የ COVID-19 ክትባት

የ COVID-19 ክትባት ነጻ እና 6 ወር ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሰዎች ሁሉ የኢሚግሬሽን ሁኔታቸውን ሳያመላክት ማግኘት የሚችሉት ክትባት ነው።

ከቤት መውጣት አልቻሉም እና የ COVID-19 ክትባት ይፈልጋሉ? እባክዎ እዚህ ይመልከቱ (*ወደ መጽሔቱ የሚወስድ ሊንክ)

ይዘቱ ለመጨረሻ ጊዜ የዘመነው በታህሳስ 9፣ 2022 ነበር።

የ Center for Disease Control and Prevention (CDC) የዘመኑ የማጠናከሪያ ክትባት ምክረ ሃሳቦች እንደሚከተሉት ናቸው፦

  • ኦርጂናል ሞኖቫለንት የ Moderna የ COVID-19 ክትባት የተቀበሉ ከ 6 ወር እስከ 5 አመት ያሉ ህጻናት የመጀመሪያ ደረጃ ተከታዮችን ካጠናቀቁ ከሁለት ወራት በኋላ አሁን የዘመነ የባይቫለንት ማጠናከሪያ ለመውሰድ ብቁ ናቸው። 
  • ከ 6 ወር-4 አመት ለሆናቸው ህጻናት የ Pfizer COVID-19 ክትባት አሁን ሁለት ሞኖቫለንት የ Pfizer ዶዞችን እና አንድ ባለ ሁለት የ Pfizer ዶዝን ያካትታል።
    • ባለ 3 ዶዝ የ Pfizer የመጀመሪያ ክትትል ገና ያልጀመሩ ወይም የመጀመሪያ ክትትላቸውን ሶስተኛ ዶዝ ያልተቀበሉ ከ 6 ወር-4 አመት ለሆናቸው ህጻናት አሁን የዘመነውን የ Pfizer ክትትል ያገኛሉ
    • ባለ 3 ዶዝ Pfizer የመጀመሪያ ክትትልን ያጠናቀቁ ከ 6 ወር-4 አመት የሆናቸው ህጻናት በዚህ ጊዜ ለተጨማሪ ክትባቶች ወይም አጋዦች ብቁ አይሆኑም
  • የመጀመሪያ ዙር ክትባት ካጠናቀቁ ነገር ግን የ COVID-19 ማጠናከሪያ ከዚህ ቀደም ካልወሰዱ—እንዲሁም የዘመነውን የ mRNA ማጠናከሪያ መውሰድ የማይችሉ ወይም የማይወስዱ ከሆነ Novavax የ COVID-19 ማጠናከሪያዎች ለአዋቂዎች ይገኛሉ

የሚያስፈልጎትን መረጃ ለመስጠት እንፈልጋለን። ለጤንነትዎ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ምርጫ ማድረግ እንዲችሉ እኛ ወቅታዊ መረጃዎችን እንሰጥዎታለን።

የ COVID-19 ክትባትን ለማግኘት ምን ማወቅ ያስፈልገኛል?

ክትባቱን እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

ቀጠሮ ለማግኘት እንዲሁም ቀጠሮ ለማስያዝ የክትባት መፈለጊያ ን ይጎብኙ።

በተጨማሪም በአቅራቢያዎ ለሚገኙ የክትባት ቦታዎች ዚፕ ኮድዎን ወደ 438-829 (GET VAX) መላክ ይችላሉ።

ስለ COVID-19 ክትባት ጥያቄዎች አልዎት? የክትባት ቀጠሮ ለማግኘት እርዳታ ያስፈልግዎታል? ወደ COVID-19 መረጃ የቀጥታ-መስመር በ 1-800-525-0127 ይደውሉ፥ ከዚያም # ይጫኑ። የቋንቋ ድጋፍ ይገኛል።

ለሁለተኛ ጊዜ ክትባትዎ (Moderna/Spikevax ወይም Pfizer/Comirnaty) ቀጠሮ የሚያስይዙ ከሆነ፣ መጀመሪያ ከወሰዱት ክትባት ጋር ተመሳሳይ የሆነ ክትባት ማግኘት ይኖርብዎታል።

እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው በቤት ውስጥ ብቻ የሚኖሩ ከሆነ፣ አስተማማኝ የኦንላይን ቅጽ ይሙሉ። የእርስዎ መልሶች ግለሰቦችን ከሚገኙ የካውንቲ እና/ወይም የግዛት Mobile Vaccine Teams (ተንቀሳቃሽ የክትባት ቡድኖች) ጋር ለማገናኘት ያስችሉናል።

እንደ መኖሪያ ቤት፣ የአጠቃቀም እርዳታ፣ የጤና መድህን ለመሳሰሉ ሌሎች ከ COVID-19 ጋር ተዛማጅ ለሆኑ ጉዳዮች፣ ወደ 211 ይደውሉ ወይም wa211.org ን ይጎብኙ

ለበለጠ መረጃ፣ የ COVID-19 ክትባቶችን ይመልከቱ፡- ምን እንወቅ ማስረጃ ገፅ።

ክትባቱን ለመውሰድ የ U.S. ዜጋ መሆን አለብኝ?

አይ፣ ክትባቱን ለመውሰድ የ U.S. ዜጋ መሆን የለብዎትም። ክትባቱን ለማግኘት የማኅበራዊ ዋስትና ቁጥር፣ ወይም የስደት ሁኔታዎ ያላቸው ሌሎች ሰነዶች አያስፈልጉዎትም ማለት ነው። አንዳንድ የክትባት አቅራቢዎች የማኅበራዊ ዋስትና ቁጥርን ይጠይቁ ይሆናል፣ ግን መስጠት የለብዎትም።

ልጃችሁ ክትባቱን ለማግኘት የግድ የ U.S. ዜጋ መሆን የለበትም። የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎች የማንንም የኢሚግሬሽን ሁኔታ አይጠይቁም። አብዛኛውን ጊዜ፣ ወላጆችና ሞግዚቶች ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶችን ክትባት ለመስጠት የእነሱን ፈቃድ መስጠት ያስፈልጋቸዋል።

የ Washington State Department of Health (የዋሽንግተን ግዛት የጤና መሥሪያ ቤት) 6 ወር  ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሰዎች በሙሉ ክትባት እንዲወስዱ ያሳስባል።

ለክትባቱ እከፍላለሁ?

