች በሙሉ በመጠቀም፦ በክትባት መከተብ እና ማጠናከሪያ በመውሰድ፣ በመመርመር እና ከታመምን ወይም ከተጋለጥን ቤት በመቆየት፣ በተጨናነቀ ህዝብ ውስጥ ጭንብል በመልበስ እና ርቀታችንን በመጠበቅ።

COVID-19 ማህበረሰባችን ውስጥ እያለ አብሮ ወደ መኖር አዲስ የህይወት ደረጃ ስንገባ ማወቅ ያለብዎት ነገር እነሆ።

እርምጃ ይውሰዱ፣ ጥንቃቄ ያድርጉ

Decorative

ይከተቡ እንዲሁም ማጠናከሪያ ይውሰዱ

የ COVID-19 ክትባቶች እና ማጠናከሪያዎች ኢንፌክሽን እና ከባድ በሽታን ለመከላከል ቁጥር አንድ መከላከያ ናቸው።

ተጨማሪ ይወቁ

 

Decorative

መቼ እንደሚመረመሩ ይወቁ

ህመም ከተሰማዎት፣ በስብሰባ ላይ ከሆኑ ወይም ለ COVID-19 ከተጋለጡ፣ በመመርመር የ COVID-19 የመስፋፋት አደጋ ይቀንሱ።

ተጨማሪ ይወቁ

Decorative

ጭምብል ያድርጉ

ጭንብል መልበስ የ COVID-19 ስርጭትን እንደሚቀንስ የተረጋገጠ ሲሆን አሁንም በአንዳንድ አከባቢዎች ውስጥ ግዴታ ነው።

ተጨማሪ ይወቁ

 

አሁን COVID-19 ካለብዎ

የቅርብ ጊዜ መመሪያዎችን ይመልከቱ

ቤትዎ ውስጥ ሆነው ከሌሎች ሰዎች ርቀው በመቆየት የቅርብ ጊዜ መመሪያዎችን ይከታተሉ።

ተጨማሪ ይወቁ

ህክምና ያግኙ

የህክምና አማራጮችዎን ለማሰስ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያነጋግሩ።

ተጨማሪ ይወቁ

ለማገገም ድጋፍ ያግኙ

ከ COVID-19 በሚያገግሙበት ጊዜ፣ የምግብ እና የመድሃኒት አቅርቦት፣ የልጅ እንክብካቤ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶችን ያግኙ።

ተጨማሪ ይወቁ

ረዥም COVID

COVID-19 ያለባቸው ሰዎች በበሽታው ከተያዙ በኋላ ከሳምንታት እስከ ዓመታት የሚቆዩ ምልክቶች ሊኖሩዋቸው ይችላል። የ COVID-19 ኢንፌክሽንን በመከላከል ረጅም ኮቪድን ይከላከሉ።

ተጨማሪ ይወቁ

ተጨማሪ መረጃ

የ COVID-19 ምልክቶች፣ ማሳያዎች እና መከላከያ

ዋና ዋና የ COVID-19 ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፦

  • ሳል፣ የትንፋሽ ማጠር ወይም የመተንፈስ ችግር፣ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ የጡንቻ ህመም፣ የጉሮሮ መቁሰል፣ አዲስ ጣዕም ወይም ሽታ የመለየት ችግር። ሌሎች ብዙም ያልተለመዱ ምልክቶች ማቅለሽለሽን፣ ማስታወክን ወይም ተቅማጥን ያካትታሉ።
  • የሚከተሉትን የ COVID-19 የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ምልክቶች ካዩ ወደ 911 ይደውሉ፦
    • ለመተንፈስ መቸገር
    • ቋሚ የደረት ህመም ወይም ግፊት
    • በድንገት መደናገር
    • መንቃት ወይም ነቅቶ መቆየት አለመቻል
    • በቆዳ ቀለም ላይ በመመርኮዝ ፈዛዛ፣ ግራጫ ወይም ሰማያዊ ቀለም ያለው ቆዳ፣ ከንፈር ወይም የጥፍር ግርጌ
  • ስጋት ውስጥ ያሉ ቡድኖች እነማን ናቸው?
    • በዕድሜ የገፉ ሰዎች፣ በማንኛውም ዕድሜ ላይ ያሉ ሥር የሰደደ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች እና እርጉዝ እናቶች ለ COVID-19 ከባድ ህመም ሊጋለጡ ይችላሉ።

እራሴን እና ቤተሰቤን እንዴት መጠበቅ እችላለሁ?

