በዚህ ገጽ ላይ ምን አለ
ራስዎንና ሌሎችን ይጠብቁ፦
ጠቃሚ ምክሮች፦
ጭስ መተንፈስ ለማንም ሰው ጥሩ አይደለም። ከእሳቶች የሚመጣ ጭስ መተንፈስን በተመለከተ ስለሚያስከትለው የጤና ስጋቶች የበለጠ ይወቁ።
ሁሉም ሰው ተጋላጭነትን ለመቀነስ እርምጃዎችን መውሰድ አለበት። ከዚህ በታች እራስዎን፣ ቤተሰብዎን፣ የቤት እንስሳትዎችዎን እና ከብቶች ከቤት ውጭ ወይም ውስጥ ከእሳቶች ጭስ ለመጠበቅ ሊወስዷቸው የሚችሏቸው እርምጃዎች ናቸው። አስም ወይም ሌሎች የሳንባ በሽታዎች ካሉብዎት የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ምክር ወይም የአስም እርምጃ ዕቅድ፣ ካለዎት ይከተሉ።
ከቤት ውጭ
ከቤት ውጭ ሲሆኑ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጊዜን እና ክብደት ይገድቡ። ለተወሰነ ጊዜ ከቤት ውጭ መሆን ካለብዎት፣ እንደ N95 ማስክ ያለ በአግባቡ የተለበሰ፣ በNational Institute for Occupational Safety and Health (NIOSH፣ ብሔራዊ የሥራ ደህንነት እና ጤና ተቋም) የተፈቀደ የቅንጣት መተንፈሻ ያድርጉ።
ጭስ በሚኖርበት ወቅት ወደ ውጭ ሲወጡ፣ የእኛን የአየር ጥራት የመረጃ ምንጮች ገጾች መመልከትዎን ያስታውሱ።
-
ማስክ መጠቀም
-
ጭስ በሚኖርበት ጊዜ ወደ ውጭ ከመሄድ መቆጠብ ካልቻሉ፣ የN95 ማስኮች የተወሰነ መከላከያ ሊሰጡዎት ይችላሉ። እነዚህ ማስኮች በጭስ ውስጥ የሚገኙትን አብዛኞቹን ጥቃቅን ቅንጣቶች የሚያጣሩ ሲሆን ነገር ግን እንደ ካርቦን ሞኖክሳይድ ያሉ ጎጂ ጋዞች አያጣሩም። የN95 ማስኮች በብዙ የቁሳቁስ መደብሮች፣ የቤት ጥገና መደብሮች እና ፋርማሲዎች ይገኛሉ።
የN95 ማስኮች የመከላከል አቅም ለማቅረብ ትክክለኛ መጠን እና አገጣጠም ያስፈልጋቸዋል። በአግባቡ ካልተለበሱ፣ አነስተኛ የመከላከል አቅም ማቅረብ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ጢም እና የፊት ፀጉር ተገቢ የሆነ አገጣጠም እንዳይፈጠር ይከላከላሉ፣ ይህም ደግሞ አነስተኛ የመከላከል አቅም ማለት ነው። የN95 ማስክን በአግባቡ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይውን ይህንን ቪዲዮ (በእንግሊዝኛ) ይመልከቱ።
የአዋቂዎች ትንሹ N95 ማስኮች ዕድሜያቸው 7 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ህጻናት ተስማሚ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን ከዚህ የሚያንሱ አይገኙም እና N95ዎች በልጆች ላይ በሰፊው ጥቅም ላይ እንዲውል አልተፈተሸም።
ስለ ህጻናት የማስክ አጠቃቀም ተጨማሪ ምክሮችን ለማግኘት Western States PEHSU መመሪያ (PDF)ን (በእንግሊዝኛ) ይመልከቱ።
ማስክ ማድረግ ለመተንፈስ የበለጠ አስቸጋሪ ያደርገዋል። የሳንባ በሽታ፣ የልብ ሕመም ወይም ሥር የሰደደ ሕመም ያለበት ማንኛውም ሰው ማስክ ከመጠቀሙ በፊት የጤና እንክብካቤ አቅራቢን ማማከር አለበት።
መስኮቶችን ዘግተው ማቆየት ወይም የቤት ውስጥ አየርን ማጣራት በማይችሉባቸው የቤት ውስጥ ቦታዎች፣ የውጪ ጭስ መጠን ከፍተኛ ከሆነ ለአጭር ጊዜ N95 ማስክ ማድረግ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። የእነዚህ የቤት ውስጥ ቦታዎች ምሳሌዎች የህዝብ ትራንስፖርት እና የንግድ ወይም የህዝብ ሕንፃዎችን ያካትታሉ።
ስለ ተገቢ አጠቃቀምና ተስማሚነት እና አንድ ማስክ በNIOSH የተፈቀደ መሆኑን እንዴት መለየት እንደሚቻል ተጨማሪ መረጃ፦