አይ። ክትባቱን በሚያገኙበት ጊዜ ምንም ነገር አያስከፍልዎትም፤ ወይም ከአቅራቢዎ ወይንም ከክትባት አቅራቢው ቡድን ወጪ መቀበል የለብዎትም። ይህ የግል መግህን፣ Apple Health (Medicaid)፣ Medicare ያላቸው ሰዎች ወይም የጤና መድን ሽፋን የሌላቸውም ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል።

ክትባት ለመውሰድ በአቅራቢዎ በሚገኙበት ጊዜ ሌሎች አገልግሎቶችን የሚያገኙ ከሆነ ለቢሮ ጉብኝት የሂሳብ ደረሰኝ ክፍያ ሊያገኙ ይችላሉ። ይህንን ለመከላከል፣ ስለ ወጪዎ አስቀድመው ከአቅራቢዎ መጠየቅ ይችላሉ።

የጤና መድን ሽፋን ከሌልዎት፣ አቅራቢዎች ለክትባቱ ሊያስከፍሉዎት እና የ COVID-19 የክትባት መርሃግብርን መጣስ አይችሉም። ክፍያ ከከፈሉ እባክዎን ወደ covid.vaccine@doh.wa.gov ኢሜይል ይላኩ።

የጤና መድህን ካልዎት እና ክፍያ ፈፅመው ከሆነ፣ በመጀመሪያ የመድህን ዕቅድዎን ያነጋግሩ። ይህ ጉዳዩን ካላስተካከለ ደግሞ፣ ለመድህን ኮሚሽነር ቢሮ ቅሬታዎን በማስገባት (በእንግሊዝኛ ብቻ) ማቅረብ ይችላሉ።

  • ለስልክ አስተርጓሚ አገልግሎት በ 800-562-6900 ይደውሉ (ያለምንም ወጪ ከ 100 በላይ ቋንቋዎች ይገኛሉ)
  • TDD/TYY፦ 360-586-0241
  • TDD፦ 800-833-6384
የጤና ኢንሹራንስ ከሌለኝስ?

የኢንሹራንስ ክፍያ ከሌልዎት፣ ለአቅራቢዎ ይንገሩት። አሁንም ክትባቱን ያለ ምንም ክፍያ ያገኛሉ።

ለክትባቱ ክፍያ የማልጠየቅ ከሆነ፣ ለምን ስለ ጤና መድህን መረጃዬ እጠየቃለሁ?

ክትባቱን በሚያገኙበት ጊዜ የክትባት አቅራቢዎ የመድህን ካርድ እንዳልዎት ሊጠይቅ ይችላል። ይህም ክትባቱን ስለሰጡዎት ክፍያ እንዲያገኙ ነው (የክትባት አስተዳደር ክፍያ)። የመድህን አገልግሎት ከሌልዎት ለአቅራቢዎ ይንገሩት። አሁንም ክትባቱን ያለ ምንም ክፍያ ማግኘት ይችላሉ።

የክትባት አስተዳደር ክፍያ ምንድን ነው እንዲሁም ማን ነው ለዚህ ወጪ የሚከፍለው?

የክትባት አስተዳደር ክፍያ አንድ የጤና አገልግሎት አቅራቢ ክትባቱን በመስጠት የሚከፈለው ክፍያ ነው። ይህ ከራሱ ከክትባቱ ዋጋ የተለየ ነው ።

የፌዴራሉ መንግሥት የክትባቱን ሙሉ ወጪ ይከፍላል። የሕዝብ ወይም የግል የጤና ኢንሹራንስ ካልዎት፣ የክትባት አቅራቢዎ ለክትባት አስተዳደር ክፍያ ክፍያውን ሊከፍላቸው ይችላል።

ከኪስዎ ወጪ ወይም ለ COVID-19 ክትባትዎ የአስተዳደር ክፍያ ከአቅራቢዎ ክፍያ መቀበል የለባችሁም። ይህ የግል መግህን፣ Apple Health (Medicaid)፣ Medicare ያላቸው ሰዎች ወይም የጤና መድን ሽፋን የሌላቸውም ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል።

በአሁኑ ጊዜ የትኞቹ የ COVID-19 ክትባቶች ይገኛሉ?

ሦስት ክትባቶች ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት እንዲውሉ ወይም በ U.S. Food and Drug Administration (FDA፣ የ U.S. የምግብና መድሀኒት አስተዳደር) ሙሉ በሙሉ ፈቃድ አግኝተዋል። እነዚህ ክትባቶች በአሁኑ ጊዜ በ Washington ግዛት ይሰጣሉ። ከ thrombocytopenia syndrome (TTS፣ ትሮምቦሳይቶፔኒያ ሲንድረም) ጋር በተያያዘ በሚከሰተው ትሮምቦሲስ ተብሎ በሚጠራው ሁኔታ ላይ እና Guillain-Barré syndrome (GBS, ጊልያን ባሬ ሲንድረም) ላይ ባለው ያልተለመደ ስጋት ምክንያት የ Pfizer (Comirnaty) እና Moderna (Spikevax) ክትባቶች ከ Johnson & Johnson ክትባት ይልቅ ይመከራሉ።

Pfizer-BioNTech የ COVID-19 ክትባት (Comirnaty)፦

ከ 6 ወር እስከ 4 አመት ለሆኑ ህጻናት ሶስት ዶዝ መድሀኒት ተሰጥቷል። የመጀመሪያዎቹ ሁለት ዶዞች በ 21 ቀናት ልዩነት እና ሶስተኛው ዶዝ ከሁለተኛው ዶዝ ከ 8 ሳምንታት በኋላ መሰጠት አለባቸው።

ይህ በ 21 ቀናት ልዩነት የሚሰጥ፣ ባለ ሁለት-ዶዝ ክትባት ነው፣ በተጨማሪም፦

  • ደካማ የበሽታ የመከላከል አቅም ያላቸው እና ባለሁለት ዶዝ የ mRNA የ COVID-19 ክትባት ያገኙ ሰዎች ተጨማሪ የመጀመሪያ ደረጃ ዶዝ መውሰድ አለባቸው።
  • ዕድሜያቸው 5 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ በሙሉ የመጀመሪያ ዙር ክትባታቸውን ወይም ቀድሞ የሚሰጥ ማጠናከሪያ ዶዛቸውን ካጠናቀቁ ከሁለት ወራት በኋላ የዘመነውን ባይቫለንት ማጠናከሪያ መውሰድ አለባቸው። Pfizer የተቀበሉ እድሜያቸው 5 አመት የሆነ ህጻናት የዘመነ የ Pfizer ባለ ሁለት ፀረ እንግዳ አካል ብቻ ሊያገኙ ይችላሉ። እድሜያቸው 6 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች የመጀመሪያ ክትትላቸው ምንም አይነት ቢሆን የዘመነ ባይቫለንት Pfizer ወይም የ Moderna ማጠናከሪያ ማግኘት አለባቸው።

ክትባቱ Comirnaty በሚል ስም 12 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት አግኝቷል። ክትባቱ ከ 6 ወር  እስከ 11 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ወጣቶች ድንገተኛ አገልግሎት እንዲሰጥ ተፈቅዶላቸዋል። ክሊኒካዊ ሙከራዎቹ ምንም ዓይነት ከባድ የደህንነት ስጋት አላሳዩም።

የ Moderna የ COVID-19 ክትባት (Spikevax)፦

ክትባቱ ዕድሜያቸው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ግለሰቦች ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት እንዲውል የተፈቀደ ነው። ይህ በ 28 ቀናት ልዩነት የሚሰጥ፣ ባለ ሁለት-መጠን ክትባት ነው፣ በተጨማሪም፦

