ረዥም COVID

ረዥም COVID ምንድነው?

በ COVID-19 የተያዙ ሰዎች ምልክቶችን እና የረዥም ጊዜ ተጽዕኖዎችን ማየታቸውን የሚቀጥሉ ሲሆን ይህም "ረዥም COVID" ወይም "ድህረ-COVID የበሽታ ምልክቶች" ይባላል። ስለ ረዥም COVID ገና ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም። ረዥም COVID ላይ የሚሰሩ ጥናቶች በቀጠሉ ቁጥር መማራችንን እንቀጥላለን።

የረዥም COVID ምልክቶች

በረዥም COVID የተያዙ ሰዎች ከተያዙ በኋላ ለሳምንታት፣ ለወራት ወይም ለዓመታት ሊቆዩ የሚችሉ የተለያዩ ምልክቶች ሊኖራቸው ይችላል።

ምልክቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፣ ነገር ግን በእነዚህ ብቻ አይወሰኑም፦

  • የድካም ስሜት፣ በተለይ ከአዕምሯዊ ወይም ከአካላዊ ስራ በኋላ
  • ትኩሳት
  • ለመተንፈስ መቸገር
  • ሳል
  • የደረት ህመም
  • ማሽተት እና/ወይም ጣዕም ላይ ለውጥ
  • ለማሰብ ወይም ትኩረት ለማድረግ መቸገር ወይም "የአዕምሮ ጭጋግ"
  • የራስ ምታት
  • የሆድ ህመም
  • የወር አበባ ዑደቶች ላይ ለውጥ ማየት

በረዥም COVID ማን ሊያዝ ይችላል?

ማንኛውም በ COVID-19 የተያዘ ሰው ረዥም COVID ሊይዘው ይችላል። በጣም ከባድ የ COVID-19 ምልክቶች ይታዩባቸው በነበሩ በተለይም ሆስፒታል መተኛት አስፈልጓቸው የነበሩ ሰዎች ላይ ይበልጥ የተለመደ ነው። በ COVID-19 በተያዙበት ወቅት ወይም ከዛ በኋላ ባለ ብዙ ስርዓት መቆጣት የበሽታ ምልክት አጋጥሟቸው የነበሩ ሰዎች በረዥም COVID ለመያዝ ከፍተኛ ስጋት ላይ ሊሆኑ ይችላሉ።  ሴቶች፣ በዕድሜ የገፉ አዋቂዎች፣ መሰረታዊ የጤና ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች እና ያልተከተቡ ሰዎች በረዥም COVID ለመያዝ የበለጠ ዕድል ያላቸው ይመስላል። እንዲሁም ብዙ ጊዜ በ COVID-19 የተያዙ ሰዎችም ረዥም COVIDን ጨምሮ የበለጠ የጤና ስጋቶች ሊኖራቸው ይችላል።  

ረዥም COVIDን መከላከል

የ COVID-19 ኢንፌክሽንን መከላከል ረዥም COVIDን ለመከላከል ምርጡ መንገድ ነው። እጅዎትን በመታጠብ፣ ሰው በተሰበሰበበት ቦታ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ፣ ሲታመሙ ቤት በመቆየት፣ እና የሚመከሩ ክትባቶችን እና ማጠናከሪያ ዶዞችን በመውሰድ እራስዎን እና ሌሎችን ከ COVID-19 ይጠብቁ።

ተከትበው ነገር ግን COVID-19 የያዛቸው ሰዎች ካልተከተቡ ሰዎች ይልቅ በረዥም COVID የመያዝ እድላቸው አነስተኛ ነው።

የ COVID-19 ክትባት ስለመውሰድ የበለጠ ይወቁ

ረዥም COVID ን መመርመር

ረዥም COVID ን መመርመር አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ታማሚዎች ምልክቶቹን ለማብራራት ሊያስቸግራቸው ይችላል። ምርመራውን ለማድረግ ምንም ዓይነት የቤተ ሙከራ ምርመራ ወይም ምስል የለም። አንድ ታማሚ ረዥም COVID ቢኖርበትም እንኳን የሕክምና ምርመራዎች የተለመዱ ውጤቶችን ሊያሳዩ ይችላሉ።

የረዥም COVID ምልክቶችን ሪፖርት ያደረጉ አንዳንድ ሰዎች የ COVID-19 ምልክቶችን አላሳዩም ወይም መጀመሪያ ሲያማቸው የ COVID-19 ምርመራ አላደረጉም። ይህ COVID-19 ይዟቸው እንደነበር ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል እና የረዥም COVID ምርመራን ይከላከላል ወይም ያዘገያል። መጀመሪያ የህመም ስሜት ሲሰማዎት የ COVID-19 ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ሲሆን ይህም በኋላ የረዥም COVID ምርመራ ሲያደርጉ ይረዳዎታል።