- የሰደድ እሳት ጭስ እና የፊት ማስኮች መረጃ ወረቀት (PDF) (በእንግሊዝኛ)
- የNIOSH የግል መከላከያ መሳሪያዎች ለሕዝብ (በእንግሊዝኛ)
-
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
-
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጤና በጣም አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የአየር ፍሰትዎ ይጨምራል፣ ይህም ደግሞ የአየር ጥራት ደካማ በሚሆንበት ጊዜ የበለጠ ብክለት ይተነፍሳሉ ማለት ነው። ጭስ በሚኖርበት ወቅት፣ በቤት ውስጥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ይሞክሩ። የቤት ውስጥ አየርዎ መጥፎ ከሆነ እንቅስቃሴዎችዎን ቀላል ያድርጓቸው። እንደ አጠቃላይ መመሪያ፣ ለጭስ ስሜታዊ ከሆኑ፣ የአየር ጥራት ለተጋላጭ ቡድኖች ጤናማ ያልሆነ ምድብ (ብርቱካንማ፣ AQI 101-150) ወይም ከዚያ የከፋ በሚሆንበት ጊዜ እንቅስቃሴዎችዎን መገደብ አለብዎት። ስሜታዊ ይሁኑ አይሁኑ፣ ምልክቶችን መከታተል አለብዎት። የአየር ጥራት በ ጤናማ ያልሆነ (ቀይ) ምድብ ወይም የከፋ (AQI 151 ወይም ከዚያ በላይ) ውስጥ ሲሆን ሁሉም ሰው እንቅስቃሴዎችን መገደብ አለበት።
ሰዎች ዝቅተኛ እና ከፍተኛ መጠን ያለው ጭስ በተመለከተ የተለያዩ ምላሾች አሏቸው፣ እና ለእራስዎ ምልክቶች ትኩረት መስጠት እና እንደ አስፈላጊነቱ እንቅስቃሴዎችዎን ማስተካከል አስፈላጊ ነው። በእንቅስቃሴው ወቅት ጥሩ ስሜት ቢሰማዎትም እንኳ ለጭስ መጋለጥ ጤናዎን ሊጎዳ እንደሚችል እና ከሰዓታት ወይም ከቀናት በኋላ ምልክቶች ሊታዩብዎት እንደሚችሉ ያስታውሱ።
አንዳንድ ሰዎች በተለይ ለዝቅተኛ የጭስ መጠን ስሜታዊ ናቸው እና የአየር ጥራት መካከለኛ ምድብ (ቢጫ፣ AQI 51-100)፣ ውስጥ ሲሆን እንደ አስም ያለባቸው ሰዎች እና የሳንባ እና የልብ ህመም ያለባቸው ሰዎች ምልክቶች ሊታዩባቸው ይችላሉ። በተለይ ለዝቅተኛ የጭስ መጠን ስሜታዊ ከሆኑ፣ በዚያ ደረጃ ተጋላጭነትን ለመቀነስ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እንመክራለን።
እንዲሁም የቤት እንስሳዎን የአየር ጥራት ዝቅተኛ በሆነበት ወቅት ከቤት ውጭ እንቅስቃሴ ከማድረግ መቆጠብ አለብዎት። ለአጭር ጊዜ እንዲጸዳዱ ብቻ የቤት እንስሳትን ወደ ውጭ ይውሰዱ።
-
መኪና መንዳት
-
የሚቻል ከሆነ መኪና ከመንዳት ይቆጠቡ። መኪና መንዳት ካለብዎት መስኮቶቹን ዘግተው ይቆዩ። የአየር ማቀዝቀዣውን ይጠቀሙ እና ማጣሪያውን እንደገና ማዘዋወር ላይ ያርጉት። አብዛኛዎቹ ተሽከርካሪዎች በመኪናው ውስጥ ያለውን አየር እንደገና ማዘዋወር ይችላሉ፣ ይህም ጭስ ያለበትን አየር ወደ ውጭ እንዳይገባ ይረዳል፤ ሆኖም ግን፣ የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን ሊከማች እና እንቅልፍ ሊያመጣ ይችላል። በየጊዜው ከሚዘዋወር አየር ወደ ንጹህ አየር መሳብ በየጊዜው መቀየር ሊኖርብዎ ይችላል።
የመኪናዎን የአየር መሳቢያ ማጣሪያዎች በእንክብካቤ ይጠብቁ እና አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ጥገና ይፈልጉ። ጭስ እይታንም ሊጎዳ ይችላል፣ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለማሽከርከር በሌሎች የአየር ሁኔታ አደጋዎች ወቅት እንደሚያደርጉት ማስተካከያ ማድረግ ሊያስፈልግዎ ይችላል።
በቤት ውስጥ