  • የበሽታ መቋቋም አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆነ ሰዎች ተጨማሪ (ሦስተኛ) መጠን።
  • የዘመነ ባይቫለንት የ mRNA ማጠናከሪያ እድሚያቸው 6 ወር እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ክትባታቸውን ለማዘመን የመጨረሻውን ዶዝ ከወሰዱ ከ 2 ወራት በኋላ ይመከራል። ከ 6 ወር-4 አመት የሆናቸው ህጻናት ከመጀመሪያ ክትትል ጋር ተመሳሳይ የሆነ የዘመነ የባይቫለንት ዶዝ መወሰድ አለባቸው። Moderna የወሰዱ እድሜያቸው 5 አመት የሆነ ህጻናት የዘመነ Moderna ወይም የ Pfizer ባይቫለንት ማጠናከሪያ ሊያገኙ ይችላሉ። እድሜያቸው 6 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች የመጀመሪያ ክትትላቸው ምንም አይነት ቢሆን የዘመነ ባይቫለንት Pfizer ወይም የ Moderna ማጠናከሪያ ማግኘት አለባቸው።

ይህ ክትባት ዕድሜያቸዉ 18 እና ከዛ በላይ ለሆኑ ግለሰቦች ሙሉ ለሙሉ የተፈቀደ ነዉ።በ Emergency Use Authorization (EUA፣ የድንገተኛ አጠቃቀም ፍቃድ) ስር የ Moderna ክትባት ከ 6 ወር– 17 አመት ላሉ ልጆች ይገኛል። COVID-19 ክትባት የመጀመሪያ ዙርን ካጠናቀቁ እንዲሁም በ CDC ለእርስዎ የሚመከረውን በጣም የቅርብ ጊዜ የማጠናከሪያ ዶዝ ከወሰዱ የ COVID-19 ክትባቶችዎ ላይ ወቅታዊ ኖት።

ክሊኒካዊ ሙከራዎቹ ምንም ዓይነት ከባድ የደህንነት ስጋት አላሳዩም።

የ Johnson & Johnson – Janssen የ COVID-19 ክትባት፦

  • ክትባቱ ዕድሜያቸው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ግለሰቦች ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት እንዲውል የተፈቀደ ነው። ይህ የአንድ መጠን (አንድ መርፌ) ክትባት ነው።
  • ዕድሜያቸው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ በሙሉ የመጀመሪያ ዙር ክትባታቸውን ወይም ቀድሞ የሚሰጥ ማጠናከሪያ ዶዛቸውን ካጠናቀቁ ከሁለት ወራት በኋላ የዘመነውን ባይቫለንት ማጠናከሪያ መውሰድ አለባቸው።

COVID-19 ክትባት የመጀመሪያ ዙርን ካጠናቀቁ እንዲሁም በ CDC ለእርስዎ የሚመከረውን በጣም የቅርብ ጊዜ የማጠናከሪያ ዶዝ ከወሰዱ የ COVID-19 ክትባቶችዎ ላይ ወቅታዊ ኖት። ክሊኒካዊ ሙከራዎቹ ምንም ዓይነት ከባድ የደህንነት ስጋት አላሳዩም። የ Pfizer እና Moderna ክትባቶች ከ Johnson & Johnson ክትባት ይልቅ ይመከራሉ።

የ Novavaxየ COVID-19 ክትባት :

  • 12 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ዕድሜዎች በ 21 ቀናት ልዩነት ሁለት መጠኖች ተሰጥተዋል።
  • ዕድሜያቸው 12 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ በሙሉ የመጀመሪያ ዙር ክትባታቸውን ወይም ቀድሞ የሚሰጥ ማጠናከሪያ ዶዛቸውን ካጠናቀቁ ከሁለት ወራት በኋላ የዘመነውን ባይቫለንት ማጠናከሪያ መውሰድ አለባቸው።
  • የዘመነውን የ mRNA ማጠናከሪያ መውሰድ የማይችሉ ወይም የማይወስዱ ከሆነ 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሰዎች የ Novavax ማጠናከሪያ ለመውሰድ መምረጥ ይችላሉ።

ክትባቱ ዕድሜያቸው 12 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ግለሰቦች ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት እንዲውል የተፈቀደ ነው። COVID-19 ክትባት የመጀመሪያ ዙርን ካጠናቀቁ እንዲሁም በ CDC ለእርስዎ የሚመከረውን በጣም የቅርብ ጊዜ የማጠናከሪያ ዶዝ ከወሰዱ የ COVID-19 ክትባቶችዎ ላይ ወቅታዊ ኖት። ክሊኒካዊ ሙከራዎቹ ምንም ዓይነት ከባድ የደህንነት ስጋት አላሳዩም። 

ለሁለተኛ ዙር ክትባቴ ዘግይቼ ከሆነ፣ የክትባቱን ተከታታይነት እንደገና በመከተብ ማስጀመር ያስፈልገኛል?

አይ። የሁለተኛ ዙር ክትባትዎን ለመውሰድ ዘግይተው ከሆነ ክትባቱን እንደገና መጀመር አያስፈልግዎትም።

የመጀመሪያውን ዶዝዎን ከወሰዱ ከሚመከሩት ቀናት  በኋላ በተቻሎት መጠን ሁለተኛ ዙር ዶዝዎን ይውሰዱ።  

ሁለተኛውን ክትባት የምንወስድበት ጊዜ የቱንም ያህል ቢርቅም፣ ሁለቱንም ክትባቶች ማግኘት አስፈላጊ ነው።

የበሽታ መከላከል ብቃት ማነስ ካለብዎትና ተጨማሪ ክትባት ለማግኘት ብቁ ከሆኑ ሁለተኛ ክትባት ከወሰዱ በኋላ ቢያንስ 28 ቀን መጠበቅ ይኖርብዎታል።

የ COVID-19 ክትባትን ነፍሰ ጡር ከሆንኩ፣ እያጠባው ከሆነ ወይም እርጉዝ ለመሆን ካቀድኩ መውሰድ እችላለሁን?

አዎን፣ የ COVID-19 ክትባቶች በእርግዝና ወቅት አስተማማኝ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። የ Centers for Disease Control and Prevention (CDC፣የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከላት) (በእንግሊዝኛ ብቻ)፣ American College of Obstetricians and Gynecologists (ACOG፣ የአሜሪካ የጽንስ እና ማህጸን ስፔሻሊስቶች ኮሌጅ) (በእንግሊዝኛ ብቻ)፣ እና Society for Maternal-Fetal Medicine (SMFM፣ የእናት-ጨቅላ ህጻን ህክምና ማህበር) (በእንግሊዘኛ ብቻ) የ COVID-19 ክትባትን ነፍሰ ጡር ለሆኑ፣ ለሚያጠቡ ወይም እርጉዝ ለመሆን ላቀዱ ሰዎች እንዲወስዱት ይመክራል። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ክትባት ከወሰዱ ልጃችሁ በእርግዝናና በእርግዝና ወቅት COVID-19 ን የሚከላከል ፀረ-እንግዳ አካል ሊያገኝ ይችላል። በ COVID-19 የተያዙ ያልተከተቡ እርጉዝ ሰዎች ከጊዜ በፊት ወሊድ ወይም በፅንስ መሞት ለመሳሰሉ ከባድ የጤና እክሎች የመጠቃት እድላቸው ከፍ ያለ ነው። በተጨማሪም ነፍሰ ጡር እያሉ በ COVID-19 የሚያዙ ሰዎች ከሁለት እስከ ሶስት እጥፍ የበለጠ የህይወት ድጋፍ እና የመተንፈሻ ቱቦ ያስፈልጋቸዋል።

በእርግዝና እና በጡት ማጥባት ወቅት የ COVID-19 ን ከትባት ስለመዉሰድ ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት እባክዎ አንድ ክትባት፣ ሁለት ህይወቶች የሚለው ድህረ ገፅ ላይ ወቅታዊ መረጃ ይመልከቱ።

የተለመዱ ክትባቶች እየወሰድኩ የ COVID-19ን ክትባት መውሰድ እችላለሁ?

