ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች | የ COVID-19 ምርመራ ማድረግ

የምርመራ ኪቶችን ማግኘት

የ COVID-19 ምርመራ የት ማግኘት እችላለሁ?

እባክዎን የሚከተሉትን አማራጮች ይሞክሩ፡ -

  • አቅራቦቶች እያሉ፣ ነጻ የምርመራ ኪት ከ አዎ ይበሉ! ይዘዙ COVID Test (በእንግሊዘኛ) ወይም የቋንቋ እርዳታ ለማግኘት በ 1-800-525-0127 ይደውሉ እና # ን ይጫኑ። ትዕዛዙን ለአንድ ቤት አንድ በማድረግ ይወስኑ።
  • ከፌደራሉ ፕሮግራም ነጻ የምርመራ ኪት በ COVIDTests.gov (በእንግሊዘኛ) ይዘዙ። ትዕዛዙን ለአንድ ቤት አንድ በማድረግ ይወስኑ።
  • የቤት ውስጥ መመርመሪያን በአካባቢ ቸርቻሪዎች እና ፋርማሲዎች ይግዙ።
  • የጤና መድህን ካለዎት በመድን እቅድዎ ስር ለታቀፈ ለእያንዳንዱ ሰው፣ አብዛኞቹ መድን ሰጪዎች በየወሩ እስከ 8 የሚደርሱ የቤት ውስጥ መመርመሪያዎችን ዋጋ መመለስ ጀምረዋል። የበለጠ መረጃ እዚህ (በእንግሊዝኛ) ያንብቡ።
  • ከእርስዎ አጠገብ ባለው የምርመራ ቦታ (በእንግሊዘኛ) ላይ ምርመራ ያግኙ።

በአቅራቢያዎ ያለ የምርመራ ጣቢያ ለማግኘት እገዛ ከፈለጉ ከ የአከባቢዎ የጤና መምሪያ ወይም ወረዳ (በእንግሊዝኛ) ጋር ያረጋግጡ። እንዲሁም 1-800-525-0127 በመደወል # ን መጫን ይችላሉ። ሲያነሱት፣ የአስተርጓሚ አገልግሎቶችን ለማግኘት ቋንቋዎን ይናገሩ።

የበይነመረብ አገልግሎት የማገኝበት የለኝም / ድር ጣቢያው በቋንቋዬ አይገኝም። WA ውስጥ ነጻ ኪት እንዴት ነው የማዝዘው?

እባክዎን በ 1-800-525-0127 ይደውሉ፣ በመቀጠል # ን ይጫኑ። የቋንቋ ድጋፍን ማግኘት ይቻላል። የጥሪ ማዕከሉ እርስዎን ወክሎ በWA እና በፌደራል የመስመር ፖርታሎች በኩል ማዘዝ ይችላል።

ነፃ ምርመራዎቼን መቼ ነው የማገኘው?

በሁለቱም ፕሮግራሞች የተጠየቁ ምርመራዎች (Say YES!COVID Test (አዎ ይበሉ! የ COVID ምርመራ) ወይም Federal Program (ፌደራል ፕሮግራም)) ብዙ ጊዜ በታዘዙ 1-2 ሳምንት ውስጥ ይደርሳሉ።

የድር ጣቢያው መመርመሪያዎች እንዳለቁ ይናገራል። መቼ ነው የሚገኙት?

እንደ አለመታደል ሆኖ፣ መዘግየቱ በብሔራዊ የአቅርቦት ሰንሰለት ፍላጎቶች ምክንያት ስለሆነ መመርመሪያዎች ወደ ማከማቻ የሚመለሱበት ትክክለኛ ቀን የለንም። እባክዎን በመደበኛነት sayyescovidhometest.org (በእንግሊዘኛ) ላይ ያረጋግጡ። ስለ ትዕግስትዎ እናመሰግናለን!

ይበልጥ ወዲያውኑ ምርመራ ከፈለጉ፣ እባክዎን 'የ COVID-19 ምርመራን የት ማግኘት እችላለሁ?' በሚለው ጥያቄ ስር የተዘረዘሩትን አማራጮች ይጠቀሙ።

ሁሉንም የሚመከሩ የምርመራ አማራጮችን ከተከተልኩ በኋላ፣ አሁንም የትም ቦታ ምርመራ ማግኘት አልቻልኩም። COVID-19 እንዳለብኝ ካሰብኩ ምን ማድረግ አለብኝ?

የ COVID-19 ምርመራን ለማግኘት እየተቸገሩ ስለሆነ እናዝናለን፣ በአሁኑ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ አቅርቦት ውስን መሆኑን እናውቃለን።

የ COVID-19 ምልክቶች ግጥሞት ከሆነ ወይም ለ COVID-19 ከተጋለጡ እና ሊያዙ ይችላሉ የሚል ስጋት ካለዎት የሚከተሉትን እንመክራለን፦

አጠቃላይ ምርመራ

መመርመር ያለበት ማነው?

Department of Health (DOH፣ የጤና ጥበቃ መምሪያ) ከ COVID-19 ጋር ወጥነት ያለው ምልክት ላለባቸው ሰዎች ምርመራ እንዲደረግ ይመክራል።

DOH በተጨማሪም ተጋላጭነት ላላቸው ፣ እንደ የቅርብ ግኑኝነቶች፣ ወይም በወረርሽኝ ሁኔታዎች ውስጥ ለተጋለጡ ሰዎች ምርመራን ይመክራል።

አዎንታዊ ምርመራ ካደረግኩኝ ምን ይሆናል?

የቅርብ ጊዜውን የ Centers for Disease Control and Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከላት) እና የ DOH መመሪያን ተከተሉ እና በቤት ራስዎን ያግልሉ ይከተሉ፣ ከሌሎች ይራቁ። ሁሉም የቅርብ ግንኙነቶች ኳራንቲን መግባት አለባቸው።

በቤት ውስጥ ለተደረገ የ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ውጤት እና የእንክብካቤ አገልግሎቶችን ለማግኘት፣ እባክዎን ወደ ዋሽንግተን ግዛት የ COVID ነጻ የስልክ መስመር በ 1-800-525-0127 ይደውሉ። የቋንቋ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

በስማርት ስልክዎ ላይ WA Notify (የዋሺንግተን የተጋላጭነት ማሳወቂያ) ከተጫነ፣ ይህን መሳሪያ በመጠቀም አወንታዊ የምርመራ ውጤትንም ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ።

የበለጠ መረጃ እዚህ መገኘት ይችላልል፦ የምርመራ ውጤቱ አዎንታዊ ከሆነ ምን መደረግ አለበት.