የ COVID-19 ሕክምናዎች

ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ያደረጉ እና በጠና የመታመም ዕድላቸው ከፍ ያለ ሰዎች ካሉ ከሚገኙ የ COVID-19 ሕክምናዎች (መድሃኒቶች) ሊጠቀሙ ይችላሉ። እነዚህ ሕክምናዎች ከባድ ሕመምን፣ ሆስፒታል መግባትን/መተኛትን እና በ COVID-19 የሚከሰት ሞትን ለመከላከል ይረዳሉ። አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ እና ለበለጠ አደጋ የተጋለጡ ከሆነ ህክምናዎች ቀደም ብለው መጀመር ስላለብዎት የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ወዲያውኑ ያነጋግሩ። የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ የትኛው የ COVID-19 መድሃኒት አማራጭ ለእርስዎ እንደሚሻል ለመወሰን ይረዳል።

የ COVID-19 ሕክምናዎች/መድሀኒቶች የመከላከል ምትክ አይደሉም። አሁንም ቢሆን ብቁ የሆኑ ሁሉ እንዲከተቡ እና የ COVID-19 ስርጭትን ለመከላከል ሌሎች እርምጃዎችን እንዲወስዱ ይመከራል።

የሞኖክሎናል አንቲቦዲ ህክምናዎች ምንድን ናቸው?

ፀረ እንግዳ አካላት እንደ COVID-19 ን የሚያመጣው ቫይረስ ያሉ የሰው አካል ቫይረሶችን ለመዋጋት የሚያመርታቸው ፕሮቲኖች ናቸው። በላብራቶሪ ውስጥ የተሰሩ ፀረ እንግዳ አካላት በሰውነትዎ ውስጥ ያለውን የቫይረስ መጠን ለመገደብ እንደ ተፈጥሯዊ ፀረ እንግዳ አካላት ይሠራሉ። ሞኖክሎናል ፀረ እንግዳ አካላት ተብለው ይጠራሉ። የከባድ የ COVID-19 ህመም ስጋት ካለብዎት እና ለ COVID-19 ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ካልዎት ወይም ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ካለው ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ከነበርዎት፣ የሞኖክሎናል አንቲቦዲ (mAb) ህክምናን ከግምት ውስጥ ሊያስገቡ ይችላሉ። እድሜዎን፣ የጤና ታሪክዎን፣ እና ለምን ያክል ጊዜ ምልክቶች እንደነበርዎት መሰረት በማድረግ COVID-19 ን ለማከም ለ mAb ህክምና (bebtelovimab) ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

የ COVID-19 የቅድመ-ተጋላጭነት ፕሮፒላክሲስ ምንድነው?

Pre-Exposure Prophylaxis (PrEP፣ ቅድመ-ተጋላጭነት ፕሮፒላክሲስ) ቫይረስ ከሰው ህዋሳት ጋር ከመጣበቅ እና ከመግባት ለመከላከል የተዘጋጀ መድሃኒት ነው። እንደሌሎች በአሁኑ ጊዜ ከሚገኙ ሞኖክሎናል ፀረ እንግዳ አካላት በተለየ፣ Evusheld አንድ ሰው ለ COVID-19 ከመጋለጡ በፊት ለመከላከል ወይም ለመከላከል ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል የተፈቀደለት ረጅም ጊዜ የሚሰራ ፀረ እንግዳ አካላት ነው። Evusheld በ COVID-19 ምክንያት ለሚነሱ ምልክቶች ሕክምና አይሰጥም እና በ COVID-19 ለተያዘ ሰው ከተጋለጡ በኋላ አይሰጥም፤ የሚሰጠው ከመጋለጥ በፊት ኢንፌክሽንን ለመከላከል ነው።

በአፍ የሚወሰዱ ጸረ-ቫይረስ መድኀኒቶች ምንድን ናቸው?