አዎ። የ Advisory Committee on Immunization Practices (ACIP፣ የክትባት ተግባራት አማካሪ ኮሚቴ) በሜይ 12፣ 2021 የምክር ሐሳባቸውን ቀይረዋል። አሁን ሌሎች ክትባቶችን በሚወስዱበት ጊዜ የ COVID-19 ክትባትን መውሰድ ይችላሉ።

ለልጅዎ አስፈላጊ የትምህርት ቤት ክትባቶች (እንግሊዝኛ ብቻ) ወይም ለሌሎች የሚመከሩ ክትባቶች ከ COVID-19 ክትባት የተለየ መርሃ-ግብር ማውጣት አያስፈልግዎትም። የ COVID-19 ክትባት ቀጠሮ ልጅዎ በሌሎች የሚያሰፈልጉት ክትባቶች ሁሉ እንዲከተብ ማድረግያ ሌላው አጋጣሚ ነው

የክትባት መረጃ ካርድ ምንድን ነው?

ለመጀመሪያ ጊዜ የ COVID-19 ክትባትን ስታገኝ የክትባት ካርድ ወረቀት መቀበል ይኖርብሃል። ይህ ካርድ ምን ዓይነት ክትባት እንዳገኘህ (Comirnaty/Pfizer-BioNTech፣ Spikevax/Moderna፣ ወይም Johnson & Johnson) እንዲሁም የወሰድክበትን ቀን ይነግርሃል።

የ Comirnaty/Pfizer-BioNTech ወይም Spikevax/Moderna ክትባት ካገኘህ ፤ አቅራቢዎ የመጀመሪያ ጊዜ ክትባትዎን ሲወስዱ ለሁለተኛ ዙር ክትባትዎ ቀጠሮ መያዝ ይኖርበታል። ሁለተኛውን ክትባት ከወሰዱ በኋላ ክትባት አቅራቢዎ ማጠናቀቅ እንዲችል ይህን ካርድ ከእርስዎ ጋር ያስቀምጡት።

ተጨማሪ መጠን ወይም የማጠናከሪያ መጠን ከወሰዱ፣ የክትባት መረጃ ካርድዎንም እንዲሁ ወደ ቀጠሮዎ መውሰድ አለብዎት። የክትባት አቅራቢዎ መጠኑን የሚመዘግበው ይሆናል።

የክትባት ካርድዎን በሚይዙበት ጊዜ ልብ ሊሏቸው የሚገቡ አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮች እዚህ አሉ፦

  • የክትባት ካርድዎን በየክትባት መጠንዎን በሚወስዱበት ጊዜ እና ከዚያ በኋላ ባለው ጊዜ ውስጥ ያስቀምጡ።
  • የዲጂታል ቅጅ በቅርቡ እንዲገኝ የካርድዎን የፊት እና የኋላ ፎቶ ያንሱ።
  • እንደገና በቀላሉ ለማግኘት እንዲችሉ ቅጂውን ለራስዎ በኢሜይል መላክ፣ አልበም መፍጠር ወይም በፎቶው ላይ መለያ ማከልን ያስቡበት።
  • አንድ መያዝ ከፈለጉ ፎቶ ኮፒ ያድርጉ።

የክትባት ካርድዎን ወደ ቀጠሮዎ ባያመጡም እንኳ ሁለተኛውን ክትባትህን ማግኘት ትችላለህ። ተመሳሳይ ዓይነት እንደገና ማግኘትዎን ለማረጋገጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ክትባት ያገኙበትን ክትባት ዓይነት (ብራንድ) እንዲፈልግ አቅራቢዎን ይጠይቁ ። የክትባት ካርድዎን ካጡ፣ የ COVID-19 የክትባት መረጃዎን ለማየት ወደ MyIR (My Immunization Registry (የእኔ ክትባት መዝገብ ቤት) ይግቡ) (በእንግሊዘኛ ብቻ) ይግቡ እና ከዚያም መረጃውን ስክሪንፎቶ ወይም ፎቶ ያንሱ። መለያ ከሌልዎት፣ በማንኛውም ጊዜ ወደ MyIR መመዝገብ ይችላሉ።

እባክዎ በ MyIR በኩል ወደ መዛግብትዎ ማረጋገጫ ለማለፍ በአፋጣኝ ላይሆን እንደሚችል ያስታውሱ፤ እና ግንኙነት በአሁኑ ጊዜ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቻ የተገደበ ነው። ወደ Department of Health COVID-19 (የ COVID-19 ጤና ጥበቃ መምሪያ) ቀጥታ-መስመር በ 833-VAX-HELP በመደወል ወይም በኢሜይል በ waiisrecords@doh.wa.gov ጋር በመገናኘት በ MyIRmobile ወይም የክትባት መዝገብ ጥያቄዎችን ለማገዝ የቀጥታ የስልክ እርዳታ ማግኘት ይቻላሉ።

ደህንነት እና ውጤታማነት

የ COVID-19 ክትባትን ማግኘት ለምን ያስፈልገኛል?

የ COVID-19 ክትባትን መውሰድ የእርስዎ ፍፁም ምርጫ ነው፤ ግን ይህንን ወረርሽኝ ለመግታት በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎች ይህንን ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ ያስፈልገናል። በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ብዙ ሰዎች በሽታውን – በክትባትም ሆነ በቅርብ ኢንፌክሽን – መከላከል ሲችሉ ለ COVID-19 ቫይረስ መስፋፋት ከባድ ይሆናል። የክትባታችን መጠን ከፍ ባለ መጠን፣ የኢንፌክሽን መጠኑ ይቀንሳል።

የ COVID-19 ክትባቶች በብዙ መንገድ ይጠብቁዎታል፦

  • በ COVID-19 ከተያዙ በከባዱ የመታመም እድልን በእጅጉ ይቀንሳሉ
  • ሙሉ በሙሉ ክትባት ማግኘትዎ ሆስፒታል የመግባት እድልዎን የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ ከ COVID-19 የመሞት አጋጣሚዎን ይቀንሳል።
  • ክትባት በማህበረሰቡ ውስጥ ጥበቃ የሚደረግላቸውነ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ በሽታው እንዳይዛመት አስቸጋሪ ያደርገዋል
  • ባለሙያዎች ሰዎች ቫይረሱን ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ የክትባቱን አቅም ማጥናታቸውን ቀጥለዋል።