  • ብቁ ሲሆኑ ክትባቱን እና ማጠናከሪያ ክትባቶችን ይከተቡ።
  • ከታመሙ በቤት ይቆዩ።
  • ጭንብል ይልበሱ እና በሰዎች በተጨናነቁ የህዝብ ቦታዎች ሲሄዱ ከሌሎች ሰዎች ስድስት ጫማ (ሁለት ሜትር) ርቀት ይጠብቁ።
  • ሕዝብ የተሰበሰበባቸውን እና በቂ አየር የሌለባቸውን ቦታዎች ያስወግዱ።
  • እጅዎን ብዙ ጊዜ ይታጠቡ ወይም የእጅ ሳኒታይዘር ይጠቀሙ።
  • ሳልዎን እና ማስነጠስዎን በክርኖ ወይም በሶፍት ወረቀት ይሸፍኑ።
  • ፊትዎን፣ አፍዎን፣ አፍንጫዎን ወይም አይንዎን አይንኩ።
  • በቤትዎ ውስጥ ያሉ አካላትን ያጽዱ።
  • የ COVID-19 ምልክቶች ካለብዎ በጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ይታዩ።
ሱቆችን እና የህዝብ ቦታዎችን በጣም ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ይጎብኙ

ከቤት ከመውጣትዎ በፊት እና በኋላ እንዲሁም ከቤት ሳይወጡ እራስዎን እና ሌሎችን ለመጠበቅ ሊያስታውሷቸው የሚችሏቸው ብዙ ነገሮች አሉ።

ከመውጣትዎ በፊት፦

  • ከታመሙ በተቻለ መጠን ወደ ሱቅ ወይም ሌላ የህዝብ ቦታ አይሂዱ። የሚፈልጉትን እቃዎች አንድ የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ እንዲወስድልዎ ያድርጉ።
  • ግሮሰሪዎችን፣ መድሃኒቶችን እና ሌሎች እቃዎችን ወደ ቤትዎ እንዲያመጡልዎት በኦንላይን ማዘዝን ግንዛቤ ውስጥ ያስገቡ።
  • ከተቻለ ከከፍተኛ ፍሰት ካለበት ሰዓት ውጭ ወደ መደብሩ መሄድን ግንዛቤ ውስጥ ያስገቡ።
  • ከቤት ከመውጣትዎ በፊት እጅዎን ይታጠቡ።

ሰዎች በሚበዙበት ቦታዎች በቤት ውስጥ ሲሆኑ፦

  • አፍንጫዎን እና አፍዎን የሚሸፍን ጭምብል ያድርጉ።
  • በፍተሻ ሰልፍ ውስጥ ጨምሮ በእራስዎ እና በሌሎች መካከል ቢያንስ ስድስት ጫማ (ሁለት ሜትር) ርቀት ይኑርዎት።
  • በሚያስሉበት ወይም በሚያስነጥሱበት ጊዜ ይሸፍኑ።
  • ፊትዎን አይንኩ።
  • ገበያ ወጥተው ከሆነ የጋሪ እጀታውን ወይም የገቢያ ቅርጫትዎን ለማጽዳት የእጅ ሳኒታይዘር ወይም ፀረ ተባይ ማጥፊያ ይጠቀሙ።

ወደ ቤት ሲመለሱ፦

  • የፊት ጭምብል ጨርቁን ይጠቡ እና በጥንቃቄ ያስቀምጡት። ሊጣል የሚችል ጭምብል ይጣሉት።
  • እጆችዎን ይታጠቡ።
  • የምግብ ደህንነት ልምዶችን ይተግብሩ። የምግብ ምርቶችን በሳኒታይዘር አያጽዱ። እንደ ሁልጊዜው ፍራፍሬዎች እና አትክልቶችን ይጠቡ።
እርግዝና፣ ልጆች እና COVID-19

