የይፋዊ የ Washington ግዛት የእይታ መመሪያ የ COVID 19 ክትባት ማረጋገጫ

የ COVID-19 ክትባት በብዙ የንግድ ስራዎች፣ ኩነቶች እና አሰሪዎች ይጠየቃል። የሚከተሉት አይነት ማረጋገጫዎች በ Washington ተቀባይነት አላቸው። የተወሰኑ ቦታዎች ከታች ከተዘረዘሩት አንድ የተለየ አይነት ብቻ ሊቀበሉ ይችላሉ።

የክፍሉን ህጎች ያክብሩ እና የተጠየቁትን ማረጋገጫ አይነት ለማሳየት አስቀድመው ይዘጋጁ።

የ CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከላት) የ COVID-19 የክትባት መረጃ ካርድ

COVID-19 Vaccination Record Card Sample

የክትባት ካርድዎን በሚይዙበት ጊዜ ልብ ሊሏቸው የሚገቡ አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮች እዚህ አሉ:

  • የክትባት ካርድዎን በክትባት ዙሮች መካከል እና ከዚያ በኋላም ያስቀምጡ፡፡
  • የዲጂታል ቅጅ በቅርቡ እንዲገኝ የካርድዎን የፊት እና የኋላ ፎቶ ያንሱ፡፡ እንደገና በቀላሉ ለማግኘት እንዲችሉ ቅጂውን ለራስዎ በኢሜል መላክ ፣ አልበም መፍጠር ወይም በፎቶው ላይ መለያ ማከልን ያስቡበት፡፡
  • አንድ መያዝ ከፈለጉ ፎቶ ኮፒ ያድርጉ፡፡
  • እንዳይጥሉት ወይም እንዳይጠፋብዎት!!
  • የክትባት ካርድዎን የሚያሳዩ የራስ ፎቶን ኦንላይን አይለጥፉ። ይልቁንም የራስ ፎቶን ያንሱ እና #vaccinateWA ወይም #wadoh በመፈለግ ዲጂታል ተለጣፊ (እስቲከራችንን) ይጠቀሙ! @WADeptHealth ንን መለያ ማድረግ አይርሱ፡፡
  • ዋናውን ካርድዎን በፕላስቲክ አያሽጉት፡፡ ሁልጊዜ ሚይዙት ፎቶ ኮፒውን በፕላስቲክ ማሸግ ይችላሉ፡፡

የ COVID-19 ክትባት ምስክር ወረቀት ወይም QR ኮዶች

Certificate of COVID-19 Vaccination - Sample

ናሙና A፦
የ COVID-19 ክትባት ምስክር ወረቀት በ MyIRmobile.com ይገኛል።
WA verify SMART Health Card QR code - Sample

ናሙና B፦
WAverify.org የ QR ኮድ
QR Code Endorsed Partner App. - Sample

ናሙና C፦
ድጋፍ ባለው አጋር የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ላይ የሚታይ QR ኮድ። (መተግበሪያዎቹ ሊለያዩ ይችላሉ)

የ WA ግዛት የክትባት መረጃ ስርዓት እትም

Certificate of Immunization - Sample

ሌላ ምን እንደ ይፋዊ የ COVID-19 ክትባት መረጃ ይቆጠራል?

  • ከሕክምና አገልግሎት አቅራቢ የተረጋገጠ የኤሌክትሮኒክ የሕክምና መረጃ እትም

ስለ ክትባት መረጃዎች ጥያቄዎች ካልዎት፣ 1-800-525-0127 ላይ ይደውሉ፣ ከዚያም # ን ይጫኑ።