የ COVID-19ምርመራ ማድረግ

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

በእኔ አቅራብያ የምርመራ ቦታ ፈልግ (በእንግሊዝኛ)

የቤት-ውስጥ ፖዘቲቭ ውጤቶችዎን በቀላሉ ሪፖርት ያድርጉ

ያለ ማዘዣ የመመርመሪያ ኪቶችን የሚገዙ እና አወንታዊ ውጤት የሚያገኙ ሰዎች ውጤቶችን እንዳገኙ ወደ ግዛቱ COVID-19 ነጻ የስልክ መስመር በ፣ 1-800-525-0127 መደወል ከዚያ # ን መጫን አለባቸው። የቀጥታ የስልክ መስመሩ ሰኞ ከ 6 a.m. እስከ 10 p.m.፣ እና ከማክሰኞ እስከ እሁድ (እና የሚከበሩ በዓላት) ደግሞ ከ 6 a.m. እስከ 6 p.m ይገኛል። የቋንቋ እገዛ አለ።

መመርመር ለምን ያስፈልግዎታል

መመርመር ህይወትን ያድናል። ምርመራ ሰዎች የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት፣ በጊዜው እንደ ማቆያ ያሉ ጥንቃቄዎችን እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል፤ የበሽታው ምልክት የሌላቸው ሰዎች አሁንም ቫይረሱን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። እንዲሁም መመርመር የህዝብ ጤና ባለስልጣናት ወረርሽኙን ለይተው እንዲያውቁ፣ እና አዳዲስ የቫይረሱ ተለዋጮችን ለመከታተል ይረዳል። መመርመር መደበኛ እንቅስቃሴዎችን ለመቀጠል የሚረዳ አስፈላጊ አካል ነው።

የ University of Washington ተመራማሪዎች እና Department of Health (DOH፣ የጤና መምሪያ) የ COVID-19 ምርመራ እና በ WA Notify (የዋሺንግተን ማሳወቂያ) የሚደረግ ክትትል ከዲሴምበር 2020 እስከ ማርች 2021 ድረስ ወደ 6,000 የሚጠጉ ኬዞችን ለመከላከል እንዳስቻለ ደርሰውበታል።

መቼ መመርመር አለብዎት

ህመም ከተሰማዎት ይመርመሩ። COVID-19 ሰፋ ያሉ ምልክቶች (በእንግሊዘኛ) አሉት፣ ስለዚህ ጥሩ ስሜት የማይሰማዎት ከሆነ፣ በተቻለ ፍጥነት ምርመራ ማድረጉ ተመራጭ ነው።

ለ COVID-19 ፖዘቲቭ ለሆነ ሰው ሲጋለጡ ምርመራ ያድርጉ። ምልክቶችን የሚያሳዩ ከሆነ በአስቸኳይ ምርመራ ያድርጉ። ምልክቶችን የማያሳዩ ከሆነ፣ ከተጋለጡበት ቀን በኋላ ለአምስት ቀናት ይጠብቁ እና ከዚያ ይመርመሩ።

በ Washington ውስጥ ያሉ ቢዝነሶች እና የዝግጅት ቦታዎች ወደ ተቋም ወይም ዝግጅት ከመግባታቸው በፊት የምርመራ እና/ወይም ክትባት መስፈርት ሊኖራቸው ይችላል። ከመጎብኘትዎ በፊት ይደውሉ ወይም ድህረ ገጻቸውን ይመልከቱ።

ከጉዞዎ በፊት እና/ወይም በኋላ መመርመር ሊያስፈልግዎት ይችላል። የ Centers for Disease Control and Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከላት) ን የቅርብ ጊዜ የጉዞ መመሪያ (በእንግሊዘኛ) ይመልከቱ።

ከቡድን ሰዎች ጋር፣ በተለይ ለከባድ በሽታ ተጋላጭ ከሆኑ ወይም የ COVID-19 ክትባታቸውን ወቅታዊ ካላደረጉ (በእንግሊዘኛ) ሰዎች ጋር በሚሰበሰቡበት ጊዜ።

የት መመርመር ይችላሉ

የዋሽንግተን ስቴት Department of Health ድህረ ገጽ በእያንዳንዱ ካውንቲ የሚገኝ ከስራ ሰአታት እና መስፈርቶች ጋር የመርመሪያ ጣቢያዎች መዝገብ (በእንግሊዘኛ) ይይዛል። ለምርመራ ጣቢያዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ 2-1-1 ይደውሉ። እንዲሁም ለቤት ውስጥ ምርመራ፣ የመደብር የምርመራ መሳሪያዎች እና በፋርማሲዎች የተመቻቹ፣ በቤት ውስጥ ለማዘዝ የሚገኙ ናቸው።