- ደህንነቱ የተጠበቀ የሙቀት መጠን ለመጠበቅ በጣም ሞቃት ካልሆነ በስተቀር መስኮቶችን እና በሮችን ይዝጉ። ወደ ታች አገናኝ።
- አየርን በHVAC ሲስተም፣ በ HEPA ተንቀሳቃሽ የአየር ማጽጃ፣ (በእንግሊዝኛ)ወይም በ DIY የሳጥን ማራገቢያ ማጣሪያ በኩል ያጣሩ።
- HVACን እንደገና እንዲዘዋወር ወይም የውጪ/ንፁህ አየር ማስገቢያውን እንዲዘጋ ያድርጉት።
- የቤት ውስጥ ብክለትን አይጨምሩ። የሚከተሉትን ያስወግዱ፦
- ሻማዎች፣ ዕጣን እና እንጨት ማቃጠል።
- የሚረጩ፣ የተበታተኑ አስፈላጊ ዘይቶችን ወይም የአየር ማጽጃዎችን መጠቀም።
- ምግብ በምድጃ መጥበስ ወይም በዘየት መጥበስ እና የጋዝ ወይም የፕሮፔን ምድጃዎችን ወይም ኦቭኖችን አጠቃቀም ይገድቡ።
- የጋዝ ወይም የፕሮፔን ምድጃዎችን ወይም ማሞቂያዎችን መጠቀም።
- ማጨስ ወይም በቤት ውስጥ ቬፕ መጠቀም።
- ቫክዩምዎ የHEPA ማጣሪያ ከሌለው በስተቀር መጥረግ ወይም ቫክዩም ማድረግ።
- እንደ ዝናብ ወይም የነፋስ አቅጣጫ በሚለዋወጥበት ወቅት ያሉ የአየር ጥራትን ለማሻሻል የሚያስችሉዎትን ጊዜያት በመጠቀም መስኮቶችን ይክፈቱ እና የHVAC ስርዓትዎ ንጹህ አየር እንዲወስድ ያድርጉ። ይህ በተለይ ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ (3-4 ቀናት ወይም ከዚያ በላይ) የጭስ ወቅቶች በሚኖሩበት ጊዜ ጠቃሚ ነው። የአየር ጥራት ሲባባስ መስኮቶችን እንደገና መዝጋት እና የንፁህ አየር ማስገቢያውን እንደገና ማጥፋትዎን ያስታውሱ።
- መስኮቶችን መዝጋት ወይም የቤት ውስጥ አየርን ማጣራት ካልቻሉ፣ የውጪ ጭስ መጠን ከፍ ካለ ለአጭር ጊዜ N95 ማስክ ማድረግ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ምሳሌዎች፦ የህዝብ ትራንስፖርት እና የንግድ ወይም የህዝብ ህንፃዎች።
- በቤት ውስጥ ንጹህ አየር ማስጠበቅ ካልተቻለ፣ እንደ የቤተሰብ ወይም የጓደኛ ቤት፣ የቤት ውስጥ የህዝብ ቦታ ወይም ተጽዕኖ ያላደረበት ቦታ ያሉ ሌሎች ቦታዎች ይሂዱ።
- በቤትዎ ውስጥ የንጹህ አየር ክፍል ይፍጠሩ (Environmental Protection Agency (EPA፣ የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ)) (በእንግሊዝኛ) ይህም በሰደድ እሳት ጭስ ወቅት የጭስ መጠን ዝቅተኛ እንዲሆን ተደረጎ የተዘጋጀ ነው።
- ቪዲዮ ይመልከቱ እና የንጹህ አየር ክፍል እንዴት መፍጠር እንደሚችሉ ይወቁ፦
-
ሞቃት እና የአየር ማቀዝቀዣ የለም
-
በተለይም የአየር ማቀዝቀዣ ወይም ማዕከላዊ የማቀዝቀዣ ስርዓት ሳይኖር፣ ሞቃታም በሚሆንበት ጊዜ ጭስ እንዳይገባ ማድረግ ፈታኝ ሊሆን ይችላል። ከሙቀት ጋር የተያያዘ ህመም በፍጥነት ሊከሰት ስለሚችል እና ለሕይወት አስጊ ሊሆን ስለሚችል ለሙቀት መጨመር ትኩረት ይስጡ። ደካማ የአየር ጥራት በሚኖርበት ጊዜ ቤት ውስጥ ሞቃት ከሆነ፣ እነዚህ እርምጃዎች ቀዝቀዝ ብለው እንዲቆዩ ሊረዱዎት ይችላሉ፦
ቀን ላይ መስኮቶችን፣ መጋረጃዎችን እና መሸፈኛዎችን ይዝጉ እና ተንቀሳቃሽ የአየር ማራገቢያዎችን ይጠቀሙ። በቀኑ በጣም ሞቃታማ በሆኑ ጊዜያቶች ወቅት የምድጃ እና ኦቭን አጠቃቀምዎን ይቀንሱ።
ከሙቀት ጋር የተያያዘ በሽታን ስለመከላከል መረጃ ለማግኘት፣ የDepartment of Health (DOH፣ የጤና መምሪያ) ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ደህንነት መመሪያን (በእንግሊዝኛ) ወይም የCenters for Disease Control and Prevention (CDC፣ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከላት) ከሙቀት ጋር የተያያዘ ህመም መከላከልን (በእንግሊዝኛ) ይከተሉ።