ክትባት ያልወሰዱ ሰዎች አሁንም በቫይረሱ በመያዝ ወደ ሌሎች ሊያስተላልፉ ይችላሉ። አንዳንድ ሰዎች በሕክምና ምክንያቶች ክትባቱን መውሰድ አይችሉም፣ ይህ ደግሞ በተለይ ለ COVID-19 ተጋላጭ ያደርጋቸዋል። ክትባት ካልታከተቡ ሆስፒታል የመግባት ወይም ከCOVID-19 ዝርያዎች (በእንግሊዝኛ ብቻ) የመሞት ከፍተኛ ዕድል አልዎት።ክትባት ማግኘትዎ እርስዎንም ሆነ ቤተሰብዎን፣ ጎረቤቶችዎንና ማኅበረሰቡን ከአደጋ ለመጠበቅ ይረዳል።

አብዛኛዎቹ ሰዎች በበሽታው ተይዘው ከተረፉ ለምን የ COVID-19 ክትባትን መውሰድ ያስፈልገኛል?

COVID-19 ሊያስከትል የሚችለው አደጋ ሞት ብቻ አይደለም። ብዙ በ COVID-19 የተጠቁ ሰዎች መለስተኛ ምልክቶች ብቻ ይታይባቸዋል። ሆኖም ግን፣ ቫይረሱ እጅግ ሊገመት የማይችል ነው፣ እና አንዳንድ የ COVID-19 ተለዋዋጭ ዝርያዎች (በእንግሊዝኛ ብቻ) የተለያዩ ምልክቶችን በማሳየት ሊያሳምሙዎት ይችላሉ። ሥር የሰደደ የጤና ችግር የሌለባቸውም ወጣቶች እንኳን ቢሆኑ፣ አንዳንድ ሰዎች በ COVID-19 በጣም ሊታመሙ ወይም ሊሞቱ ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ፣ “የ COVID ረዥም-ተጓዥች” በመባል የሚታወቁት ለወራት የሚቆዩ ምልክቶችን በማሳየት የሕይወታቸውን ጥራት ሊያስተጓጉሉ ይችላሉ። አዲስ ቫይረስ እንደ መሆኑ መጠን የ COVID-19 የረጅም ጊዜ ጉዳቶችን ገና አላውቅንም። ክትባት መውሰድ ከቫይረሱ ለመከላከል ከሁሉ የተሻለው መከላከያችን ነው። ወጣት እና ጤነኛ ቢሆንም እንኳን የ COVID-19 ን ክትባት ማግኘት አለብዎት።

የ COVID-19 ልዩ ዘር ምንድን ነው?

ቫይረሶች ከሰው ወደ ሰው በሚዛመቱበት ጊዜ ይለዋወጣሉ (ይቀያየራሉ)። 'ልዩ ዘር' (variant) በሚውቴሽን አማካኝነት የሚገኝ ቫይረስ ነው። በጊዜ ሂደት አንዳንድ የተለያዩ ዝርያዎች ይጠፋሉ ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ በማኅበረሰቡ ውስጥ መስፋፋታቸውን ቀጥለዋል ።

Centers for Disease Control and Prevention (CDC፣ የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል) (በእንግሊዝኛ ብቻ) አሳሳቢ የሆኑ የቫይረሱ ተለዋጮችን በተመለከተ ለይቶ ያሳውቃል። በአሁኑ ጊዜ ፤ በርካታ የተለያዩ የቫይረሱ ተለዋጮች አሳሳቢ ሆነዋል ምክንያቱም በፍጥነትና በቀላሉ ስለሚዛመቱ ፤ ተጨማሪ የ COVID-19 ኢንፌክሽኖችን ስለሚያስከትሉ ነው።

የ COVID-19 ክትባቱ የተለያዩ ተለዋጭ ዝርያዎችን በመቃወም ይሰራል?

በአሁኑ ጊዜ እኛ በ U.S. ያሉን የ COVID-19 ክትባቶች ከባድ ሕመምን፣ ሆስፒታል መተኛትን እና ሞትን ለመከላከል፣ በተለዋዋጮች ላይም ቢሆን እንዲሁ በጥሩ ሁኔታ እየሰሩ ነው። ሆኖም፣ የህዝብ ጤና ባለሙያዎች ከቀላል እና መካከለኛ የ COVID-19 ህመም አንጻር፣ በተለይም ከፍተኛ-ተጋላጭነት ባለው ህዝብ መካከል የቀነሰ መከላከል እየተመለከቱ ነው።

የዘመኑት ማጠናከሪያዎች በሽታ የመከላከል አቅምን ለመጨመር እና ከኦሚክሮን ዝርያ ምርጥ ጥበቃን ለመስጠት የተፈጠሩ ናቸው። ለምርጥ ጥበቃ ሁሉንም የተመከሩ የሚገኙ ዶዞችን መውሰድ አስፈላጊ ነው።

ክትባት እርስዎን፣ የሚወድዋቸውንና ማኅበረሰብዎን ለመጠበቅ ከሁሉ የተሻለው መንገድ ነው። ከፍተኛ የክትባት ሽፋን የቫይረሱን ስርጭት የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ አዳዲስ የቫይረስ ተለዋጭ ዓይነቶች እንዳይፈጠሩ ይረዳል።

ክትባቶቹ አስተማማኝ መሆናቸውን እንዴት ልናውቅ እንችላለን?

የ COVID-19 ክትባቶች ደሕንነታቸዉ የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ Centers for Disease Control & Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል) የሀገሪቱን የክትባት ደሕንነት የመቆጣጠር አቅምን አስፋፍቷል፣ አጠናክሯል። በዚህ ምክንያት፣ የክትባት ደሕንነት ባለሙያዎች የ COVID-19 ክሊኒካል ሙከራ ግዜ ላይ ላይታዩ የሚችሉ ጉዳዮችን ሊቆጣጠር እና ሊያዉቁ ይችላሉ።

Johnson & Johnson ክትባት ላይ ምን እየተካሄደ ነው?

