ሀገር አቀፍ የህፃናት ዱቄት ወተት እጥረት ለብዙ ቤተሰቦች ውጥረትን ፈጥሯል። እነዚህ መርጃዎች የህፃናቶቻቸውን አመጋገብ ለመደገፍ ምግብ ለማግኘት የሚሞክሩትን ቤተሰቦች መርዳት ይችላሉ። ከታች ያለው መረጃ የመጣው ከ American Academy of Pediatrics (AAP፣ የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ) (በእንግሊዘኛ አያያዥ) ፣ከ U.S. Department of Health and Human Services (የአሜሪካ የጤና እና የሰብዓዊነት አገልግሎቶች መምሪያ (በእንግሊዘኛ አያያዥ) ፣ ከ ዋሺንግተን Women, Infants, and Children(WIC፣ ሴቶች፣ ጨቅላዎች፣ እና ሕፃናት) ፕሮግራም፣ ከ Centers for Disease Control and Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከላት) (በእንግሊዘኛ አያያዥ) ፣ እና ከ U.S. Food and Drug Administration (FDA፣ የአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር) (በእንግሊዘኛ አያያዥ) ነው።
- ለልጄ የህፃናት ዱቄት ወተት ማግኘት ካልቻልኩ ምን ማድረግ አለብኝ?
-
የልጅዎ ሐኪም፣ ነርስ፣ ወይም ክሊኒክ ስለልጅዎ አመጋገብ ምርጥ የመረጃ ምንጭ ነው።ምንም አይነት ስጋቶች ካለዎት እባክዎ ያነጋግሯቸው።
በ WIC ከተሳተፉ፦
የህፃን ዱቄት ወተትዎን ለማግኘት ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለማወቅ የአካባቢዎ የWIC ክሊኒክ (በእንግሊዘኛ አያያዥ) ያግኙ። WIC አሁን ለቤተሰቦች ተጨማሪ ምርጫዎችን ለመስጠት ብዙ አይነት የህፃናት ዱቄት ወተት ያቀርባል። በአካባቢዎ የሚገኘውን ክሊኒክ ማግኘት ካልቻሉ፣ ወደ ክልሉ WIC ቢሮ በ 1-800-841-1410 ከሰኞ እስከ አርብ፣ ከ 8፡00 am – 5፡00 pm ይደውሉ። በተፈቀዱ የ WIC የህፃናት የዱቄት ወተት ላይ ለተጨማሪ መረጃ የዋሺንግተን WIC ድረ ገጽ ን (በእንግሊዝኛ) ይመልከቱ።Basic Food (መሠረታዊ ምግብ) Supplemental Nutrition Assistance Program (SNAP፣ የአጋዥ ምግብ እርዳታ ፕሮግራም) ጥቅማጥቅሞች የመድኃኒት መሸጫ ቤቶችን ጨምሮ በተለያዩ መደብሮች ውስጥ የህፃናት ዱቄት ወተት ለመግዛት ሊያገለግሉ ይችላሉ።በአካል ወይም በመስመር ላይ ለመግዛት ጥቅማጥቅሞቹን መጠቀም ይችላሉ። ለ SNAP ብቁ መሆንዎን ለማወቅ፣ የ Parenthelp123 ድረ-ገጽን (በእንግሊዘኛ) (በእንግሊዝኛ) ይጎብኙ ወይም በ 1-800-322-2588 ይደውሉ።
ሌሎች ቤተሰቦች በሙሉ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦
- ትናንሽ መደብሮችን እና የመድኃኒት መደብሮችን ይመልከቱ ወይም ከስመ ጥር ብራንድ መደብሮች እና የመድኃኒት መደብሮች በመስመር ላይ ይግዙ።
- አምራቾችን በቀጥታ ማነጋገር፦