ወጪ

የኢንሹራንስ አቅራቢዎች አሁን በወር እስከ ስምንት ፈተናዎች ለቤተሰቦች ይከፍላሉ። ስለ ኢንሹራንስ ክፍያ (በእንግሊዘኛ) ተጨማሪ ይወቁ

በካውንቲ ወይም በስቴት በሚደገፉ የምርመራ ጣቢያዎች ለሚደረጉ ምርመራዎች ከኪስ የሚወጣ ወጪ የለም። ብዙ ምርመራዎች፣ በተለይም ምልክቶች ለሚያጋጥሟቸው ሰዎች፣ በኢንሹራንስ ሊከፈሉ ወይም በ Department of Health ድጎማ ሊደረጉ ይችላሉ።

እንዲሁም የቤት ውስጥ ምርመራዎችን በሀገር ውስጥ ወይም በመስመር ላይ ቸርቻሪዎች እና ፋርማሲዎች መግዛት ይችላሉ። ምንም ኢንሹራንስ ወይም የሐኪም ማዘዣ አያስፈልግም።

የምርመራ ዓይነቶች

አሁን ላይ የሚገኙት ምርመራዎች ፈጣን የአንቲጂን ምርመራዎችን፣ ሞለኪውላዊ ምርመራዎችን (ሁለቱም በቤተ-ሙከራ ላይ የተመሰረቱ እና የእንክብካቤ ነጥቦች)፣ እና አንዳንድ የቤት የራስ-ምርመራን ያካትታሉ። ልዩ የሆነ የማንኛውም ምርመራ አቅርቦት እንደ ፍላጎት እና የአምራች አቅም ይለያያል።

የቤት ውስጥ ምርመራ እንዴት እንደሚወስድ

ትክክለኛ ውጤት ለማግኘት በኪቱ ውስጥ ያሉትን ፈጣን የቤት ውስጥ ምርመራዎችን መመሪያዎች መከተል ያስፈልጋል። በርካታ ብራንዶች የቪዲዮ መመሪያዎችን ይሰጣሉ። ለበለጠ ምርጥ ልምዶች፣ ለቤት ውስጥ ምርመራ የ CDC ምክሮችን ይመልከቱ  (በእንግሊዘኛ).

በፈጣን ምርመራዎች የውሸት አሉታዊ ውጤቶች ሊከሰቱ ይችላሉ። አንዳንድ የመመርመሪያ ኪቶች ሁለት ምርመራዎችን ሊያካትቱ ይችላሉ (ለመመርመር በሳጥኑ ላይ ያሉትን መመሪያዎች ይከተሉ)

ፈተና እንዴት እንደሚሰራ ለበለጠ መረጃ የእኛን የፈተና ተዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ይጎብኙ.

ምርመራ እንዴት እንደሚሰራ

አብዛኛው ምርመራ የሚደረገው በአፍንጫ በሚገባ ጥጥ በመጠቀም ነው። አንዳንድ ምርመራዎች ምራቅን በመሰብሰብ ሊደረጉ ይችላሉ። ተጨማሪ ዝርዝሮች በሙከራ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች ገጽ ላይ ይገኛሉ።

መቼ ከሌሎች ራስን ማግለል ወይም መለየት

ምመራዎችን ከማድረጋቹ በፊት እና ውጤቱን ከተቀበሉ በኋላ ራስን ማግለል ወይም መለየት ሊኖርብዎ ይችላል። ይህ በክትባትዎ ሁኔታ እና በሚያሳዩት ምልክቶች ይወሰናል። የቅርብ  ጊዜው የሲዲሲ መመሪያ ይህንን በሁኔታዎች ይከፋፍለዋል። (በእንግሊዘኛ) እንዲሁም ምልክታዊ እና/ወይም ለ COVID-19 የተጋለጡ ሰዎች የእኛን መመሪያ መከተል ይችላሉ።

ቀጣይ-ክትትል

ምልክቶች ካልዎት በቻሉት መጠን ቤት ይቆዩ።  የ COVID-19 ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ካልዎት፣ የራስዎን እና የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ መውስድ የሚችሉት እርምጃዎች መኖራቸው መልካሙ ዜና ነው። የበለጠ መረጃ እዚህ መገኘት ይችላል፦ የምርመራ ውጤቱ አዎንታዊ ከሆነ ምን መደረግ አለበት