- በቀዝቃዛ ውሀ ገላ ይታጠቡ ወይም ሻወር ይውሰዱ። ለሕይወት አስጊ የሆኑ ችግሮችን ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ከከፍተኛ የሙቀት ለውጦች ይጠንቀቁ።
- የበረዶ ከረጢቶችን ይጠቀሙ ወይም እግርዎን በቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ይንከሩ። እርጥብ ጨርቅ በአንገትዎ ጀርባ ላይ ያድርጉ ወይም ከአየር ማራገቢያ አጠገብ ሲቀመጡ እራስዎን በውሃ ይረጩ።
- በተለይም ውሀ እየጠጡ ይቆዩ። የአካልዎን ውሃ መጠን ስለሚቀንሱ ስኳር የበዛባቸው ወይም የአልኮል መጠጦችን ያስወግዱ።
- ቅዝቃዜ ወዳለው የቤት ውስጥ ክፍል ይሂዱ - ለጥቂት ሰዓታት ብቻ ቢሆንም እንኳን። በማህበረሰብዎ ውስጥ ስለሚገኙ የማቀዝቀዣ ማዕከላት ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት፣ Washington 2-1-1 ይጎብኙ።
- የአየር ጥራትን ይከታተሉ እና የአየር ጥራት ሲሻሻል መስኮቶችዎን ይክፈቱ። የቅርብ ጊዜ የአየር ጥራት መረጃ ለማግኘት በEPA የእሳት እና የጭስ ካርታ ላይ የዳሳሾችን “አዝማሚያ” መረጃ መመልከት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።
- ከቤት ውስጥ ይልቅ ውጪው ቀዝቃዛ ሲሆን ብቻ መስኮቶችን ይክፈቱ። ክፍት መስኮት በጣም ውጤታማ የሚሆነው በር ወይም ተጨማሪ መስኮት ንፋስ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ ሲከፈት ነው። ለተጨማሪ መረጃ፣ ያለ አየር ማቀዝቀዣ የቤት ውስጥ ቦታዎችን ማቀዝቀዝ (PDF) (በእንግሊዝኛ) ን ይመልከቱ።
- የቤት ውስጥ አየርን ለማጣራት እርምጃዎችን ይውሰዱ - "በቤቴ ውስጥ የአየር ማጣሪያን ማሻሻል" የሚለውን ከዚህ በታች ይመልከቱ።
-
በቤቴ ውስጥ የአየር ማጣሪያን ማሻሻል
-
በቤትዎ ውስጥ ያለውን አየር ማጣራት የቤት ውስጥ የአየር ጥራትዎን ሊያሻሽል እና ለጭስ ያለዎትን ተጋላጭነት ሊቀንስ ይችላል። ሶስት የማጣሪያ አማራጮች ከዚህ በታች ተብራርተዋል። በእያንዳንዱ አማራጮች ውስጥ የተለያዩ ጉዳዮች እና አቅርቦቶች እንዳሉ ልብ ይበሉ። የሰደድ እሳት ጭስ እንደደረሰ አቅርቦቶች በፍጥነት ስለሚሸጡ፣ ከሰደድ እሳት ወቅት በፊት አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ለመግዛት ይሞክሩ። የሰደድ እሳት ጭስ ወቅት አብዛኛውን ጊዜ የሚጀምረው በጁላይ ወይም ኦገስት ወር ነው፣ ነገር ግን ከሜይ መጀመሪያ ጀምሮ ሊጀምር ይችላል።
1. የማሞቂያ፣ የአየር ማናፈሻ እና/ወይም የአየር ማቀዝቀዣ (HVAC) ስርዓት ካለዎት፣ ቅንጣትን ለማስወገድ ደረጃ የተሰጠው ማጣሪያ ይጠቀሙ። ይህ በቤትዎ ውስጥ በሙሉ ከሰደድ እሳት ጭስ የሚመጡ ጥቃቅን ቅንጣቶችን ይቀንሳል።
- ማሻሻያዎችን ከማድረግዎ በፊት የHVAC መመሪያዎን ያንብቡ ወይም ከHVAC ባለሙያ ጋር ይመካከሩ።
- MERV 13 ደረጃ የተሰጠው ማጣሪያ ወይም ስርዓትዎ ሊቋቋመው የሚችለውን ከፍተኛ ደረጃ የተሰጠው ማጣሪያ ይጠቀሙ። በስርዓቱ ላይ ከመጠን በላይ ጫና እንዳይፈጠር ለመከላከል ስርዓትዎ ሊቋቋመው የሚችለውን ጥልቅ የሆነ ሽንሽን ያለው ማጣሪያ ይምረጡ። ማጣሪያው ጥብቅ ብሎ መግጠም አለበት። ለበለጠ መረጃ የEPA የMERV ደረጃ ምንድን ነው (በእንግሊዝኛ) ይመልከቱ?