እርጉዝ ከሆኑ ምን ማወቅ እንዳለብዎት

  • እርጉዝ ወይም በቅርብ ያረገዙ ሰዎች እርጉዝ ካልሆኑ ሰዎች ጋር ሲነጻጸር ለ COVID-19 ከባድ ህመም የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው።
  • በእርግዝና ወቅት በ COVID-19 የተያዙ ሰዎች በተጨማሪም ያለ ጊዜ ለሚመጣ ምጥ (ከ 37 ሳምንታት በፊት የመውለድ) እና የሞተ ልጅ የመወለድ እድላቸው ከፍ ያለ እና ለሌሎች የእርግዝና ችግሮች የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው።
  • እርጉዝ ወይም በቅርብ ጊዜ ያረገዙ ሰዎች እናእነሱ የሚያገኟቸው ሰዎች ከ COVID-19 ስርጭት እራሳቸውን ለመከላከል እነዚህን እርምጃዎች መውሰድ አለባቸው፦
    • ክትባት ይከተቡ እና የማጠናከሪያ ዶዝዎን ይውሰዱ።
    • ማስክ ያድርጉ።
    • ከሌሎች ስድስት ጫማ ርቀት ይራቁ እንዲሁም የተጨናነቁ እና በደንብ አየር የማይገባባቸውን ቦታዎች ያስወግዱ።
    • በሽታውን ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳያስተላልፉ ምርመራ ያድርጉ።
    • እጅዎን በተደጋጋሚ ይታጠቡ እና ሳልዎን ይሸፍኑ እንዲሁም በክርንዎ ወይም በቲሹ ላይ ያስነጥሱ።
    • ዘወትር ቤትዎን ያጽዱና ከጀርም ነጻ ያድርጉ።
    • ጤናዎን በየቀኑ ይከታተሉ።
    • ስለ እርግዝናቸው ስጋቶች ካላቸው፣ ቢታመሙ ወይም COVID-19 አለብኝ ብለው ካሰቡ ወዲያውኑ ወደ ጤና እንክብካቤ አቅራቢያቸው ይደውሉ።

እርግዝና እና የ COVID-19 ክትባት

  • ለእርጉዝ፣ ጡት ለሚያጠቡ፣ ለማርገዝ ለሚሞክሩ ወይም ለወደፊቱ ለሚያረግዙ ሰዎች ለ COVID-19 መከተብ ይመከራል።
  • በእርግዝና ወቅት ለ COVID-19 የሚሰጡ ክትባቶች ደህንነት እና ውጤታማነት ላይ ያለው ማስረጃ እየጨመረ ነው። መረጃው እንደሚያመለክተው በእርግዝና ወቅት የ COVID-19 ክትባቱን የመከተብ ጥቅሞች፣ ከሚታወቁት ወይም ሊከሰቱ ከሚችሉ የክትባት አደጋዎች ይበልጣል።
  • እርጉዝ ግለሰቦች ብቁ ሲሆኑ የ COVID-19 ክትባት ማጠናከሪያ ዶዝ መውሰድ አለባቸው።
  • የ COVID-19 ክትባቶች በእርጉዝ ሴቶች ወይም በልጆቻቸው ላይም ቢሆን፣ የ COVID-19 ኢንፌክሽን አያስከትሉም።
  • በአሁኑ ጊዜ የ COVID-19 ክትባቶችን ጨምሮ ማንኛውም ክትባት በሴቶች ወይም በወንዶች ላይ የመውለድ ችግር እንደሚፈጥር የሚያሳይ ምንም ማስረጃ የለም።
  • እርጉዝ ነዎት፣ ስለ COVID-19 ክትባት ተጨማሪ ጥያቄዎች አሉዎት? የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ወይም MotherToBaby ን ያነጋግሩ፣ ባለሙያዎቻቸው በስልክ ወይም በመወያየት ጥያቄዎችዎን ሊመልሱ ይችላሉ። ይህ ነፃ፣ ሚስጥራዊ አገልግሎት ከሰኞ እስከ አርብ፣ ከ 8 a.m እስከ 5 p.m ይገኛል። በቀጥታ ለመወያየት ወይም ኢሜል ለመላክ MotherToBaby (እንግሊዝኛ እና ስፓኒሽ ብቻ) ይጎብኙ ወይም በ 1-866-626-6847 ላይ ይደውሉ (በእንግሊዘኛ እና በስፓኒሽ ብቻ የሚገኝ ነው)።