- የተረጋገጠ የአመጋገብ ወይም የጡት ማጥባት አማካሪ በስልክ፣ በጽሁፍ፣ በፌስቡክ ሜሴንጀር፣ በድር ላይ ውይይት፣ ወይም በቪዲዮ ጥሪ ለማግኘት የ Gerber ን MyGerber Baby Expert (ማይገርበር የልጅ ባለሙያ) (በእንግሊዝኛ) ይጠቀሙ። የበለጠ በቀላሉ ሊገኝ የሚችል ተመሳሳይ ቀመር ለመለየት ሊረዱዎት ይችላሉ።
- ለ Abbott የደንበኛ መስመር ይደውሉ፦ 1-800-986-8540
- የ Abbott ን አስቸኳይ የምርት ጥያቄ ቅጽ (በእንግሊዝኛ) ይጠቀሙ፡ - አስቸኳይ የምርት ጥያቄ በ Abbott በኩል እንዲያቀርቡ የእርስዎን OBGYN ወይም የልጅዎን ሐኪም፣ ነርስ፣ ወይም ክሊኒክ ይጠይቁ።
- የ Mead Johnson/Reckitt ን የደንበኛ አገልግሎት መስመር ይደውሉ፦ 1-800 BABY-123 (222-9123)
- የማህበረሰብ ሃብቶችን ይመልከቱ፦
- በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የ Community Action Agency (CAA፤ማህበረሰብ ድርጊት ኤጀንሲ) (በእንግሊዘኛ) ያግኙ። የእርስዎ ሰፈር CAA የህፃናት ዱቄት ወተት ሊሰጥዎ ወይም የህፃናት ዱቄት ወተት ካላቸው የአካባቢ ኤጀንሲዎች ጋር ሊያገናኝዎት ይችላል።
- ወደ United Way 2-1-1በእንግሊዘኛ(በእንግሊዘኛ) ይደውሉ፡ United Way ላይ ካለው የማህበረሰብ ሃብት ስፔሻሊስት ጋር ለመገናኘት 2–1-1 ን ይጫኑ።ዝቅተኛ ወይም ምንም ወጪ የማይጠይቁ የሕፃናት ዱቄት ወተት እና የሕፃን ምግብ የሚያገኙባቸውን የምግብ ማከማቻዎች እና ሌሎች ቦታዎችን ለማግኘት ሊረዱዎት ይችላሉ።
- የህፃናት ዱቄት ወተት ክምችት እንዳለ ለመጠየቅ ለ አካባቢዎን የምግብ ባንክ (በእንግሊዝኛ) ይደውሉ።
- የልጅዎን ሐኪም፣ ነርስ፣ ወይም ክሊኒክ ስለተለገሰ ወተት ይጠይቁ። በሐኪም ማዘዣ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የተለገሰ የጡት ወተት ከ Northwest Mother’s Milk Bank (በእንግሊዘኛ) ማግኘት ይችሉ ይሆናል።
- በዚህ አስቸኳይ ሁኔታ፣ የ American Academy of Pediatrics (የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ)፣ ልጅዎ ልዩ የህፃናት ዱቄት ወተት ካላስፈለገው በስተቀር አብዛኞቹ ሕፃናት ለተገኘው ማንኛውም የህፃናት ዱቄት ወተት፣ የመደብር ብራንዶችን ጨምሮ ቢቀይሩ ምንም ችግር የለውም ብሏል።ልጅዎ በአንድ የተወሰነ በከፍተኛ ሃይድሮላይዝድ (በእንግሊዘኛ) ወይም በአሚኖ አሲድ ላይ የተመሰረተ የህፃናት ዱቄት ወተት እንደ Elecare ያሉ ዱቄት ወተቶች የሚጠቀም ከሆነ፣ ስለሌሎች አማራጮች የልጅዎን ሐኪም፣ ነርስ፣ ወይም ክሊኒክ ይጠይቁ።
- OBGYNዎን ወይም የልጅዎን ሐኪም፣ ነርስ፣ ወይም ክሊኒክ ሊሰጡ የሚችሉ የህፃናት የዱቄት ወተት ናሙናዎች በእጃቸው ካሉ ይጠይቁ።
- ለረዘመ ጊዜ እንዲቆይ ተጨማሪ ውሃ ወደ ዱቄት ወተት ማከል ምንም ችግር የለውም?