- የስርዓት ማራገቢያውን እንደገና ማዘዋወር ላይ ያድርጉት እና በአርገብጋቢው ሁነታ ላይ ያለማቋረጥ እንዲሰራ ያቀናብሩ። (ስርዓትዎ ወደ "በራ" መዋቀሩን ያረጋግጡ፣ "ራስ-ሰር" አይደለም)
- የMERV 13 ማጣሪያ ከሌለዎት፣ ጭስ እንዳይገባዎት ንጹህ አየር ማስገቢያውን ይዝጉ። የአየር ጥራት ሲሻሻል እንደገና ይክፈቱት።
- ማጣሪያው ሲቆሽሽ ወይም በአምራቹ መመሪያዎች ወይም በHVAC ባለሙያ እንደተገለጸው መተካትዎን ያስታውሱ። ረጅም የጢስ ጊዜያት በሚኖሩበት ወቅት የማጣሪያ ምትክ ብዙ ጊዜ ያስፈልጋሉ።
2. HEPA ተንቀሳቃሽ የአየር ማጽጃዎች በአንድ ክፍል ውስጥ ወይም በተወሰነ ቦታ ውስጥ ከጭስ ውስጥ ቅንጣቶችን በማስወገድ የቤት ውስጥ የአየር ጥራትን ማሻሻል ይችላሉ። የካርቦን ማጣሪያዎችን የያዙ የHEPA አየር ማጽጃዎች ከቤት ውስጥ አየር ውስጥ አንዳንድ ጎጂ ጋዞችን ማስወገድ ይችላሉ።
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተንቀሳቃሽ የአየር ማጽጃ ይምረጡ፦
- ማጣሪያ ብቻ - አዮኒክ፣ ኦዞን ወይም አልትራቫዮሌት (UV) ቴክኖሎጂዎች የሉም።
- ከፍተኛ ብቃት ያለው የቅንጣት አየር (HEPA) ማጣሪያ።
- ለክፍልዎ ትክክለኛው መጠን።
- ብዙ ድምጽ የማያወጣ።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ይመልከቱ፦
- ተንቀሳቃሽ የአየር ማጽጃዎች (በእንግሊዝኛ)
- ሰራተኞችን ለመጠበቅ ተንቀሳቃሽ የአየር ማጽጃዎችን መምረጥ እና መጠቀም፣ National Institute of Environmental Health Sciences (NIEHS፣ ብሔራዊ የአካባቢ ጤና ሳይንስ ተቋም) (በእንግሊዝኛ)
- በቤት ውስጥ የአየር ማጽጃዎች መመሪያ፣ EPA (በእንግሊዝኛ)
3. የራስዎን የሳጥን ማራገቢያ ማጣሪያ (እንዲሁም DIY የሳጥን ማራገቢያ ማጣሪያ ተብሎም ይጠራል) መስራት አየርን ለማጣራት እና የቤት ውስጥ የአየር ጥራትን በአንድ ክፍል ወይም በተመደበ ቦታ ለማሻሻል ርካሽ አማራጭ ሊሆን ይችላል።
- መደበኛ 20" x 20" የሳጥን ማራገቢያ (2012 ወይም ከዚያ በላይ) ይምረጡ
- በሳጥን ማራገቢያ ውስጥ ምን መፈለግ እንዳለብዎት፦
- በምርት ዝርዝሮች ስር UL-listed ወይም ETL-listed የሚል ማራገቢያ ይፈልጉ። አዳዲስ ሞዴሎች ተጨማሪ የደህንነት ባህሪያት ጨምረዋል።
- ከ2012 በፊት የተገነቡ የሳጥን ማራገቢያዎች የእሳት አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ። የድሮ ሞዴል ማራገቢያ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ ያለ ክትትል አይተዉት ወይም በሚተኙበት ጊዜ አይጠቀሙበት።
- የመቆጣጠሪያው ቅንብሮች እና የኤሌክትሪክ ገመዱ በደጋፊው ውጫዊ ጠርዝ ላይ የሚገኙበትን ማራገቢያ መምረጥ ጠቃሚ ነው፣ ይህም ማጣሪያው ከተገጠመ በኋላ ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል።
- በሳጥን ማራገቢያ ውስጥ ምን መፈለግ እንዳለብዎት፦
- 20” x 20” MERV 13 ማጣሪያ ከሳጥኑ ማራገቢያ ጋር ያያይዙ። 1 MERV ማጣሪያ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ የሚለጠጥ ገመድ፣ መጠፈሪያዎች፣ ቴፕ ወይም ማጣሪያውን ከአየር ማራገቢያው ጋር ማያያዣዎችን መጠቀም ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይመልከቱ፦