ለአራስ ሕፃን COVID-19 ካለባቸው እንዴት እንደሚንከባከቡ

  • እርጉዝ እያሉ COVID-19 ይዟቸው የነበሩ ሴቶች የወለዷቸው ልጆች አብዛኞቹ COVID-19 የለባቸውም።
  • አብዛኞቹ COVID-19 የተገኘባቸው አዲስ የተወለዱ ልጆች ቀላል ወይም ምንም ምልክቶች ያልነበረባቸው ሲሆን አገግመዋል። አንዳንድ አራስ ሕፃናት በ COVID-19 ከባድ ሕመም እንደተያዙ ሪፖርቶች ያመለክታሉ።
  • ለ COVID-19 እራስዎን ከለዩ እና አራስ ልጅ ካለዎት፣ እራስዎን የሚለዩበት ጊዜ እስኪያልቅ ድረስ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ያድርጉ፦
    • ከእርስዎ ጋር ከማይኖሩ ሰዎች እራስዎን ለመለየት ቤት ይቆዩ።
    • ካልተያዙ ሌሎች የቤተሰብዎ ዓባላት ራስዎን ያግልሉ (ይራቁ) እና በጋራ ቦታዎች ላይ ማስክ ያድርጉ።
    • አራስ ልጅዎን እንዲከባከብ ሙሉ በሙሉ የተከተበ እና ለከባድ በሽታ የመጋለጥ እድል የሌለው ጤናማ ተንከባካቢ ያግኙ። ከተቻለ ሌላ ተንከባካቢ ሕፃኑን መመገብ እንዲችል የጡትዎን ወተት ይለቡ። ፎርሙላ የሚሰጡት ከሆነ፣ ጤናማ የሆነው ተንከባካቢ እንዲያዘጋጅ ይጠይቁዋቸው።
    • እራስን የመለየቱ ጊዜ ከማብቃቱ በፊት አራስ ልጅዎን መንከባከብ ካለብዎት፣ ልጅዎን በሚይዙበት ወይም በሚመግቡበት ጊዜ ጭምብል ማድረግን ጨምሮ የሚመከሩ ጥንቃቄዎችን ይከተሉ።
    • አራስ ልጅዎ COVID-19 ምልክቶች እንዳለው እና እንደሌለው ይከታተሉ።
  • አሁን ያለው መረጃ እንደሚያመለክተው የጡት ወተት ቫይረሱን ወደ ሕፃናት የመተላለፍ እድል የለውም። የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የ COVID-19 ክትባት የተከተቡ ሰዎች ፀረ እንግዳ አካላት መከላከያን በጡት ወተት በኩል ወደ ልጃቸው ያስተላልፋሉ። COVID-19 ካለብዎት እና ጡት ለማጥባት ከወሰኑ፦
    • ከማጥባትዎ በፊት እጅዎን ይታጠቡ።
    • ጡት በሚያጠቡበት ወቅት እና ከልጅዎ በስድስት ጫማ (ሁለት ሜትር) ርቀት ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ ጭምብል ያድርጉ።

የ Perinatal Support Washington የእርዳታ ስልክ ለሁሉም አዲስ እና ለሚጠባበቁ ወላጆች ወይም ለሚወዷቸው ሰዎች፣ የአእምሮ ጤና መረጃ እና ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ይገኛል። ለ Perinatal Support Washington የእርዳታ ስልክ በ 1-888-404-7763 ላይ ይደውሉ ወይም የ Perinatal Support ድህረ ገጽን ይጎብኙ (እንግሊዝኛ ብቻ)። የጽሑፍ መልዕክት ይላኩ ወይም በ warmline@perinatalsupport.org ኢሜል ያድርጉ።