በአፍ የሚወሰድ የፀረ-ቫይረስ ህክምና SARS-CoV-2 ቫይረስ (COVID-19 ን የሚያመጣው ቫይረስ) በሰውነትዎ ውስጥ እንዳይባዛ በማድረግ፣ በሰውነትዎ ውስጥ ያለውን የቫይረሱን መጠን በመቀነስ ወይም በሽታ የመከላከል ስርዓትዎን በማገዝ ሰውነትዎ COVID-19 ን እንዲዋጋ ይረዳል። ሕክምና በማግኘት፣ ምልክቶቹ ያን ያህል አሳሳቢ ያልሆኑ እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል ደግሞም ሕመምዎ እየተባባሰ እንዳይሔድ እና ሆስፒታል የመተኛት እድሎንም ይቀንሰዋል። ለ COVID-19 የፀረ-ቫይረስ ሕክምናዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ ምልክቶች ላላቸው፣ ሆስፒታል ላልሆኑ፣ ለአምስት ቀናት ወይም ከዚያ በታች ምልክቶች ላጋጠማቸው እና ለከባድ ሕመም ከፍተኛ ተጋላጭ ለሆኑ ታካሚዎች ይገኛል።

የደም ሥር (IV) ፀረ-ቫይረስ ምንድን ናቸው?

Remdesivir (እንግሊዝኛ ብቻ) በ Food and Drug Administration (FDA፣ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር) ተቀባይነት ያለው እና በአሁኑ ጊዜ በ Washington State Department of Health (WADOH፣ የዋሺንግተን ግዛት የጤና መምሪያ) የማይሰራጭ የፀረ-ቫይረስ መድሃኒት ነው። ቫይረሱን በራሱ ቅጂዎች እንዳይሰራ (መባዛትን) በመከልከል ይሰራል። Remdesivir በጊዜ ሂደት በደም ሥር ውስጥ በሚገኝ መርፌ የሚሰጥ ሲሆን ይህም IV infusion ይባላል።

Remdesivir ሆስፒታል ላልሆኑ ጎልማሶች እና ለከባድ COVID-19 በሽታ ከፍተኛ ተጋላጭነት ላላቸው ህጻናት ህክምና ተፈቅዷል። ኤፕሪል 25፣ 2022 FDA ይህንን ማፅደቂያ በማስፋት ቢያንስ 3 ኪሎ ግራም (6.6 ፓውንድ ገደማ) የሚመዝኑ እና ለከባድ በሽታ የተጋለጡትን ቢያንስ 28 ቀናት የሆናቸው ህጻናትን በማካተት remdesivir ን ለመጀመሪያ ጊዜ በ FDA የተፈቀደለት ከ12 ዓመት በታች ያሉ የህጻናት ህክምና አድርጎታል።

Remdesivir በተቻለ ፍጥነት መጀመር አለበት፣ እና ምልክቱ በጀመረ በሰባት ቀናት ውስጥ ከፍተኛ ስጋት ያላቸው ሰዎች ምልክት ካላቸው እና ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ ከጤና እንክብካቤ ሰጪያቸው ጋር መገናኘት አስፈላጊ ነው። ሕክምናው በተከታታይ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠውን የ IV መርፌዎች በቀን አንድ ጊዜ ይሰጣል።

ሁሉም የጤና እንክብካቤ መስጫ ተቋማት የተመላላሽ ታካሚ remdesivir ሕክምናን ሊሰጡ አይችሉም - ሕመምተኞች የሕክምና አማራጭ ሊሆን እንደሚችል ለማየት የጤና እንክብካቤ አቅራቢያቸውን ማነጋገር አለባቸው።

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

mAbs በ COVID-19 የተያዙ ሰዎችን እንዴት ይረዳሉ?

በአሜሪካ Food and Drug Administration (FDA፣ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር) ለአደጋ ጊዜ አገልግሎት የተፈቀደላቸው የMAb ሕክምናዎች ከፍተኛ አደጋ (እንግሊዝኛ እና ስፓኒሽ ብቻ) ላይ ያሉ ሰዎችን ለከባድ የበሽታው ምልክቶች በሚከተሉት ሊረዳቸው ይችላል።

  • ሆስፒታል የመግባት እድልን ይቀንሳሉ
  • ከ COVID-19 በተሻለ ፍጥነት ማገገም
የ mAb ህክምናን ማን ሊወስድ ይችላል?