- እንዲሁም ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ማጣሪያዎችን ስለመጠቀም ግምት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። በርካታ ማጣሪያዎችን መጠቀም በአራጋቢው ሞተር ላይ ያለውን ሸክም ሊቀንስ ይችላል። 2 ማጣሪያዎችን የያዘ የDIY የሳጥን ማራገቢያ ማጣሪያ ምሳሌ እዚህ ይመልከቱ፦
- 4 ወይም 5 የMERV ማጣሪያዎችን የያዘ DIY የሳጥን ማራገቢያ ማጣሪያ ምሳሌ እዚህ ይመልከቱ፦
- የሳጥኑን የአየር ማራገቢያ አምራች መመሪያዎችን ይከተሉ፣ የሚከተሉትንም ጨምሮ
- ጥቅም ላይ እያለ ልጆችን ያለ ክትትል አይተዉ።
- የማራዘሚያ ገመድ አይጠቀሙ።
- አብዛኛውን ጊዜ ለማሳለፍ ባሰቡበት ክፍል ውስጥ እና መስኮቶችን እና በሮች ዝግተው መቆየት በማይችሉበት ክፍል ውስጥ የሳጥን ማራገቢያ ማጣሪያውን ያስቀምጡ። በትንሽ ክፍሎች እና ወደ ሌሎች ክፍሎች የሚወስዱ በሮች ሊዘጉ በሚችሉባቸው ቦታዎች የበለጠ ውጤታማ ይሆናል።
- የማራገቢያው አየር እንዳይዘጋ ማጣሪያውን ከግድግዳዎች፣ የቤት እቃዎች ወይም ሌሎች ነገሮች ቢያንስ አንድ ጫማ ርቀት ላይ ያስቀምጡ።
- በመስኮት ውስጥ እንዲሰራ አያድርጉት።
- Puget Sound Clean Air Agency (ፑጌት ሳውንድ ንጹህ አየር ኤጀንሲ) አንድ ትንሽ ክፍል (15' x 15') ለማጽዳት ቢያንስ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ እንደሚወስድ አረጋግጧል።
- መስኮቶችን እና በሮችን ዝግ አድርገው ይቆዩ።
- ቆሻሻ በሚሆንበት ጊዜ ማጣሪያውን ይቀይሩ። ይህ ጭስ በሚኖርበት ወቅቶች ብዙ ጊዜ ሊከሰት ይችላል።
የራስዎን የሳጥን ማራገቢያ ማጣሪያ ሲሰሩ፣ ውስንነቶቹን መረዳት አስፈላጊ ነው። ከEPA ጋር በመተባበር በUL በተደረገ ሙከራ ከ2012 ወይም ከዚያ በኋላ በተመረቱ ማራገቢያዎች ላይ ምንም አይነት የደህንነት ስጋቶች አልተገኙም፣ የሳጥን ማራገቢያዎች ከማጣሪያ ጋር እንዲሰሩ የተነደፉ አይደሉም፣ እና ውጤታማነቱ እንደ ዲዛይኑ እና እንደተመረጠው አቅርቦት ይለያያል። EPA እንደ በገበያ ላይ የሚገኙ የHEPA ተንቀሳቃሽ የአየር ማጽጃዎች ካሉ የሚታወቅ ችሎታ ካላቸው ምርቶች አንጻር እንደ ዘላቂ አማራጭ አድርጎ አይመክራቸውም።
የቤት ውስጥ አየርን ከጭስ ነጻ ስለማድረግ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ የEPA የቤት ውስጥ አየር ማጣሪያ የመረጃ ወረቀት (PDF) (በእንግሊዝኛ) ይመልከቱ።
ጭስ በሚኖርባቸው ወቅቶች ህጻናትን እና ተማሪዎችን ይጠብቁ
ህጻናት እና ወጣቶች ከሰውነት ክብደታቸው አንጻር ሲታይ ከአዋቂዎች ይልቅ ብዙ አየር ወደ ውስጥ ስለሚተነፍሱ፣ ከጭስ ለሚመጡ የጤና ችግሮች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው። ይህ ደግሞ አጠቃላይ ወደ ሰውነታቸው የሚተነፍሱትን የአየር ብክለት መጠን ይጨምረዋል። በተጨማሪም፣ የመተንፈሻ አካላት ስርዓት እስከ 21 ዓመት ዕድሜ ገደማ ድረስ ማደግ ይቀጥላል።
የጤና እክል ያለባቸው ህጻናት እና ወጣቶች (አስም እና ሌሎች የሳንባ በሽታዎችን፣ የልብ በሽታን፣ እና የስኳር በሽታን ጨምሮ) የጤና እክል ከሌለባቸው ህጻናት ጋር ሲነጻጸሩ ለድንገተኛ ህክምና ክፍል ጉብኝቶች እና ሆስፒታል ለመግባት ያላቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ ነው። ህጻናት እና ወጣቶች ለጭስ መጋለጥ ምክንያት የትምህርት ውጤታማነት መቀነስ፣ የነርቭ ሥርዓት ዕድገት ችግሮች፣ እና በአዋቂነት ጊዜ ለሚከሰቱ የረጅም ጊዜ የጤና እክሎችም ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ።