ከ ዲሴምበር 2021 ጀምሮ፣ የ Washington State Department of Health (DOH፣ የጤና መምሪያ) ከ ባለ አንድ-መርፌው Johnson & Johnson (J&J) ክትባት ይልቅ (Pfizer-BioNTech ወይም Moderna) የ mRNA COVID-19 ክትባት ለማግኘት እንዲመርጡ ይመክርዎታል። 

ይህ ማሻሻያ ከ J&J ክትባትን ተከትሎ የተከሰቱ ሁለት ያልተለመዱ ሁኔታዎች አዲስ ውሂብ ከቀረበ በኋላ የ Centers for Disease Control and Prevention (የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል) መመሪያዎች ተከትሏል።

እነዚህ ሁኔታዎች ከ J&J የ COVID-19 ክትባቶች ጋር የተያያዙ ናቸው፣ ከ Pfizer ወይም Moderna ክትባቶች ጋር አይያያዙም። በአሁኑ ወቅት የ COVID-19 ክትባት ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች፣ DOH የ Moderna እና Pfizer ክትባቶችን ይመክራል። ሆኖም፣ ሁለቱንም እነዚያን ክትባቶች ለመውሰድ ካልቻሉ ወይም ፈቃደኛ ካልሆኑ የ J&J ክትባት አሁንም ይገኛል። እባክዎ ስለ አማራጮችዎ ለመነጋገር የጤና እንክብካቤ አቅራቢ ያግኙ። 

የ J&J የ COVID-19 ክትባትን ባለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ከወሰዱ ወይም የ J&J የ COVID-19 ክትባትን ለመውሰድ እቅድ ካልዎት፣ በ TTS ምክንያት የሚከሰት የደም መርጋት ዓይነት የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን ይወቁ። እነዚህም ከባድ የራስ ምታት፣ የሆድ ህመም፣ የእግር ህመም፣ እና/ወይም የትንፋሽ ማጠርን ያካትታሉ። ከእነዚህ ምልክቶች አንዱ ካጋጠመዎት፣ እባክዎን ወዲያውኑ የህክምና እርዳታ ያግኙ።

ማንኛውም ዓይነት የ COVID-19 ክትባት ከወሰዱ በኋላ ባለው የመጀመሪያ ሳምንት ውስጥ፣ ትኩሳት፣ የራስ ምታት፣ ድካም እና የመገጣጠሚያ/የጡንቻ ህመምን ጨምሮ ከቀላል እስከ መካከለኛ ምልክቶች መታየት የተለመደ ነው። እነዚህ የጎንዮሽ ጉዳቶች ብዙውን ጊዜ ክትባት ከወሰዱ በሶስት ቀናት ውስጥ የሚጀምሩ ሲሆን ለተወሰኑ ቀናት ብቻ ሊቆዩ ይገባል።

አንድ ክትባት የ FDA ፈቃድ አለው ሲባል ምን ማለት ነው?

ሙሉ ተቀባይነት ለማግኘት፣ FDAው ድንገተኛ የአጠቃቀም ፈቃድ ከማግኘት ይልቅ ረዘም ላለ ጊዜ መረጃዎችን ይገመግማል። አንድ ክትባት ሙሉ በሙሉ ፈቃድ እንዲያገኝ፣ መረጃው በክትባት ምርት ላይ ከፍተኛ የሆነ የደህንነት፣ ውጤታማነት እና የጥራት ቁጥጥር ማሳየት አለበት።

የአስቸኳይ ጊዜ አጠቃቀም ፈቃድ (EUA) ሙሉ ፈቃድ ከማግኘት በፊት FDA ውን በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ ውስጥ አንድን ምርት ለማቅረብ ይፈቅድለታል። የ EUA ዓላማ ለረጅም ጊዜ መረጃዎችን ከመመርመር በፊት የሰዎችን ሕይወት ለማዳን ክትባቶችን ማግኘት እንዲችሉ ማድረግ ነው። ይሁን እንጂ EUA አሁንም ቢሆን በጥቂት ጊዜ ውስጥ በክሊኒካዊ መረጃዎች ላይ ጥልቅ ምርምር ማድረግ ያስፈልጋል። በ FDA የተሰጠ ማንኛውም EUA በ Western States Pact (የምዕራብ ግዛቶች ስምምነት) (እንግሊዘኛ ብቻ) ውስጥ በ Scientific Safety Review Workgroup (የሳይንሳዊ ደህንነት ፍተሻ ቡድን) ተጨማሪ ምርመራ ይደረግበታል።

የምዕራብ ግዛቶች ስምምነት ምንድን ነው?

ይህ የቡድን ስራ በክትባት ደህንነት ዙሪያ ሌላ የባለሙያ ግምገማ ደረጃን አቅርቧል። የፓኔል ውይይቱ በሁሉም አባል የሆኑ ግዛቶች የተመረጡ ባለሙያዎችን እና በክትባት እና በህዝብ ጤና ላይ የሰለጠኑ በብሄራዊ ደረጃ እውቅና ያላቸው ሳይንቲስቶችን ያካተተ ነበር። COVID-19 የጤና ድንገተኛ አደጋ ተብሎ ሲታወጅ ከምዕራባዊ ግዛቶች ጋር በቅርበት ለመቀናጀት እና ትብብር ለማድረግ፣ ይህ የፓኔል ውይይት በአሁኑ ጊዜ በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ ስላሉን አራት ክትባቶች ከፌደራል ግምገማዎች ጋር ሁሉንም በግልጽ የሚገኙ ውሂቦችን በአንድ ጊዜ ገምግሟል። ወደ ወረርሺኙ አዲስ የማገገሚያ ምዕራፍ ስንሸጋገር፣ የ Western States Pact (የምዕራብ ግዛት ስምምነት) ፈርሷል፣ እና በምዕራባዊ ግዛቶች ያሉ ሁሉም የክትባት አጠቃቀም ፈቃድ በ Food & Drug Administration (FDA፣ የምግብ እና መድሃኒት አስተዳደር) የሚወሰን ሲሆን የክትባት ምክሮች ከ Center for Disease Control and Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል) ይመጣሉ።

የ Western States Scientific Safety Review Workgroup ግኝቶችን ያንብቡ፡-

የ COVID-19 ክትባት በሰውነቴ ውስጥ እንዴት ይሠራል?

በሰውነትዎ ውስጥ ክትባቱ እንዴት እንደሚሰራ ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ።

የ mRNA ክትባቶች (የ Pfizer እና Moderna የ COVID-19 ክትባቶች)

ከተገኙት ክትባቶች መካከል ሁለቱ መልእክተኛ RNA (mRNA) ክትባቶች ይባላሉ።

mRNA ክትባት ህዋሳትዎ ምንም ጉዳት የሌለው የኮሮና ቫይረስ የፕሮቲን ቁራጭ እንዴት እንደሚሠሩ ያስተምራል። የሰውነትዎ በሽታን የመከላከል ስርዓት ፕሮቲኑ እንግዳ እንደሆነ ያያል፣ እናም ሰውነትዎ ፀረ እንግዳ አካላትን መስራት ይጀምራል። እነዚህ ፀረ እንግዳ አካላት ወደፊት በበሽታው ከተያዙ COVID-19 ን እንዴት እንደሚዋጉ ያስታውሳሉ። ክትባት ሲወስዱ በሽታውን ሳይዙ ለ COVID-19 መከላከያ ይገነባሉ። mRNA ሥራውን ካከናወነ በኋላ በፍጥነት ይሰባበራል፤ እንዲሁም በጥቂት ቀናት ውስጥ ሰውነቱ ያጸዳዋል።

ቫይራል ቬክተር ክትባቶች (የ Johnson & Johnson የ COVID-19 ክትባት)