MAb ዎች የተሰሩት ለምከተሉት ሰዎች ነው፦

  • ለ COVID-19 ምርመራ አዎንታዊ ውጤት ላገኙ
  • ለ 10 ቀናት ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ቀላል እና መካከለኛ የሆኑ የበሽታውን ምልክቶች ላዩ
  • በከባድ ሁኔታ የመታመም እድላቸው ከፍተኛ ከሆነ
የሞኖክሎናል ፀረ እንግዳ አካላት ሕክምና ከወሰድኩኩ በኋላ የኮቪድ ክትባት መውሰድ እችላለሁ?

ከ COVID-19 ኢንፌክሽን በኋላ የፓሲቭ ፀረ እንግዳ ሕክምና (ሞኖክሎናል ፀረ እንግዳ ቴራፒ ወይም ኮንቫልሰንት ፕላዝማ) ከተቀበሉ፣ ሕክምናውን ከጨረሱ በኋላ በማንኛውም ጊዜ የ COVID-19 ክትባት መውሰድ ይችላሉ። ግለሰቦች የፓሲቭ ፀረ እንግዳ ህክምና ካበቃ በኋላ ለ90 ቀናት መጠበቅ አይጠበቅባቸውም። 

ለፓሲቭ ፀረ እንግዳ ህክምና ብቁ መሆንን በተመለከተ ላሉ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ከአቅራቢዎ ጋር ያማክሩ። 

የሞኖክሎናል ፀረ እንግዳ አካላት ህክምና እንዳገኘሁ እንዴት ማሳየት እችላለሁ?

የ mAb ህክምናን ያካሄደው የህክምና አቅራቢ ህክምናውን መቼ እንደወሰዱ የሚጠቁሙ ሰነዶችን ሊሰጥዎት ይችላል።

የአፍ ፀረ-ቫይረስ መድሃኒቶችን ለመቀበል ብቁ የሆነው ማነው?

Paxlovid፦ ጎልማሶች እና የህፃናት ህመምተኞች (እድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆነ ቢያንስ 88 ፓውንድ/40 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ) ሆስፒታል መተኛትን ወይም ሞትን ጨምሮ ወደ ከባድ COVID-19 የመሸጋገር ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።

Molnupiravir፦ ሆስፒታል መተኛትን ወይም ሞትን ጨምሮ ወደ ከብድ የ COVID-19 ህመም የመሸጋገር ዕድላቸው ከፍተኛ የሆነባቸው እና በ Food and Drug Administration (FDA፣ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር) የተፈቀዱ አማራጭ የ COVID-19 ሕክምና አማራጮች ተደራሽ አይደሉም ወይም በህክምና ምርመራ ተገቢ አይደሉም

ህክምናው በ Medicaid/Children's Health Insurance Program (CHIP) የተሸፈነ ነው?

አዎ። Medicaid/Children's Health Insurance Program (CHIP፣ የልጆች የጤና መድህን ፕሮግራም) የአስተዳደሩን ክፍያ (በእንግሊዘኛ ብቻ) ለ mAbs ሕክምናዎች እየሸፈነ ነው። የክትባት አስተዳደር ክፍያ አንድ የጤና አገልግሎት አቅራቢ ህክምናውን እንዲሰጥዎት የሚከፈል ክፍያ ነው። ለአብዛኛዎቹ mAb ቦች፣ የምርቱ ዋጋ በፌዴራል መንግሥቱ በራሱ ተሸፍኗል።

ኢንሹራንስ ከሌለኝ፣ የ COVID-19 ሕክምና ማግኘት እችላለሁ?

በፌዴራል መንግሥት የሚገዙ የ COVID-19 ሕክምናዎች ለታካሚዎች ያለ ምንም ወጪ ይሰጣሉ። ነገር ግን፣ አቅራቢዎች በኢንሹራንስ፣ በታካሚዎች ወይም በፌደራል ፕሮግራሞች የሚሸፈኑ የማከፋፈያ፣ የሕክምና እና የአስተዳደር ክፍያዎች ሊኖራቸው ይችላል። የሕክምና ዘዴዎችን በሚፈልጉበት ጊዜ ምን ዓይነት ሽፋን እንዳለ ለማወቅ እባክዎን ከአገልግሎት አቅራቢዎ ጋር ያማክሩ።

ሰነድ የሌላቸው ግለሰቦች ለ COVID-19 ህክምና ሊያገኙ ይችላሉ?