እርዳታ ማግኘት አስፈላጊ ነው። የእርዳታ ስልክ መስመር ከሰኞ እስከ አርብ፣ ከ 9 a.m እስከ 4:30 p.m በቀጥታ ይነሳል (በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽ ብቻ)። በምሽቶች እና ቅዳሜና እሁድ ላይ፣ እባክዎን መልዕክት ያስቀምጡ፤ አንድ ሰው በ 1-12 ሰዓታት ውስጥ ጥሪዎን ይመልሳል። የድጋፍ መስመሩ በማህበራዊ ሠራተኞች፣ ፈቃድ ባላቸው ቴራፒስቶች፣ ወይም ከወሊድ በኋላ ድብርት ወይም ጭንቀት ባጋጠማቸው ወላጆች የተሟላ ነው።

ራስዎን እና ቤተሰብዎን ይንከባከቡ

Washington Listens፦ ስለ COVID-19 ጭንቀት ከአንድ ሰው ጋር መነጋገር ከፈለጉ ለ Washington Listens በ 1-833-681-0211 ይደውሉ። ሁልጊዜ ከሰኞ እስከ አርብ ከ 9 a.m እስከ 9 p.m የሚያናግሩት ሰው ያለ ሲሆን ቅዳሜና እሁድ ከ 9 a.m እስከ 6 p.m ድረስ TTY እና የቋንቋ መዳረሻ አገልግሎቶች ይገኛሉ። ተጨማሪ መረጃ በእኛ የአእምሮ ጤና እና ስሜታዊ ደህንነት ገጽ (እንግሊዝኛ ብቻ) ላይ ይገኛል።

  • ስለ ወቅታዊው ወረርሽኝ ሁኔታ እና ተጨማሪ ምክሮች ከታመኑ የሚዲያ አውታሮች፣ የአካባቢ እና የህዝብ ጤና ኤጀንሲዎች እንዲኡም ከህዝብ ጤና ድረ-ገጾች ወቅታዊ መረጃ ጋር በደንብ ይወቁ።
  • እንደ ስልክ ቁጥሮች፣ ድረ ገጾች እና የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎች ያሉ የማህበረሰቡን ሀብቶች ዝርዝር ያዘጋጁ። ትምህርት ቤቶችን፣ ዶክተሮችን፣ የህዝብ ጤና ድርጅቶችን፣ ማህበራዊ አገልግሎቶችን፣ የማህበረሰብ የአእምሮ ጤና ጣቢያዎችን እና የስልክ መስመሮችን መጨመር ይችላሉ።
  • በስልክ ወይም በኦንላይን አገልግሎቶች ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር እንደተገናኙ ይቆዩ።
  • መሰረታዊ የጤና አቅርቦቶች (እንደ ሳሙና፣ አልኮል ያለው የእጅ ሳኒታይዘር፣ ሶፍቶች፣ ቴርሞሜትር፣ ትኩሳትን የሚቀንሱ መድሃኒቶች እና የቤት ውስጥ የ COVID-19 መመርመሪያ ኪቶች ያሉ) ይኑርዎት።
  • እርስዎ ወይም የቤተሰብዎ አባላት በመደበኛነት የሚወስዱትን የመድሃኒት አቅርቦት ለማግኘት ይሞክሩ።

ድጋፍ ለቤተሰብዎ ወጣት አባላት

  • ከጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ በስልክ፣ በጽሁፍ፣ በኢሜል ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በማነጋገር ቀጣይ ድጋፍ እና ግንኙነትን ይፈልጉ።
  • ዜናው ልጆቻችሁን የሚያስጨንቅ ከሆነ፣ እረፍት መውሰድዎን አይርሱ። ከኢንተርኔት ወይም ከሌሎች ምንጮች የሚያገኙትን ማንኛውንም መረጃ ግልጽ ለማድረግ ከእነሱ ጋር ይነጋገሩ።
  • ልጆች ጥያቄዎች እንዲጠይቁ በማበረታታት እና ወቅታዊውን ሁኔታ እንዲያውቁ በመርዳት ድጋፍ ማድረጉ ላይ ያተኩሩ።
  • ስላለዎት ስሜት ይናገሩ እና እውቅና ይስጡ።
  • ሥዕል በመሳል ወይም በሌሎች እንቅስቃሴዎች ስሜቶቻቸውን እንዲገልጹ እርዷቸው።
  • ማጽናኛ ይስጡ እና ከተለመደው ትንሽ የበለጠ ታጋሽ ይሁኑ።