ከ COVID-19 ክትባቶች አንዱ ቫይራል ቬክተር ክትባት ይባላል።

የቬክተር ክትባቶች የሚሰሩት በተዳከመ የቫይረስ ስሪት (COVID-19 ከሚያስከትለው የተለየ ቫይረስ) ነው። እነዚህ ክትባቶች ህዋሳትዎ ምንም ጉዳት የሌለው የኮሮና ቫይረስ የፕሮቲን ቁራጭ እንዴት እንደሚሠሩ ያስተምራል። የሰውነትዎ በሽታን የመከላከል ስርዓት ፕሮቲኑ እንግዳ እንደሆነ ያያል፣ እናም ፀረ እንግዳ አካላትን መስራት ይጀምራል። ሳይታመሙ በ COVID-19 ወደፊት ከሚመጣው ኢንፌክሽን እንዴት እንደሚጠብቅዎት ሰውነትዎት ይማራል።

ያለን የቬክተር ክትባት አንድ መጠን ነው። ከፍተኛ ጥበቃ ለማግኘት በተለምዶ ከመጠኑ በኋላ ሁለት ሳምንታት ያህል ይወስዳል።

ንዑስ የፕሮቲን ክትባቶች (የ Novavax COVID-19 ክትባት)

በ Food & Drug Administration (FDA፣ የምግብ እና መድሃኒት አስተዳደር) ከተፈቀዱት የ COVID-19 ክትባቶች አንዱ ንዑስ የፕሮቲን ክትባት ነው። ንዑስ የፕሮቲን ክትባቶች COVID-19 የሚያስከትለውን (በህይወት ያለ ቫይረስን ሳይጠቀም) አነስተኛ ቫይረሶችን (ፕሮቲኖች) ክትባቱ በሰውነት ውስጥ በተሻለ ሁኔታ እንዲሰራ ለመርዳት የታሰበ ተጨማሪ ይዘዋል። አንድ ጊዜ የሰውነት በሽስታ ተከላካይ ስርዓትዎ ለፕሮቲን ዘለላው እንዴት ምላሽ እንደሚሰጥ ካወቀ፣ ከዚያ ለእውነተኛው ቫይረስ በፍጥትነት ምላሽ መስጠት ይችላል እና ከ COVID-19 ይጠብቅዎታል። ንዑስ ክትባቶች COVID-19 በሚያስከትለው ቫይረስ መጠቃት አይችሉም እና ከእኛ DNA ጋር መስተጋብር አይፈጥሩም።

የቫይረሱ ንዑስ ክትባት የሚገኘው በሁለት-ዶዝ ክትባት ነው። አብዛኛውን ጊዜ ሙሉ በሙሉ ለመጠበቅ ከሁለተኛው ዶዝ በኋላ ሁለት ሳምንቶች ገደማ ይወስዳል።

አንዳንድ ጊዜ ክትባት መለስተኛ ትኩሳት ወይም እንደ ጉንፋን የመሰለ ምልክቶችን ያስከትላል፣ ግን እነዚህ ጎጂ አይደሉም።

ለበለጠ መረጃ፣ እነዚህን ምንጮች ይመልከቱ፡- የ COVID-19 ክትባቶች አጭር ገለጻ (PDF) እና የ COVID-19 ክትባቶች፦ ማወቅ ያለብዎት ነገሮች (PDF)

በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉ በርካታ ሰዎች ኮሮናቫይረስን መዋጋት ከቻሉ፣ ቫይረሱ የሚሄድበት ቦታ አይኖረውም። ይህ ማለት የበሽታውን ስርጭት በፍጥነት መግታት እና ይህን ዓለም አቀፍ በሽታ ለማስቆም ወደ መጨረሻው ደረጃ እንቃረባለን ማለት ነው።

የ COVID-19 ክትባቶች እንዴት ይሰራሉ?

ይህ አጭር ቪዲዮ የ COVID ክትባቶች እንዴት እንደሚሰሩ ያብራራል።

የ mRNA ክትባት ምንድን ነው?

ተላላኪ RNA ወይም mRNA ክትባት አዲስ ዓይነት ክትባት ነው። mRNA የተባለው ክትባት ሴሎቻችንን ምንም ጉዳት የሌለውን የ"ስፓይክ ፕሮቲን"ን እንዴት መሥራት እንደሚቻል ያስተምራሉ። ስፓይክ ፕሮቲን በኮሮናቫይረስ ከላይ የምናየው ነገር ነው። የእናንተ በሽታ ተከላካይ ሕዋሳት ፕሮቲኑ እዚያ ቦታ ላይ መኖር እንደማይገባው እና ሰውነታችሁ በሽታ የመከላከል አቅም መገንባት እና የፀረ እንግዳ አካላትን መሥራት እንደሚጀምር ያደርጋል። ይህም "በተፈጥሮ" የ COVID-19 ኢንፌክሽን ሲያጋጥመን ከሚከሰቱ ነገሮች ጋር ተመሳሳይ ነው። mRNA ሥራውን ካከናወነ በኋላ በፍጥነት ይሰባበራል፤ እንዲሁም በጥቂት ቀናት ውስጥ ሰውነቱ ያጸዳዋል።

ምንም እንኳ ባለፉት ጊዜያት ለሌሎች የህክምና እና የእንስሳት ህክምና ዓይነቶች mRNAን የተጠቀምን ቢሆንም ይህን ዘዴ በመጠቀም ክትባቶችን መፍጠር በሳይንስ ውስጥ ትልቅ ሽቅብ ከመሆኑም በላይ ወደፊት ክትባቶችን በቀላሉ ለመፍጠር ያስችላል ማለት ሊሆን ይችላል።

ስለ mRNA ክትባቶች እንዴት እንደሚሰሩ በ CDC ድረ-ገፅ ላይ ተጨማሪ ያንብቡ (ድረ ገጹ ላይ በእንግሊዘኛ ብቻ)።

ቫይራል ቬክተር ክትባት ምንድን ነው?

ይህ ዓይነቱ ክትባት የተለየ የተዳከመ አይነት የቫይረስ ተለዋጭ (የ "ቬክተር") የሚጠቀም ሲሆን ይህ ቫይረስ ለሴሎችዎ መመሪያ ይሰጣል። ቬክተሩ ወደ አንድ ሕዋስ ገብቶ በሴሉ ማሽን በመጠቀም የ COVID-19 ስፓይክ ፕሮቲንን ምንም ጉዳት የሌለው ንጣፍ አድርጎ ይፈጥራል። ሴሉ በውስጡ ያለውን ስፓይክ ፕሮቲን የሚያሳይ ሲሆን የሰውነትዎ በሽታ ተከላካይ ሕዋሳት ምጣኔ ውስጡ እንደሌለ ያያል። የሰውነትዎ በሽታ ተከላካይ ሕዋሳት ፀረ እንግዳ አካላትን መሥራትና ሌሎች በሽታ ተከላካይ ሕዋሳት ኢንፌክሽን ነው ብለው የሚያስቡትን ነገር እንዲከላከሉ ማድረግ ይጀምራሉ። ሳይታመሙ በ COVID-19 ወደፊት ከሚመጣው ኢንፌክሽን እንዴት እንደሚጠብቅዎት ሰውነትዎት ይማራል።

ንዑስ የፕሮቲን ክትባት ምንድን ነው?

