ረዥም COVID

ረዥም ኮቪድ ምንድነው?

አንድ ሰው በኮቪድ-19 ከታመመ በኋላ ረዥም ኮቪድ ሊከሰትበት ይችላል። ይህ ሥር የሰደደ በሽታ ነው፣ ይህም ማለት ለረጅም ጊዜ ይቆያል፣ እና/ወይም ከጊዜ በኋላ ሊመጣና ሊሄድ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ «የድህረ-ኮቪድ ሲንድሮም»፣ «ከኮቪድ-19 በኋላ ያለ ሁኔታ (PCC)» ወይም «የረዥም ጊዜ ኮቪድ» ተብሎ ይጠራል።

ረዥም ኮቪድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ጎልማሶች እና ሕፃናት ላይ ጉዳት ያደረሰ ከባድ የሕዝብ ጤና ስጋት ነው። ምልክቶቹ ከቀላል እስከ ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ እና ቢያንስ ለሦስት ወራት ሊቆዩ ይችላሉ። በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ረዥም ኮቪድ የአካል ጉዳትን ሊያስከትል ይችላል። 

ስለ ረዥ

ም ኮቪድ እስካሁን ብዙም የሚታወቅ ነገር የለም ምክንያቱም አዲስ በሽታ ነው። ኮቪድ-19ን የሚያመጣው የ SARS-CoV-2 ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በ 2019 ነው። ጥናቱ እየቀጠለ በሄደ ቁጥር ተጨማሪ ነገሮችን መማራችንን እንቀጥላለን።

የረዥም COVID ምልክቶች

የረዥም ኮቪድ ምልክቶቹ ከኮቪድ-19 ኢንፌክሽን በኋላ ለወራት ወይም ለዓመታት ሊቆዩ ይችላሉ። ምልክቶቹ ከሰው ወደ ሰው ሊለያዩ ይችላሉ እና ለመለየት ወይም ለመመርመር አስቸጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ።

Centers for Disease Control and Prevention (CDC፣ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከላት) ባሉት መሰረት፣ ከ 200 በላይ የረዥም ኮቪድ ምልክቶች አሉ። ምልክቶቹ ከአካላዊ ወይም አዕምሯዊ እንቅስቃሴ በኋላ ሊባባሱ ይችላሉ። በጣም የተለመዱ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ዕለት ተዕለት ኑሮን የሚያስተጓጉል ድካም
  • አካላዊ ወይም አዕምሯዊ እንቅስቃሴ ካደረጉ በኋላ በአጠቃላይ ጥሩ ስሜት አለመሰማት (ለመግለጽ አስቸጋሪ በሆነ መንገድ)
  • ለማሰብ ወይም ትኩረት ለማድረግ መቸገር፣ «የአዕምሮ ጭጋግ» በመባልም ይታወቃል
  • ትኩሳት
  • ለመተንፈስ መቸገር
  • ሳል
  • የደረት ህመም
  • የጨመረ የልብ ምት (የልብ ምት መጨመር)
  • የማሽተት እና/ወይም የጣዕም ላይ ለውጥ
  • የራስ ምታት
  • የእንቅልፍ ችግሮች
  • ጭንቀት እና ድባቴ
  • ከተቀመጡበት ሲነሱ የማዞር ስሜት
  • የመገጣጠሚያ ወይም የጡንቻ ሕመም
  •  የመውጋት ስሜቶች
  • የሆድ ህመም
  • ተቅማጥ
  • የሰገራ ድርቀት
  • ብጉር
  • የወር አበባ ዑደቶች ላይ ለውጥ ማየት

በረዥም ኮቪድ ማን ሊያዝ ይችላል?

ማንኛውም ኮቪድ-19 ያለበት ሰው ረዥም ኮቪድ ሊይዘው ይችላል፣ ኮቪድ-19 ሲይዘው ምንም አይነት ምልክቶች ባይታይበትም እንኳ። ከአንድ ጊዜ በላይ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች በእያንዳንዱ ኢንፌክሽን በረዥም ኮቪድ የመያዝ ስጋት አላቸው። 

ሰኔ 2024 በታተመው ጥናት መሰረት፣ በዋሽንግተን ውስጥ 6.4% የሚሆኑት ጎልማሳዎች እስከ ጥቅምት 2023 ድረስ ረዥም ኮቪድ ያጋጠማቸው ሲሆን 117,000 የሚሆኑት ደግሞ ከፍተኛ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንተጣለባቸው ይገመታል። ይህ ጥናት በተጨማሪም በዚህ ጊዜ ውስጥ የረዥም ኮቪድ መጠን በማዕከላዊ እና በምስራቅ ዋሽንግተን ከፍተኛ መሆኑን አረጋግጧል። ረዥም ኮቪድ ያለባቸው የዋሽንግተን ጎልማሳዎች መቶኛ በመደበኛነት በ Household Pulse Survey (የቤት ውስጥ የፐልስ ጥናት) ይገመታል። 

CDC እንደሚገልጸው ለረዥም ኮቪድ የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ የሆኑ ሰዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
•    ሴቶች።
•    በዕድሜ የገፉ አዋቂዎች።
•    የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች
•    የሂስፓኒክ እና ላቲኖ ሰዎች።
•    በኮቪድ-19 በጣም የታመሙ ወይም ሆስፒታል የገቡ ሰዎች።
•    የኮቪድ-19 ክትባት ያልወሰዱ ሰዎች። 

በጤና እኩልነት ችግር የሚሰቃዩ ሰዎች ከረዥም ኮቪድ ጋር በተያያዘ ለአሉታዊ የጤና ተጽዕኖ የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። የጤና እኩልነት ችግር የሚከሰተው አንድ የሰዎች ቡድን በስርዓት (አጠቃላይ ስርዓትን የሚጎዳ)፣ ሊወገድ በሚችል እና ምክንያታዊ ባልሆኑ ምክንያቶች ምክንያት የተለያዩ የጤና ውጤቶች ሲኖሩት ነው። 

Office of the Assistant Secretary of Health (OASH፣ የጤና ረዳት ጸሐፊ ጽሕፈት ቤት) በገለጸው መሰረት፣ የጤና እንክብካቤ የማግኘት እድላቸው አነስተኛ የሆኑ ወይም በጤና እንክብካቤ ስርዓት ውስጥ መገለል (ኀፍረት ወይም የጥፋተኝነት ስሜት) የሚሰማቸው ቡድኖች የረዥም ኮቪድ ምርመራ የማድረግ ዕድላቸው አነስተኛ ሊሆን ይችላል።

OASH የረዥም ኮቪድ ልዩነቶችን እንዴት እየፈታ እንደሆነ እዚህ ማንበብ ይችላሉ።

ረዥም ኮቪድን መከላከል

ኮቪድ-19ን ባለመያዝ ረዥም ኮቪድን መከላከል ይችላሉ። የኮቪድ-19 ክትባቶችን በወቅቱ እና በአግባቡ መውሰድ ከኮቪድ-19 ለመከላከል ከሁሉ የተሻለው መንገድ ነው። 

ኮቪድ-19 ይዟቸው የተከተቡ ሰዎች ካልተከተቡ ሰዎች ይልቅ በረዥም ኮቪድ የመያዝ እድላቸው አነስተኛ ሊሆን ይችላል።

የኮቪድ-19 ኢንፌክሽንን ለመከላከል ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው ሌሎች መሣሪያዎች ማስክ ማድረግ፣ የአየር ፍሰትን እና ማጣራትን ማሻሻል፣ እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና እና በውኃ መታጠብ፣ በተደጋጋሚ የሚነኩ ቦታዎችን ማጽዳት፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እና ምርመራ ማድረግን ያካትታሉ። 

ኮቪድ-19 ካለብዎት፣ ሌሎችን እነዚህን መመሪያዎች በመከተል ከኮቪድ-19 ይጠብቁ። 

እራስዎን ከረዥም ኮቪድ ይጠብቁ፦ ይከተቡ (እንግሊዘኛ) (PDF)

የ COVID-19 ክትባት ስለመውሰድ የበለጠ ይወቁ

የረዥም ኮቪድ ምርመራ

ረዥም ኮቪድን መመርመር አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ምልክቶችን መረዳት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። በአሁኑ ጊዜ የ ረዥም ኮቪድን ምርመራ ለማድረግ የሚያስችሉ ምንም የቤተ ሙከራ ምርመራዎች ወይም የምስል ምርመራዎች የሉም። የሕክምና ምርመራዎች አንድ ታካሚ ረዥም ኮቪድ ቢኖርበትም እንኳ መደበኛ ውጤቶችን ሊያሳዩ ይችላሉ። ረዥም ኮቪድ ከሌሎች ሥር የሰደዱ በሽታዎች ጋር ተመሳሳይ ምልክቶች ወይም ባህሪያት ሊኖረው ይችላል።

አንዳንድ የ ረዥም ኮቪድ ምልክቶችን ሪፖርት የሚያደርጉ ሰዎች የኮቪድ-19 ምልክቶችን አያሳዩም ። እነሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲታመሙ የኮቪድ-19 ምርመራ አላደረጉም። ይህ ደግሞ ኮቪድ-19 እንዳለባቸው ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል እና ምርመራውን ሊያወሳስበው ይችላል። አስፈላጊ ከሆነ፣ በኋላ ላይ ለ ረዥም ኮቪድ ምርመራዎ እንዲረዳዎት ሲታመሙ ለኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።

ለረዥም ኮቪድ የጤና እንክብካቤ ቀጠሮ የማረጋገጫ ዝርዝር (CDC) (እንግሊዘኛ)

አዲስ እና ቀድሞ የነበሩ የጤና ሁኔታዎች

ረዥም ኮቪድ ብዙ የአካል ክፍሎችን ሊጎዳ ይችላል። ታካሚዎች አንድ ወይም ከዚያ በላይ ሊመረመሩ የሚችሉ ሁኔታዎች ሊኖራቸው ይችላል እንደ፦ የራስ በሽታ መከላከያ ሁኔታዎች እና ማያልጂክ ኢንሴፋሎሜላይቲስ/ስር የሰደደ የድካም ሲንድሮም (ME/CFS)

ይህ ማለት ኮቪድ-19 የነበረባቸው ሰዎች እንደ ስኳር ወይም የልብ ሁኔታዎች ያሉ አዳዲስ የጤና ስጋቶች ለማዳበር የበለጠ ዕድል አላቸው ማለት ነው። እንደ የስኳር በሽታ እና የልብ ህመም ያሉ ቀደም ሲል የነበሩ የጤና ሁኔታዎችም ከኮቪድ-19 ህመም በኋላ ሊባባሱ ይችላሉ።

ከረዥም ኮቪድ ጋር መኖር

የረዥም ኮቪድ በሽታን እንዴት መመርመር እና ማከም እንደሚቻል ብዙ ነገር ገና አልታወቀም። የረዥም ኮቪድ መኖር ወይም ረዥም ኮቪድ ያለበትን ሰው መደገፍ ግራ የሚያጋባ ሊሆን ይችላል። ረዥም ኮቪድ ከሰው ወደ ሰው የተለያዩ ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል። ምልክቶቹ ለአንዳንዶች መቆጣጠር የሚችሉ እና ለሌሎች ደግሞ የአካል ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ብቻዎን እንዳልሆኑ ያስታውሱ። Centers for Disease Control and Prevention (CDC) ባሉት መሰረት፣ ከ 4 ጎልማሶች መካከል 1 ሰው ረዥም ኮቪድ አለበት ይህም የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻቸውን እንደሚገድብ ሪፖርት አድርጓል። የድጋፍ ቡድንን መቀላቀል የብቸኝነት ስሜትን ለማስታገስ ይረዳል።
ተጨማሪ ይወቁ፦

ማስተካከያዎችን መጠየቅ። ማስተካከያ ማለት ለአንድ ሰው ወይም ነገር የሚደረግ ለውጥ ነው። የበሽታው ምልክቶች ሰዎች ከመታመማቸው በፊት ማድረግ የሚችሏቸውን ነገሮች ለማድረግ አስቸጋሪ ወይም የማይቻል ሊያደርጉ ይችላሉ። ከሥራና ከትምህርት ቤት ጋር የተያያዙ ስራዎችን መስራት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። አሰሪዎች እና ትምህርት ቤቶች በበሽታው ምክንያት ለሚታዩት ምልክቶችዎ ምክንያታዊ ማስተካከያዎችን የማድረግ ኃላፊነት ሊኖራቸው ይችላል።  

ከዚህ በታች «የረዥም ኮቪድ እና የአካል ጉዳተኛ መብቶችን» ይመልከቱ።

ተጨማሪ ይወቁ፦

ጉልበትዎን በአግባቡ ይጠቀሙ። የተለመደው ምልክት የአእምሮ ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካደረጉ በኋላ ብዙውን ጊዜ ድካም መሰማት ነው። ጕልበትዎን ለመቆጠብ እንዲሁም በቀን ውስጥ ብዙ ጊዜ ዕረፍት ለመውሰድ ይሞክሩ። ከረዥም ኮቪድ ጋር ጉልበትዎን ለመቆጠብ የሚያስችልዎትን 4 ፒ ዎችን እዚህ ይማሩ፦ 120-066 - ረዥም-ኮቪድ «4 ፒ ዎች» ፖስተር - 8.5x11 - ሰኔ 2023 (wa.gov) (እንግሊዘኛ)

ረዥም ኮቪድ እና የአካል ጉዳተኛ መብቶች

ረዥም ኮቪድ አካላዊ እና አዕምሯዊ ጉዳቶችን ሊያስከትል ይችላል። በ Americans with Disabilities Act (ADA፣ የአሜሪካውያን አካል ጉዳተኞች ሕግ) መሠረት የአካል ጉዳት ሊሆን ይችላል። ረዥም ኮቪድ ያለባቸው ሰዎች በአካል ጉዳተኝነት ላይ ከሚደረግ መድልዎ በሕግ ሊጠበቁ ይችላሉ። ከንግድ ድርጅቶች፣ ከግዛት እና ከአካባቢው መስተዳድሮች ተገቢውን ማስተካከያ የማግኘት መብት ሊያገኙ ይችላሉ።

በ ADA ስር የ «ረዥም ኮቪድ» እንደ አካል ጉዳተኝነት መምሪያ (እንግሊዘኛ)

ረዥም ኮቪድ እና እርግዝና

ነፍሰ ጡር ወይም በቅርቡ ነፍሰ ጡር የሆኑ ሰዎች በኮቪድ-19 የመታመም ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ኮቪድ-19 በእርግዝና እና እያደገ ባለው ህፃን ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል። እርጉዝ የሆኑ ወይም ጡት የሚያጠቡ ሴቶች የኮቪድ-19 ክትባትን እንዲወስዱ መምከር ለደህንነታቸው የሚመከር ነው።

ነፍሰ ጡር ሴቶች ረዥም ኮቪድ ሊያጋጥማቸው ይችላል። በእርግዝና ወቅት እና ከእርግዝና በኋላ የረዥም ኮቪድ ተፅእኖዎች ላይ አሁንም ጥናቶች እየተደረጉ ነው።

ረዥም ኮቪድ እና ወጣቶች

ወጣቶችም በረዥም ኮቪድ ምክንያት ሊታመሙ ይችላሉ። ብዙውን ጊዜ የሚደክሙ ወይም ትኩረታቸውን መሰብሰብ የሚከብዳቸው ወጣቶች በትምህርት ቤትም ሆነ በሌሎች እንቅስቃሴዎች ለመካፈል ይቸገራሉ። ትናንሽ ልጆች የበሽታ ምልክቶቻቸውን በደንብ መግለጽ ላይችሉ ይችላሉ።

ረዥም ኮቪድ ያለባቸው ልጆች ለልዩ ትምህርት፣ ጥበቃዎች ወይም ተዛማጅ አገልግሎቶች በሁለት የፌደራል ህጎች መሰረት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

በወጣቶች ላይ ረዥም ኮቪድን ለመከላከል ከሁሉ የተሻለው መንገድ ወጣቶች የኮቪድ-19 ክትባትን እንዲከተቡ ማድረግ ነው። ስለ ኮቪድ-19 ክትባቶች እዚህ የበለጠ ይወቁ። 

ለማህበረሰቡ መረጃዎች

ለሐኪሞች እና ለሕዝብ ጤና የሚውሉ መረጃዎች

ለባልደረባዎች የሚሆን መረጃ