ስለ ህፃናት ጤና እና የሰደድ እሳት ጭስ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ይመልከቱ፦ በWestern States Pediatric Environmental Health Specialty Units (PEHSU) የህፃናት ጤና እና ሰደድ እሳት (በእንግሊዝኛ)
-
ለወላጆች እና ለአስተማሪዎች
-
ልጆች ከእሳት ስለሚመጣው ጭስ እና እንዴት እንደሚጎዳቸው እንዲማሩ የሚያግዙ የመረጃ ምንጮች ከዚህ በታች ቀርበዋል።
- የሰደድ እሳት የጤና ተፅእኖዎችን እንዲረዱት በይነተገናኝ ኢ-መጽሐፍ ይሆነውን፣ የSofia ታሪክ በPEHSU (በእንግሊዝኛ) ከልጆችዎ ጋር በመሆን ያንብቡ።
- ለልጆችዎ አንዳንድ ክሬዮኖችን እና Ready Wrigley ለሰደድ እሳት እና ለጭስ እንቅስቃሴ ዝግጁ፣ CDC (PDF) (በእንግሊዝኛ) ይስጧቸው።
- ያንብቡ ወይም በEPA የተዘጋጀውን Coco ቀይ የሆነው ለምንድነው (በእንግሊዝኛ) የተሰኘውን ቪዲዮ ከልጆችዎ ጋር ይመልከቱ።
-
ለትምህርት ቤቶች፣ ለህፃናት እንክብካቤ ተቋማት እና ለበጋ ካምፖች
-
የዋሽንግተን የህፃናት እና የወጣቶች እንቅስቃሴዎች መመሪያ (PDF) ልጆችን እና ወጣቶችን በጭስ ውስጥ ካሉ ጥቃቅን ቅንጣቶች (PM2.5) ለመጠበቅ ምክሮችን ይሰጣል።
ለትምህርት ቤት፣ ለህጻናት እንክብካቤ ማዕከላት፣ ለአትሌቲክስ ልምምዶች እና ጨዋታዎች፣ ከትምህርት ሰዓት በፊት እና በኋላ ለሚካሄዱ ፕሮግራሞች፣ ለካምፖች፣ ለመስክ ጉብኝቶች፣ እና ለሌሎች ከቤት ውጭ ለሚደረጉ ፕሮግራሞች እና እንቅስቃሴዎች ተግባራዊ ሊደረግ ይችላል። ይህ መመሪያ ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸውን ቃኚዎችን ጨምሮ ከቤት ውጭ እና ከቤት ውጭ የአየር ጥራት ክትትልን በተመለከተ መረጃም አለው። በትምህርት ቤቶች እና በንግድ ሕንፃዎች ውስጥ ጭስ ለመቀነስ መመሪያውን ይከተሉ፦
- በሰደድ እሳት ጭስ ወቅት የአየር ዝውውርን እና የቤት ውስጥ የአየር ጥራትን ማሻሻል (በእንግሊዝኛ)
- ትምህርት ቤቶችን ለመዝጋት የሰደድ እሳት ጭስ መመሪያ ማጠቃለያ (PDF) (በእንግሊዝኛ)
- ለህዝብ ጤና፣ የአየር ጥራት እና ሌሎች ባለስልጣናት ተጨማሪ የቴክኒክ መመሪያ እና የአደጋ መገናኛ መረጃ ምንጮች የሰደድ እሳት ጭስ አጋር መርጃዎች ላይ ይገኛሉ።
የቤት እንስሳት እና ከብቶችን ጭስ በሚኖርበት ጊዜ ጤናማ ሆነው እንዲቆዩ ያድርጉ
ጭስ የእንስሳትንም ጤና ሊጎዳ ይችላል። የአየር ጥራት ደካማ በሚሆንበት ጊዜ፣ በተለይም የልብ ወይም የሳንባ ችግር ያለባቸውን እንስሳት ይከታተሉ። እንስሳትዎ ምንም አይነት የጭስ መቆጣት ምልክቶች ካሳዩ የእንስሳት ሐኪምዎን ያነጋግሩ፦
- ሳል ወይም ማስመለስ።
- የመተንፈስ ችግር፣ አፍ ክፍቶ መተንፈስን ጨምሮ፣ በሚተነፍሱበት ጊዜ ከፍ ያለ ድምጽ፣ የመተንፈስ ፍጥነት መጨመር፣ ወይም ሦስቱም።
- የአፍንጫ ፍሳሽ።
- ድካም ወይም መዛል።
- ግራ መጋባት ወይም መደናቀፍ።
-
የቢት እንስሳት
-
- በተቻለ መጠን በቤት ውስጥ ያቆዩዋቸው እና ከቤት ውጭ እንቅስቃሴ ከማድረግ ይቆጠቡ።
- ከቤት ውጭ ለመጸዳዳት የሚቆዩበትን ጊዜ አጭር ያድርጉት።