-
አይ። በማሸጊያው ላይ ያሉትን መመሪያዎች እና የልጅዎ ሐኪም፣ ነርስ፣ ወይም ክሊኒክ የሚሰጠውን መረጃ ሁልጊዜ መከተል አለብዎት። የቀጠነ ዱቄት ወተት አደገኛ ስለሆነ ልጅዎ በቂ ምግብ እንዳያገኝ ሊያደርግ ይችላል።ያ ከባድ የጤና ችግሮች ሊያስከትል ይችላል።
- በቤት ውስጥ የሚሰራ የዱቄት ወተት ማዘጋጀት እችላለሁ?
-
የ American Academy of Pediatrics የራስዎን የሕፃን ዱቄት ወተት እንዳይሰሩ አጥብቆ ይመክራል። በቤት ውስጥ የተሰራ ዱቄት ወተት ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም እና ለልጅዎ በቂ ምግብ አይሰጥም። አንዳንድ የጨቅላ ሕጻናት ሞት በቤት ውስጥ ከተዘጋጁ ዱቄት ወተቶች ጋር ተያይዟል።
- ከውጪ የሚመጣ የሕፃናት ዱቄት ወተት ማግኘት እችላለሁ?
-
የ U.S. Food and Drug Administration (FDA) ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የህጻናት ዱቄት ወተት አቅርቦትን ለማሳደግ እርምጃዎችን ወስዷል።በ ሜይ 16፣ የደህንነት እና የአመጋገብ ደረጃዎችን የሚያሟሉ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ወደ አሜሪካ ሊደርሱ እንደሚችሉ FDA ተናግሯል (በእንግሊዘኛ)።
- የህፃን ልጆች ዱቄት ወተት ለጨቅላ ህፃኔ መመገብ እችላለሁ?
-
የ American Academy of Pediatrics (AAP) የልጆች የህፃን ዱቄት ወተት ለጨቅላ ህፃናት አይመክርም። ነገር ግን AAP ሌላ ምርጫ ከሌለዎት፣ የልጆች የህፃን ዱቄት ወተት ወደ አንድ አመት ለሚጠጉ ህጻናት ለጥቂት ቀናት ለመጠቀም ደህና ነው።
- በጊዜያቸው ላልተወለዱ ህፃናት የሚሰራ የዱቄት ወተት ጊዜውን ጠብቆ/ጨርሶ ለተወለደው ህፃኔ መስጠት እችላለሁ?
-
ለጥቂት ሳምንታት ሌላ ነገር የማይገኝ ከሆነ የ American Academy of Pediatrics (AAP) በጊዜያቸው ላልተወለዱ ህፃናት የሚሰራ የዱቄት ወተት ጊዜያቸውን ጨርሰው ለተወለዱ ህፃናት መስጠት ደህና ነው።
- በህፃናት ዱቄት ወተት ምትክ ለህፃኔ የላም ወተት መስጠት እችላለሁ?
