Stroke and Heart Attack Signs and Symptoms - Amharic

ኣማርኛ

ስትሮክ እና የልብ ድካም ሁልጊዜ ድንገተኛ አደጋዎች ናቸው። ግን የስትሮክ እና የልብ ድካም ምልክቶችን ያውቃሉ?

እውቀት ኃይል ነው። ምልክቶቹን በመማር፣ በሚከሰቱበት ጊዜ በመለየት እና ለእርዳታ ወደ 911 በመደወል ህይወትን ያድኑ።

ስትሮክ

  • ድንገተኛ ድንዛዜ ወይም ድክመት በፊት፣ በክንድ ወይም በእግር፣ በተለይም በአንደኛው የሰውነት ክፍል ላይ
  • ድንገተኛ ግራ መጋባት ወይም ንግግርን ለመረዳት መቸገር
  • ድንገተኛ የአንዱ ወይም የሁለቱም ዓይኖች ማየት መቸገር
  • ድንገተኛ በእግር መሄድ መቸገር፣ ማዞር፣ ወይም ሚዛንን ማጣት ወይም አካልን ማስተባበር አለመቻል
  • ባልታወቀ ምክንያት ድንገተኛ ከባድ ራስ ምታት

የልብ ድካም

  • በደረት ላይ ህመም ወይም ምቾት ማጣት
  • ማዞር፣ ማቅለሽለሽ ወይም ማስመለስ
  • የአገጭ፣ የአንገት ወይም የጀርባ ህመም
  • በክንድ ወይም በትከሻ ላይ ምቾት ማጣት ወይም ህመም
  • የትንፋሽ ማጠር

አንድ ሰው ስትሮክ ወይም የልብ ድካም ሊኖረው ይችላል ብለው ሲያስቡ፣ አይጠብቁ። ወዲያውኑ ወደ 911 ይደውሉ። የአስቸኳይ ጊዜ የህክምና አገልግሎት ሰራተኞች ስትሮክን እና የልብ ድካምን ለመለየት እና ታካሚውን በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ለማድረስ የሰለጠኑ ናቸው። እነዚህ የህክምና ድንገተኛ ሁኔታዎች ሊታከሙ የሚችሉ እና ህመምተኛው በፍጥነት በሚታከምበት ጊዜ ወደ ቤተሰቡ እና ወደ ተለመደው አሰራሩ የመመለስ እድሉ ሰፊ ነው።