- በቤት ውስጥ ከእነሱ ጋር ጊዜ ያሳልፉ እና በአእምሮም ሆነ በአካል ንቁ ሆነው እንዲቆዩ ከእነሱ ጋር ጨዋታዎችን ይጫወቱ።
- የቤት እንስሳት ወፎች በተለይ ለጭስ እና ለደካማ የአየር ጥራት ስሜታዊ ናቸው እና ከቤት ውጭ ተጋላጭነትን ማስወገድ አለባቸው።
ለተጨማሪ መረጃ፣ የቤት እንስሳትዎን ከሰደድ እሳት ጭስ ይጠብቁ፣ EPA (በእንግሊዝኛ) ይመልከቱ
-
ከብቶች
-
- እንቅስቃሴያቸውን ይገድቡ እና ሁልጊዜም በሚመገቡት ምግብ ወይም በሣር ድርቆሽ አቅራቢያ በቂ ንጹህ ውሃ ያቅርቡ።
- የአየር መተላለፊያ ቱቦዎችን የበለጠ ሊያስቆጡ የሚችሉ የአቧራ ቅንጣቶችን እንዳይተነፍሱ ለመከላከል የደረቀውን ሣር ውሃ ውስጥ ይንከሩት።
- ዝቅተኛ አቧራ ወይም አቧራ የሌለባቸውን ምግቦች በመመገብ እና የእንስሳት ማቆያ ቦታውን ውሃ በመርጨት የአቧራ ተጋላጭነትን ይገድቡ።
ደካማ የአየር ጥራት ክስተት ከተከሰተ በኋላ እንስሳት ለማገገም በርካታ ሳምንታት ሊያስፈልጋቸው ይችላል። እንስሳትዎን በተሻለ ሁኔታ እንዴት መከታተል እንደሚችሉ እና መቼ ወደ እንቅስቃሴ እንደሚመለሱ፣ እንደሚይዙ፣ እንደሚንቀሳቀሱ ወይም እንደሚያጓጉዙ ከእንስሳት ሐኪምዎ ጋር ይነጋገሩ።
ለተጨማሪ መረጃ፣ ትላልቅ እንስሳትዎን እና ከብቶችዎን ከሰደድ እሳት ጭስ ይጠብቁ (PDF) (በእንግሊዝኛ) ይመልከቱ።
የአእምሮ ጤናዎን ይጠብቁ
ለረጅም ጊዜ ለጭስ መጋለጥ የአእምሮ እና የባህሪ ጤናን ሊጎዳ ይችላል። የሰደድ እሳት ጭስ እና አደጋዎች የዕለት ተዕለት ተግባሮቻችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፣ ይህም ከቤት ውጭ የምናሳልፈውን ጊዜ መገደብ እና እንቅስቃሴዎቻችንን መቀየርን ያካትታል። አንዳንድ ሰዎች በቤት ውስጥ ከመቆየት ወይም የፀሐይ ብርሃን በማጣት ምክንያት ብቻቸውን እንደሆኑ ሊሰማቸው ይችላሉ። ጭስ ለጤና እና ለደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ነው። የአእምሮ እና የአካል ጤናን መጠበቅ ሁለቱም እጅግ በጣም አስፈላጊ ናቸው።
ጭስ በሚኖርባቸው ወቅቶች ለአእምሮ ጤናዎ ሊያደርጉ የሚችሏቸው አንዳንድ ነገሮች እነሆ፦
- ማህበራዊ ግንኙነት ቁልፍ ነው። እርዳታ መጠየቅ የሚችሉትን ሰው እና እርዳታዎን የሚፈልግ ሌላ ሰው ይለዩ። የሚወዷቸው ሰዎች እና ጎረቤቶች ላይ ክትትል ያድርጉ።
- ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር በቤት ውስጥ ንጹህ አየር ባለባቸው አካባቢዎች ወይም እንደ ቤተ-መጻሕፍት፣ የገበያ ማዕከል ወይም ሌላ የተጣራ የቤት ውስጥ አየር ባለበት ቦታ አብረው ወደ ንፁህ አየር ወዳለበት የቤት ውስጥ የህዝብ ቦታ ይሂዱ።
- DIY የሳጥን ማራገቢያ ማጣሪያዎችን አንድ ላይ ይስሩ።
- በቤት ውስጥ ቀላል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ።
- የቤት እንስሳትዎም የተወሰነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲያገኙ ከእነሱ ጋር በቤት ውስጥ ጊዜ ያሳልፉ እና ጨዋታዎችን ይጫወቱ።
- ስለ የሰደድ እሳት ጭስ ጭንቀትን መቋቋም (PDF) (በእንግሊዝኛ) የበለጠ ያንብቡ።
ተጨማሪ የመረጃ ምንጮች
- AirNow፣ እሳቶች፣ EPA (በእንግሊዝኛ)
- ለሰደድ እሳት ጭስ ዝግጁ የሆነ የመሳሪያ ሳጥን፣ EPA (በእንግሊዝኛ)
- የሰደድ እሳት ጭስ ሰውነትዎን እንዴት እንደሚጎዳ፣ CDC (በእንግሊዝኛ)