ሰነድ የሌላቸው ግለሰቦች ከ Alien Emergency Medical Program (ዜጋ ላልሆኑ የድንገተኛ ጊዜ የሕክምና ፕሮግራም) (እንግሊዘኛ ብቻ) ሽፋን ማግኘት ይችላሉ፡-

  • የ COVID-19 ግምገማ እና ህክምናን ለማካተት ብቁ የሆኑ ድንገተኛ አደጋዎች።
  • ቢሮ፣ ክሊኒክ፣ ወይም በቴሌ ጤና ላይ የሚያካትት የምርመራ እና የሕክምና ቅንብሮች።
  • የተፈቀዱ አገልግሎቶች። ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ያደረጉ ግለሰቦች የመድሃኒት እና የመተንፈሻ አገልግሎት ሽፋን ሊኖራቸው ይችላል። አዎንታዊ የ COVID-19 ውጤቶች የክትትል ጉብኝቶች እና መድሃኒቶች የተሸፈኑ ሊሆኑ ይችላሉ

ለ AEM እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

እድሜያቸው ከ 19 እስከ 64 የሆኑ አዋቂዎች፦

ዕድሜያቸው 65 ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ጎልማሶች፣ ዓይነ ስውራን፣ አካል ጉዳተኞች ወይም የረጅም ጊዜ አገልግሎት የሚያስፈልጋቸው፡-

  • መስመር ላይ፡- Washington Connection (እንግሊዘኛ እና ስፓኒሽ ብቻ)
  • ስልክ፡- 1-877-501-2233

ለ COVID-19 ህክምና ያግኙ

Test to Treat (ከምርመራ ወደ ህክምና)  (በእንግሊዘኛ ብቻ) ፕሮግራም ፈጣን እና ቀላል የህይወት አድን የ COVID-19 ህክምናዎችን ያቀርባል። አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ፣ ከጤና እንክብካቤ አቅራቢ ጋር መገናኘት ይችላሉ (ጣቢያ ላይ ወይም በቴሌ ጤና በኩል)፣ እና ብቁ ከሆኑ፣ ለአፍ የጸረ ቫይረስ ሕክምና የሐኪም ማዘዣ ማግኘት እና ይህ ማዘዣ እንዲሞላ ማድረግ ይችላሉ - ሁሉም በአንድ ቦታ።

Test to Treat አመልካችን ይጎብኙ ወይም በ 1-800-232-0233 (TTY 1-888-720-7489) በእንግሊዝኛ፣ በስፓኒሽ፣ እና በሌሎች ከ150 በላይ ቋንቋዎች እርዳታ ለማግኘት ይደውሉ።የጥሪ ማዕከሉ በሳምንት 7 ቀናት ከ 8am እስከ እኩለ ሌሊት ET፣ ክፍት ነው እና በአቅራቢያዎ የሚገኝ ቦታ ለማግኘት ይረዳዎታል።

መድህን ወይም ኢንሹራንስ ለሌላቸው ግለሰቦች ያሉ ግብዓቶች

የ COVID-19 ሕክምና ወይም ሌላ የጤና እንክብካቤ ሽፋን የሚፈልጉ ኢንሹራንስ የሌላቸው ግለሰቦች የሚከተሉትን ማግኘት ይችላሉ፡-

ኢንሹራንስ የሌላቸው ግለሰቦች የሚከተሉት የፌደራል ብቃት ያላቸው የጤና ማዕከላት (FQHCs) አካል በሆኑት በብዙ ክሊኒኮች አገልግሎት መፈለግ ይችላሉ። 

መድኃኒት የሚገኝበትን ቦታ ለማግኘት እርዳታ ያስፈልግዎታል? የ Test to Treat (በእንግሊዘኛ ብቻ) ጣቢያ ለማግኘት ወደ 1-800-232-0233 (TTY 888-720-7489) ይደውሉ።

ተጨማሪ የመረጃ ምንጮች፡-

ተጨማሪ ጥያቄዎችን ለመመለስ የግዛቱ የ COVID-19 የስልክ መስመር አለ።የቀጥታ መስመር መረጃ በ አግኙን ገጽ ላይ አለ።

ስለ COVID-19 ሕክምናዎች ተጨማሪ ለማግኘት የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከልን COVID-19 ህክምናዎች ገጽ ን ይጎብኙ።