አስቸኳይ የጨቅላ ህጻናት የዱቄት ወተቶች ከገበያ መልሶ የመሰብሰብ ጥሪ

Mead Johnson Nutrition በ 12.6 እና በ 19.8 oz የቆርቆሮ ጣሳዎች ውስጥ የሚገኘውን Nutramigen Powder የህጻናት ዱቄት ወተቶች ከገቢያ እንዲሰበሰቡ ማስታውቂያ አውጥቷል። ሌሎች የ Mead Jonson ምርቶች አልተጠቁም።

ከገበያ የሚሰበሰቡ የህጻናት የዱቄት ወተቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • የባች ቁጥሮች፦
    • ZL3FHG (12.6 oz የቆርቆሮ ጣሳዎች)
    • ZL3FMH (12.6 oz የቆርቆሮ ጣሳዎች)
    • ZL3FPE (12.6 oz የቆርቆሮ ጣሳዎች)
    • ZL3FQD (12.6 oz የቆርቆሮ ጣሳዎች)
    • ZL3FRW (19.8 oz የቆርቆሮ ጣሳዎች)
    • ZL3FXJ (12.6 oz የቆርቆሮ ጣሳዎች)
  • UPC ኮድ፦
    • 300871239418
    • 300871239456
  • የአገልግሎት ማብቂያ ቀን፦ 1 Jan 2025

የዱቄት ወተት ቈርቈሮ ጣሳ ቁጥሮችን ያጣሩ፦

  • ከገበያ ላይ እንዲሰበሰብ የታዘዘ ከሆነ የዱቄት ወተቱን ለልጅዎ አይመግቡ።
  • ሁሉም እንዲሰበሰብ የታዘዙ ጣሳዎች ላይ “አይጠቀሙ” የሚል ምልክት ያድርጉ።
  • በዱቄት ወተት እንዲለወጡ፣ እንዲሰበሰቡ የታዘዙትን የቆርቆሮ ጣሳዎች ይያዙ።

እንዲሰበሰብ የታዘዘውን የህጸናት የዱቄት ወተት እንዴት እንደሚለውጡ፡-

የህጻናት ዱቄት ወተቱን ወደ መደብሩ ለመመለስ ይሞክሩ፦

  • እያንዳንዱ መደብር እንደሚያቀርበው ነገር የተለየ ነው።
  • አንዳንድ መደብሮች እንዲመለስ የታዘዘውን የህጻናት ዱቄት ወተት መልሰው ወስደው ልውውጥ፣ የስቶር ክሬዲት ሊሰጡ ወይም ገንዘብ ተመላሽ ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህ አማራጭ ካልዎት ማንኛውንም የህፃናት የዱቄት ወተት ለመግዛት ያንን ክሬዲት ወይም ተመላሽ የተደረገ ገንዘብ መጠቀም ይችላሉ።
  • መደብሩ የህጻናት ዱቄት ወተቱን የማይለውጥ ከሆነ ከዚህ በታች ቁጥር 2 ይመልከቱ።

ወደ እርስዎ WIC ክሊኒክ በሚከተለው ይደውሉ፦

  • በመደብሮችዎ ውስጥ የትኛው የWIC የህጻናት ዱቄት ወተት እንደሚገኝ ይመልከቱ፤
  • እንደ አስፈላጊነቱ የህጻናት ዱቄት ወተት ጥቅማጥቅሞችን ለመተካት ወይም ለመለወጥ ወደ ክሊኒኩ ይደውሉ፤
  • ክሊኒክዎን ማግኘት ካልቻሉ፣ ለስቴቱ በ 1-800-841-1410 ላይ ይደውሉ። ከሰኞ እስከ አርብ ከ 8am እስከ 5pm።

Mead Johnson ን በ 866-534-9986 ወይም በኢሜይል በ consumer.relations@rb.com ያነጋግሩ እና ይህ ምርት ተጎድቶ እንደሆነ ለማረጋገጥ ይረዱዎታል። ማንኛውም ስጋት ካለዎት የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያነጋግሩ።