Care Connect Washington

እርስዎ ወይም ቤተሰብዎ በኮቪድ-19 ተጎድተዋል? በ 1-833-453-0336 ላይ Care Connect ዋሽንግተንን በማግኘት በማህበረሰብዎ ውስጥ ካሉ የአካባቢ እንክብካቤ አስተባባሪ እርዳታ ማግኘት ይችላሉ። የእንክብካቤ አስተባባሪው የእርስዎን ፍላጎቶች ለመረዳት ጊዜ ይወስድ እና ከዚያ እርስዎ እና መላው ቤተሰብዎ እንደ መኖሪያ ቤት፣ የጤና መድህን፣ የልጅ እንክብካቤ፣ የምግብ እርዳታ ፕሮግራሞች እና ሌሎች ዓይነት አገልግሎቶች ካሉ ሀብቶች ጋር እንዲገናኙ ያግዝዎታል። የሚገኙ አገልግሎቶች እንደየአካባቢው ይለያያሉ።

Care Connect ዋሽንግተን ኮቪድ-19 ላለባቸው ሰዎች በቤት ውስጥ ተገልለው እንዲቆዩ ለማድረግ በወረርሽኙ መጀመሪያ ላይ የተዘጋጀ ፕሮግራም ነው። አሁን ፕሮግራሙ በኮቪድ-19 የተጎዱ ሰዎችን የረዥም ጊዜ ፍላጎቶች ለማሟላት እየረዳ ይገኛል። ለምሳሌ፣ አንዳንድ ሰዎች ከኮቪድ-19 የሚመጡ የረጅም ጊዜ የጎንዮሽ ጉዳቶች ያጋጥማቸዋል። ሌሎች ሰዎች ታመው ሥራቸውን አጥተው ሊሆን ይችላል እና ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ለመመለስ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። Care Connect ዋሽንግተን ሊረዳ ይችላል።

Care Connect ዋሽንግተን በ Department of Health (ጤና ዲፓርትመንት)፣ በስምንት የክልል ማዕከሎች እና በመላው ስቴቱ ውስጥ ባሉ ማህበረሰቦች ውስጥ ባሉ ከ100 በላይ የአካባቢ እንክብካቤ አስተባባሪዎች መካከል ያለ ሽርክና ነው። የ Care Connect ሲስተም ሰዎች መረጋጋት እና የተሻለ ጤና እንዲያገኙ በመርዳት ማህበረሰቦችን ያጠናክራል። የአካባቢ እንክብካቤ አስተባባሪዎች ለአንድ ሰው እንደ ሥራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች፣ ድጎማ የሚደረግላቸው የመኖሪያ ቤት ወይም የሕጻናት እንክብካቤ፣ እንደ Supplemental Nutrition Assistance Program (SNAP፣ ተጨማሪ የምግብ እርዳታ ፕሮግራም) ወይም Special Supplemental Nutrition Program for Women, Infants, and Children (WIC፣ ልዩ ተጨማሪ የስርዓተ ምግብ ፕሮግራም ለሴቶች፣ ጨቅላዎች፣ እና ሕጻናት)፣ Apple Health እና ሌሎችም ላሉ የምግብ እርዳታ ፕሮግራሞች እንዲያመለክቱ ለመርዳት አብረው ይሠራሉ። Care Connect ሰዎች የሚፈልጉትን መረጃ በመረጡት ቋንቋቸው ያቀርባል።

Care Connect regions map with services in these counties: Grays Harbor, Mason, Thurston, Pacific, Wahkiakum, Lewis, Cowlitz, Clark, Skamania, Clickitat, Yakima, Benton, Franklin, Adams, Lincoln, Ferry, Stevens, Pend Oreille, Spokane, King, Pierce, Snohomish, Skagit, Whatcom

ክልላዊ አቀራረብ ለ COVID-19 እርዳታ

የግዛቱ የጤና መምሪያ፣ ከአካባቢው የጤና ስልጣኖች እና ከአጋሮቻቸው ጋር በመተባበር Care Connect Washington በክልል በክልሎች እየሰራ ነው። እያንዳንዱ ክልል እንደ የመድኃኒት አቅርቦት፣ የጤና እንክብካቤ፣ ለስራ አጥነት ማመልከት መርዳት፣ ሎካል የቤት ኤጀንሲዎች፣ የምግብ ባንኮች፣ የልጅ እንክብካቤ አቅራቢዎች እና ሌሎችም ያሉ ሰዎችን ብቁ ከሆኑባቸው አገልግሎቶች ጋር የሚያገናኙ ማኅበረሰብ ላይ መሰረት ያደረጉ አጋሮች ጋር ይሰራል።

አገልግሎቶች የሚገኙት የት ነው?

በኮቪድ-19 ለተጎዱ ሰዎች አገልግሎቶች በሁሉም የስቴቱ ክፍሎች ይገኛሉ።

ምስራቅ ክልል

Better Health Together (በእንግሊዝኛ ብቻ) Adams Ferry Lincoln Pend Oreille Spokane እና Stevens ካውንቲዎች እንደ Care Connect ዋሽንግተን ማዕከል ያገለግላል።

ኪንግ ካውንቲ

HealthierHere (በእንግሊዘኛ ብቻ) መገናኛ ለኪንግ ካውንቲ እንደ Care Connect ዋሽንግተን ያገለግላል።

ሰሜን ማዕከላዊ ክልል

North Sound Accountable Community of Health (በእንግሊዝኛ ብቻ) ለ Island፣ San Juan፣ Skagit፣ Snohomish፣ እና Whatcom ካውንቲዎች እንደ Care Connect Washington Hub ያገለግላል።

ሰሜን ምዕራብ ክልል

WithinReach (በእንግሊዘኛ ብቻ) ለክላላም፣ ጄፌርሰን እና ኪትሳፕ ካውንቲዎች የእንክብካቤ ማስተባበሪያ አገልግሎቶችን ይሰጣል።

ፒርስ ካውንቲ

Elevate Health (በእንግሊዝኛ ብቻ) ለፒርስ ካውንቲ እንደ Care Connect ዋሽንግተን ማዕከል ያገለግላል።

ደቡብ ምስራቅ ክልል

Greater Health Now(በእንግሊዘኛ ብቻ) ለኪቲታስ፣ ዋላ ዋላ፣ ዊትማን፣ ኮሎምቢያ፣ ጋርፊልድ፣ አሶቲን፣ ያኪማ፣ ቤንቶን እና ፍራንክሊን ካውንቲዎች እንደ Care Connect ዋሽንግተን ማዕከል ያገለግላል።

ደቡብ ምስራቅ ክልል

Southwest Washington Accountable Community of Health (SWACH) (በእንግሊዝኛ ብቻ)ለክላርክ፣ ክሊኪታት፣ እና ስካማኒያ ካውንቲዎች እንደ Care Connect ዋሽንግተን ማዕከል ያገለግላል።

ምዕራብ ክልል

Cascade Pacific Action Alliance’s Community CarePort (በእንግሊዝኛ ብቻ) ለካውሊዝ፣ ዋህኪአኩም፣ ፓሲፊክ፣ ግሬይስ ሀርበር፣ ማሰን፣ ተርስተን እና ውስ ካውንቲዎች እንደ Care Connect Washington Hub ያገለግላል።

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

የ Care Connect Washington አገልግሎቶችን እኔ ማግኘት እችላለሁ?

በኮቪድ-19 ከተጎዱ ለአገልግሎቶች ብቁ ይሆናሉ። ይህም በአሁኑ ጊዜ በኮቪድ-19 የታመሙ ወይም ከዚህ ቀደም ኮቪድ-19 የነበረባቸውን ሰዎች ያካትታል።

በ 1-833-453-0336 ላይ ይደውሉ። የቋንቋ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

ፍላጎቶችዎን ለመረዳት እና ከሀብቶች እና አገልግሎቶች ጋር እንዲገናኙ ለመርዳት የአካባቢ እንክብካቤ አስተባባሪ ያነጋግርዎታል።

ምን ዓይነት እርዳታ ልጠብቅ?

የአካባቢዎ እንክብካቤ አስተባባሪ እርስዎን ለማወቅ እና ፍላጎቶችዎን ለመረዳት ጊዜ ይሰጣል። ከዚያም እርስዎን ለመደገፍ የጤና እንክብካቤ፣ ድጎማ የሚደረግለት መኖሪያ ቤት ወይም የሕጻናት እንክብካቤ፣ የሥራ አጥ ጥቅማጥቅሞች፣ የምግብ ዕርዳታ እና ሌሎችንም ጨምሮ የሚገኙ የአካባቢ መገልገያዎችን ይለያሉ። አገልግሎቶች እንደ ክልሉ ይለያያሉ። Care Connect Washington የሚያስፈልጎትን መረጃ በሚመርጡት ቋንቋ ያቀርባል። የ Care Connect አገልግሎቶች ያለ ምንም ወጪ ይገኛሉ። 

እርዳታ ከማግኘቴ በፊት ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

የክልል እንክብካቤ አቅራቢዎ ሪፈራል ባገኙ በአንድ ቀን ውስጥ እርዳታ ለማቅረብ የቻለውን ሁሉ ጥረት ያደርጋል።

መረጃዬን የምትጠብቁት እንዴት ነው?

የእንክብካቤ አስተባባሪዎ ከጥሪ ማዕከል ያገኘውን መረጃ ያረጋግጣል እንዲሁም ስለፍላጎቶችዎ ይጠይቃል። ከእንክብካቤ አስተባባሪዎ ጋር የሚያጋሩት መረጃ ምስጢሩ ይጠበቃል። የእንክብካቤ አስተባባሪ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ ሰራተኞች እና Department of Health (ጤና ዲፓርትመንት) መረጃውን በመጠቀም የሚያስፈልጉዎትን መሰረታዊ አገልግሎቶች ይለያሉ። የግል ወይም ግላዊ የጤና መረጃን አያጋሩም።

Care Connect regions map with services in these counties: Grays Harbor, Mason, Thurston, Pacific, Wahkiakum, Lewis, Cowlitz, Clark, Skamania, Clickitat, Yakima, Benton, Franklin, Adams, Lincoln, Ferry, Stevens, Pend Oreille, Spokane, King, Pierce, Snohomish, Skagit, Whatcom
ወጪው ስንት ነው?

ለዚህ አገልግሎት ክፍያ አይጠየቁም። Care Connect Washington በዋሺንግተን ግዛት የ COVID-19 ምላሾችን የሚደግፉ የተለያዩ ፈንዶችን አግኝቷል።

እርዳታ ከማግኘቴ በፊት ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

የክልል እንክብካቤ አቅራቢዎ ሪፈራል ባገኙ በአንድ ቀን ውስጥ እርዳታ ለማቅረብ የቻለውን ሁሉ ጥረት ያደርጋል።

እርዳታ ሳገኝ አሁንም ራሴን ማግለል አለብኝ?

አዎ። COVID-19 ን ለጎረቤቶቻችን፣ ለጓደኞቻችን፣ ለቤተሰቦቻችን፣ እና ለስራ ባልደረቦቻችን እንዳናስተላልፍ እና ማኅበረሰቦቻችን ላይ ሰፊ አሉታዊ ተጽዕኖዎቹን ለመቀነስ ራስን ማግለል ጥቅም ላይ የሚውል አስፈላጊ መሳሪያ ነው። ራስን ከማግለል ጊዜዎ በኋላ እርዳታ የሚያስፈልጎት ከሆነ፣ የአካባቢ የእንክብካቤ አስተባባሪዎ ከረጅም ጊዜ ሎካል አገልግሎቶች ጋር በማገናኘት ቀጣይ የጤና እና የማኅበራዊ ፍላጎቶችዎን ይደግፋል።

ራሴን ማግለል ያለብኝ መቼ ነው?

ራስን ማግለል፦  አዎንታዊ የ COVID-19 ውጤት ወይም ምልክቶች ካለዎት፣ ወይም የምርመራ ውጤት እየጠበቁ ከሆነ፣ ስርጭቱን ለማቆም ራስዎን ማግለል አለብዎት።

የ COVID-19 ምልክቶቼ እየተባባሱ ከሄዱ ምን ማድረግ አለብኝ?

ምልክቶችዎ እየተባባሱ ከሄዱ በፍጥነት የህክምና እርዳታ ያግኙ። አንድ ሰው የሚከተሉትን ምልክቶች ካሳየ፣ ወዲያውኑ ድንገተኛ የህክምና እርዳታ ያግኙ፦

  • የመተንፈስ ችግር
  • በደረት ውስጥ የማያቋርጥ ህመም ወይም ክብደት
  • አዲስ ግራ መጋባት
  • መንቃት ወይም ነቅቶ መቆየት አለመቻል
  • ከንፈር ወይም ፊት ሰማያዊ መሆን

*ይህ ሙሉ ዝርዝር አይደለም። ከባድ ለሆኑ ወይም አሳሳቢ ለሆኑብዎት ሌሎች ማናቸውም ምልክቶች እባክዎ የሕክምና አቅራቢዎ ጋር ይደውሉ።

የሕክምና ድንገተኛ ሁኔታ ካለብዎ እና ወደ 911 ለመደወል ከፈለጉ ለላኪው COVID-19 እንዳለብዎት ወይም ደግሞ ሊኖርዎት እንደሚችል ይንገሩ። የሚቻል ከሆነ ድንገተኛ የሕክምና አገልግሎት ከመድረሱ በፊት የፊት ሽፋን ያድርጉ።

ለከባድ ህመም እና ሆስፒታል መተኛት ስጋት ላይ ከሆንኩስ?

ይበልጥ ከባድ ህመም ሊያጎለብቱ ለሚችሉ በ COVID-19 ለተያዙ ሰዎች በ COVID-19 ቴራፒዩቲክስ ቅድመ ጣልቃ መግባት የከባድ ህመም እና ሆስፒታል የመተኛት ስጋትን ሊቀንስ ይችላል።

ብቁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ካሰቡ፣ ለ PrEP (pre-exposure prophylaxis)፣ ሞኖክሎናል አንቲቦዲዎች ወይም የአፍ ኣንቲቫይራሎች ብቁ መሆንዎን ለመወሰን ከጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ጋር ያውሩ።

ተጨማሪ መረጃ፦ የ COVID-19 ቴራፒዩቲክስ የእውነታ ሉሆች እና መመሪያ (በእንግሊዘኛ ብቻ)።

የ Care Connect Washington አገልግሎቶችን ለምን ያህል ጊዜ ማግኘት እችላለሁ?

የክልልዎ እንክብካቤ አስተባባሪ እስከ 21 ቀናት ድረስ ይረዳዎታል። በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ የእርስዎ የእንክብካቤ አስተባባሪ ቀጣይ የጤና እና ማኅበራዊ ፍላጎቶችን ለመደገፍ ከረጅም ጊዜ አገልግሎትች ጋር ያገናኞታል።

Care Connect Washington የሚሰራው እንዴት ነው?

Care Connect Washington ለተባበረ እንክብካቤ በግዛት የሚደገፍ፣ አካባቢ ላይ ትኩረት የሚያደርግ አቀራረብ ነው።

Washington State Department of Health ክልላዊ የእንክብካቤ ትብብር ምላሽ ያስተዳድራል፣ የስራ ቅጥር እና ስልጠና ይደግፋል፣ ግዛት አቀፍ እና አካባቢያዊ መርጃዎችን ያቀራርባል፣ እንዲሁም እንደ ፈንድ እና ቴክኒካዊ መዋቅር ያሉ የውህደት መርጃዎችን በማስተዳደር ውጤቶችን ያሻሽላል።

እያንዳንዶቹ ክልሎች ሰዎች በ COVID-19 ምክንያት ራስን ማግለል ሲያስፈልጋቸው ሰዎችን ከአካባቢያዊ መርጃዎች ጋር ለማገናኘት ማኅበረሰብ ላይ መሰረት ያደረገ የስራ ግብር ይለያሉ እንዲሁም ይተገብራሉ። አስፈላጊ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ክልሎች ከአካባቢያዊ አቅራቢዎች ጋር አብረው ይሰራሉ፣ ይህም ለአካባቢያዊ የኢኮኖሚ ማገገም አስተዋጽዖ ያደርጋል።

የእንክብካቤ አስተብባሪዎች የሚመደቡት የእያንዳንዱ ሰው ልዩ የጤና እና ማኅበራዊ ፍላጎቶች ለመገምገም፣ ለመደገፍ፣ እና ለመከታተል፣ እንዲሁም የ COVID የእንክብካቤ ድርጊት እቅድ ለመፍጠር ነው። ፕሮግራሙ በተቻለው ሁሉ ሰዎችን በሚመርጡት ቋንቋ ከመርጃዎች ጋር ያገናኛል እንዲሁም ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ሂደቱ ላይ ይከታተላቸዋል።

መረጃዬን የምትጠብቁት እንዴት ነው?

የእርስዎ የእንክብካቤ አስተባባሪ ከነፃ የ COVID-19 መረጃ መስመር የሚያገኘውን መረጃ አረጋግጦ ስለ ፍላጎቶችዎ ይጠይቃል። ከእንክብካቤ አስተባባሪዎ ጋር የሚያጋሩት መረጃ ምስጢሩ ይጠበቃል። የእንክብካቤ አስተባባሪ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ ሰራተኞች እና Department of Health መረጃውን በመጠቀም የሚያስፈልጉዎትን መሰረታዊ አገልግሎቶች ይለያሉ። የግል ወይም ግላዊ የጤና መረጃን አያጋሩም።

Care Connect Washington የ COVID-19 ስርጭትን የሚከላከለው እንዴት ነው?

መሰረታዊ ማኅበራዊ እና የጤና ፍላጎቶችን ለማሟላት እርዳታ የሚያገኙ ሰዎች በቤት ራስን ማግለል በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ይበልጥ እድል አላቸው። አዎንታዊ የ COVID-19 ውጤት ያላቸውን ሰዎች ቤት ራሳቸውን እያገለሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ፣ Care Connect Washington የ COVID-19 ስርጭትን መቀነስ እና ኢኮኖሚያ ማገገምን መጨመር ይችላሉ። ስርዓቱ ትኩረት የሚያደርገው ያላቸው የጤና እና ማኅበራዊ ፍላጎቶች ለ COVID-19 ይበልጥ ተጋላጭ የሚያደርጋቸው ሰዎች ላይ ስለሆነ፣ የጤና ችግሮችን ለመድረስ እና በ COVID-19 ይበልጥ የተጎዱ ማኅበረሰቦችን ለመደገፍ ይረዳል።

ድጋፍ የሚያስፈልገው ሰው ካወቅኩ ከ Care Connect Washington የማናግረው ማንን ነው?

እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው በአሁኑ ጊዜ በቤት ውስጥ ራሳቸውን እያገለሉ ከሆኑ እና እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ፣ የግዛቱን ነፃ የ COVID-19 መረጃ መስመር ያግኙ።

ለስቴት COVID-19 የመረጃ መስመር፡ ወደ 1-800-525-0127 ይደውሉ፣ በመቀጠል # ይጫኑ። የቋንቋ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

  • ሰኞ ከ 6 a.m. እስከ 10 p.m.
  • ከማክሰኞ እስከ እሁድ ከ 6 a.m. እስከ 6 p.m. እንዲሁም የሚከበሩ የመንግስት በዓላት
Care Connect Washington የባህሪ ጤና አገልግሎቶችን ያጠቃልላል?

አዎ። የእርስዎ የእንክብካቤ አስተባባሪ የባሕሪ ጤና አገልግሎቶችን በማኅበረሰብዎ ውስጥ እንዲያገኙ ይረዳዎታል።

የእንክብካቤ ትብብር ድጋፍ አገልግሎቶች ለ Tribal Nations ዓባላት ይገኛሉ?

አዎ። የአለጠ ለማወቅ፣ ወደ COVID19.CareCoordination@doh.wa.gov ኢሜይል ያድርጉ ወይም ወደ 564-999-1565 ድደውሉ።

የትርጉም አገልግሎቶች አሉ?

አዎ። የግዛቱን COVID-19 የመረጃ መስመር በ 1-800-525-0127 ላይ ይደውሉ፣ ከዚያ #ን ሲጫኑ፣ የቋንቋ እርዳታ ይገኛል።

ከእንክብካቤ አስተባባሪ ጋር አንዴ ከተገኛኙ፣ Care Connect Washington የሚያስፈልጎትን መረጃ በሚመርጡት ቋንቋ ያቀርባል።

የመረጃ ምንጮች