-
የ American Academy of Pediatrics ከ 6 ወር በላይ ለሆኑ ህፃናት መደበኛ (ልዩ ያልሆነ) ዱቄት ወተት ለሚወስዱ ህፃናት፣ ሙሉየላም ወተት ለአጭር ጊዜ (ከሳምንት ያልበለጠ) አማራጭ ሊሆን ይችላል ይላል። ቡድኑ ተስማሚ እንዳይደለ እና ከአንድ ሳምንት በላይ መሰጠት እንደሌለበት ይናገራል።የላም ወተት በሚሰጡበት ጊዜ፣ ልጅዎ የደም ማነስ(በእንግሊዘኛ) ለመከላከል በቂ አይረን ማግኘቱን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።እንደ የታሸጉ የሕፃን ምግብ ሥጋዎች ወይምበአይረን የበለጸጉ እህሎች ያሉ ብዙ አይረን ያላቸውን ጠጣር ምግቦችለልጅዎ መመገብ እንዲሁ አስፈላጊ ነው። በእጥረቱ ጊዜ ለአንድ ሳምንት ለልጅዎ ሙሉ የላም ወተት መስጠት ካስፈለግዎት፣ከልጅዎ ሐኪም፣ ነርስ፣ ወይም ክሊኒክ ጋር ይነጋገሩ።
- የፍየል ወተት ለጨቅላ ህፃኔ መመገብ እችላለሁ?
-
በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የፍየል ወተት ለህፃናት አይፈቀድም። ይሁን እንጂ፣ አንዳንድ አገሮች ከፍየል የተሠሩ የሕፃናት የዱቄት ወተቶችን አጽድቀዋል። በዚህ የእጥረት ወቅት የ U.S. Food and Drug Administration እነዚያን ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ሊፈቅድ ይችላል።
- ለህፃኔ የአትክልት ወተት መስጠት እችላለሁ?
-
- የ American Academy of Pediatrics (AAP) ከአንድ ዓመት እድሜ ለሚያንሱ ህፃናት ወይም የተለየ የህፃን ዱቄት ወተት ለሚፈልጉ ህፃናት አማራጭ ወተቶችን አይመክርም። በድንገተኛ ጊዜ፣ ወደ አንድ አመት ለሚጠጋ ህጻን ለጥቂት ቀናት የአኩሪ አተር ወተት መስጠት ይችላሉ፣ ነገር ግን የአኩሪ አተር ወተቱ ፕሮቲን እና ካልሲየም ሊጨመርበት ይገባል።የዱቄት ወተት በሚገኝበት ቅጽበት ወደዚያ መመለስዎን እርግጠኛ ይሁኑ።
- ለህፃንዎ የአልመንድ ወተት ወይም ሌሎች የአትክልት ተዋፅዖ የሆኑ ወተቶችን አይስጡ። እነዚህ በአብዛኛው በቂ ፕሮቲን እና ንጥረ-ነገሮች አያካትቱም።
- የአትክልት ወተት ለመጠቀም እያሰቡ ከሆነ ከልጅዎ ሐኪም፣ ነርስ፣ ወይም ክሊኒክ ጋር ይነጋገሩ።
- ልጄ በ Abbott የታሰበ ልዩ የዱቄት ወተት ያስፈልገዋል/ጋታል። ምን ማድረግ አለብኝ?
-
የ U.S. Food and Drug Administration Abbott አንዳንድ ልዩ እና ሜታቦሊክ የዱቄት ወተቶችን (በእንግሊዘኛ አገናኝ) ከኩባንያው ፋብሪካ በስተርጂስ፣ እንዲሁም በሚቺጋን በአንዳንድ ሁኔታዎች እንዲለቅ ይፈቅዳል ብሏል።ልጅዎ ከእነዚያ አንዱ የዱቄት ወተት ካስፈለገው የልጅዎን ሐኪም፣ ነርስ፣ ወይም ክሊኒክ ስለተለገሰ ወተት ይጠይቁ።
- ልጄን የዱቄት ወተት እየመገብኩ ከሆነ ጡት ማጥባት መጀመር ይቻላል?
-
ከረዥም ጊዜ ማቆም በኋላ ጡት ማጥባት ወይም ጡት አጥብተው ሳያውቁ መጀመር ይቻላል፣ ነገር ግን ጊዜ እና ጥረት ይጠይቃል። የወተት አቅርቦትን እንዴት ማነሳሳት እንደሚቻልLa Leche League International ግብዓቶችአሉት።