ለታካሚ ጠቃሚ ምክሮች፦ ለድህረ-COVID ሁኔታዎች የጤና እንክብካቤ አቅራቢ ቀጠሮዎች (በእንግሊዘኛ)

አዲስ እና ነባር የጤና ሁኔታዎች

የ COVID-19 ኢንፌክሽን የተለያዩ የሰውነት ክፍል ስርዓቶችን ሊጎዳ ይችላል እና አንዳንድ ጊዜ ረዥም COVID ላይ ሚና የሚጫወቱ የራስ ሰር በሽታን የመከላከል ሁኔታዎችን ሊያነሳሳ ይችላል። የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት ተጽዕኖ ስር በወደቁ የሰውነት አካሎች ላይ መቆጣት ወይም የህብረህዋስ ጉዳት ሲፈጥር ራስ ሰር በሽታ የመከላከል ሁኔታዎች ሊከሰቱ ይችላሉ። ይህ ማለት COVID-19 የነበረባቸው ሰዎች እንደ ስኳር ወይም የልብ ሁኔታዎች ያሉ አዳዲስ የጤና ስጋቶች ለማዳበር የበለጠ ዕድል አላቸው ማለት ነው።  ከ COVID-19 ኢንፌክሽን በኋላ እንደ ስኳር እና የልብ ህመም ያሉ ነባር የጤና ሁኔታዎች እንዲሁ ሊባባሱ ይችላሉ።

ረዥም COVID እና የአካል ጉዳተኛ መብቶች

ረዥም COVID አካላዊ እና አዕምሯዊ ጉዳቶችን የሚያስከትል ያስከትላል እና በ Americans with Disabilities Act (ADA፣ የአካል ጉዳተኛ አሜሪካውያን አዋጅ) ስር እንደ አካል ጉዳት ተደርጎ ይወሰዳል። ረዥም COVID ያለባቸው ሰዎች ከአካል ጉዳት መድልዎ ህጋዊ ከለላ አላቸው። ከረዥም COVID ጋር የተገናኙ ውሱንነቶችን ለማካተት ከንግዶች፣ ግዛት፣ እና አካባቢያዊ መንግስቶች ለምክንያታዊ ለውጦች መብት ሊኖራቸው ይችላል።

 የ “ረዥም COVID” እንደ አካል ጉዳት በ ADA ስር መመሪያ (በእንግሊዘኛ)

ረዥም COVID እና እርግዝና

ነፍሰ ጡር ወይም በቅርብ ነፍሰ ጡር የሆኑ ሰዎች በ COVID-19 በጠና የመታመም ዕድላቸው ሰፊ ነው። COVID-19 በእርግዝና እና እያደገ ባለው ሕፃን ላይ ተጽዕኖ የሚያደርጉ ውስብስብነቶችን ሊፈጥር ይችላል።

ረዥም COVID ለምን ያህል ጊዜ እርግዝና ላይ ተፅዕኖ እንደሚያደርግ ገና ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም። The National Institutes of Health (NIH፣ ብሔራዊ የጤና ተቋማት) (በእንግሊዘኛ) ነፍሰ ጡር እያሉ በ COVID-19 ተይዘው የነበሩ ሴቶች እና ልጆቻቸው ላይ የ COVID-19 የረዥም ጊዜ ተጽዕኖዎችን በተመለከተ የ 4-ዓመት ጥናት ያደርጋል።

ረዥም COVID እና ወጣቶች

ወጣቶችም እንዲሁም በረዥም COVID ሊታመሙ ይችላሉ። እንደ ድካም እና ትኩረት ለማድረግ መቸገር ያሉ የረዥም COVID ምልክቶችን እያዩ ያሉ ወጣቶች በት/ቤት እና በሌሎች እንቅስቃሴዎች ላይ ለመሳተፍ ሊቸግራቸው ይችላል። ወጣት ልጆች ምልክቶቻቸውን ለመናገር ሊቸገሩ ይችላሉ።

ረዥም COVID ያለባቸው ልጆች ለልዩ ፍላጎት ትምህርት፣ ጥበቃዎች ወይም ተዛማጅ አገልግሎቶች በ 2 ፌዴራል ህጎች (በእንግሊዘኛ) ስር ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

ወጣቶች የ COVID-19 ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ በወጣቶች ላይ ረዥም COVIDን ለመከላከል ምርጡ መንገድ ነው።

ወጣቶችን ስለመከተብ የበለጠ ይወቁ

ለሐኪሞች መረጃ