በ Food & Drug Adminstration (FDA፣ የምግብ እና መድሃኒት አስተዳደር) ከተፈቀዱት የ COVID-19 ክትባቶች አንዱ ንዑስ የፕሮቲን ክትባት ነው። ንዑስ የፕሮቲን ክትባቶች COVID-19 የሚያስከትለውን (በህይወት ያለ ቫይረስን ሳይጠቀም) አነስተኛ ቫይረሶችን (ፕሮቲኖች) ክትባቱ በሰውነት ውስጥ በተሻለ ሁኔታ እንዲሰራ ለመርዳት የታሰበ ተጨማሪ ይዘዋል። አንድ ጊዜ የሰውነት በሽስታ ተከላካይ ስርዓትዎ ለፕሮቲን ዘለላው እንዴት ምላሽ እንደሚሰጥ ካወቀ፣ ከዚያ ለእውነተኛው ቫይረስ በፍጥትነት ምላሽ መስጠት ይችላል እና ከ COVID-19 ይጠብቅዎታል። ንዑስ ክትባቶች COVID-19 በሚያስከትለው ቫይረስ መጠቃት አይችሉም እና ከእኛ DNA ጋር መስተጋብር አይፈጥሩም።

ደጋፊ ምንድን ነው?

በ Novavax ውስጥ ያለው ደጋፊ የሰውነትን በሽታ የመከላከል ምላሽ በተጨማሪ እንዲጠነክር ለመደገፍ የሚረዳ ተጨማሪ ነው።

ክትባቶቹ ውስጥ ምን አይነት ግብዓቶች አሉ?

በ COVID-19 ክትባቶች ውስጥ የሚገኙት ንጥረ ነገሮች ለክትባት በጣም የተለመዱ ናቸው። እነሱ የ mRNA ንቁውን ንጥረ ነገር የሚከላከሉ፣ በሰውነት ውስጥ በተሻለ ሁኔታ እንዲሠሩ የሚያግዙ እና በማከማቸት እና በማጓጓዝ ጊዜ ክትባቱን የሚከላከሉ የተቀየረ አድኖቫይረስ ንቁ ንጥረ ነገርን ቅባት፣ ጨዎች እና ስኳሮች ከመሳሰሉ ሌሎች ንጥረ ነገሮች ጋር ይዘዋል።

Novavax የ COVID-19 ክትባት ተጨማሪን፣ ከስቦች እና ስኳር ጋር አብሮ የያዘ የፕሮቲን ንዑስ ላይ የተመሰረተ ክትባት ነው። ይህ ክትባት mRNA አይጠቀምም።

የ Pfizer፣ Moderna, Novavax እና Johnson and Johnson ክትባቶች የማያካትቷቸው ነገሮች የሰው ህዋሳት (የፅንስ ሴሎችን ጨምሮ)፣ የ COVID-19 ቫይረስ፣ ላቴክስ፣ተጠባቂዎች ወይም የአሳማ ምርቶች ወይንም ጄልቲን ጨምሮ ማንኛውም የእንስሳ ምርቶች በውስጣቸው አይይዙም። ክትባቶቹ በእንቁላል ውስጥ አያድጉም እና ምንም አይነት የእንቁላል ውጤቶችን አይዙም

ስለ ንጥረ ነገሮች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህንን የጥያቄ እና መልስ ድረ-ገጽ ከፊላዴልፊያ የልጆች ሆስፒታል (በእንግሊዝኛ ብቻ) ይመልከቱ። በተጨማሪም የ Pfizer ((ድረ ገጹ ውስጥ በእንግሊዘኛ ብቻ)፣ Moderna (ድረ ገጹ ውስጥ በእንግሊዘኛ ብቻ)፣ Novavax (ድረ ገጹ ውስጥ በእንግሊዘኛ ብቻ) እና Johnson & Johnson (ድረ ገጹ ውስጥ በእንግሊዘኛ ብቻ) የመረጃ ገጾች ውስጥ የሙሉ ንጥረ-ነገሮቹን ዝርዝር ከፈለጉ ማግኘት ይችላሉ።

የ Johnson & Johnson ክትባት የፅንስ ሕብረ ሕዋስ አለው?

የ Johnson & Johnson የ COVID-19 ክትባት እንደ ሌሎች ብዙ ክትባቶች ተመሳሳይ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተፈጠረ ነው። የፅንስ ወይም የፅንስ ህዋሳትን ክፍሎች አልያዘም። የክትባቱ አንዱ ክፍል ከ 35 ዓመታት በፊት በቀጠሮ ከተደረጉ ውርጃዎች ከተገኙ ሕዋሳት በላብራቶሪ ውስጥ እንዲጎለብቱ ከተደረጉ የህዋሳት ቅጂዎች የተሠራ ነው። ከዚያን ጊዜ አንስቶ ፤ የእነዚህ ክትባቶች ሴሎች መስመር በቤተ ሙከራ ውስጥ ተጠብቀው የቆዩ ሲሆን እነዚህን ክትባቶች ለመሥራት ተጨማሪ የፅንስ ሴሎች ምንጭ አያስፈልግም። ይህ ለተወሰኑ ሰዎች አዲስ መረጃ ሊሆን ይችላል። ሆኖም፣ የፈንጣጣ፣ ሩቤላ እና ሄፓታይቲስ ኤ ክትባቶች በተመሳሳይ መንገድ የተዘጋጁ ናቸው።

የ COVID-19 ክትባት መካንነት ያስከትላል?

ክትባቶቹ የመውለድ ወይም የስንፈተ ወሲብ ችግር እንደሚያስከትሉ የሚያሳይ ሳይንሳዊ ማስረጃ የለም። ክትባቱ ወደ ሰውነትዎ ሲገባ፣ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ጸረ እንግዳ አካሎችን ለመስራት ከበሽታ የመከላከል ስርአትዎ ጋር ይሰራል። ይህ ሂደት የመራቢያ አካላትዎ ላይ ጣልቃ አይገባም።

የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማእከል (CDC) (በእንግሊዘኛ ብቻ)American College of Obstetricians and Gynecologists (ACOG) (በእንግሊዘኛ ብቻ)፣ እና Society for Maternal-Fetal Medicine (SMFM) (PDF) (በእንግሊዝኛ ብቻ) ለነፍሰ ጡር፣ አጥቢ ወይም ለማርገዝ ዕቅድ ላላቸው ሰዎች የ COVID-19 ክትባት እንዲወስዱ ይመክራሉ። የ COVID-19 ክትባትን የወሰዱ ብዙ ሰዎች ከዚያ በኋላ እርጉዝ ሆነዋል ወይም ጤናማ ሕፃናትን ወልደዋል።

በአሁኑ ጊዜ ማንኛውም ክትባቶች የ COVID-19 ክትባቶችን ጨምሮ የወንድ የመራባት ችግር እንደሚያስከትሉ የሚያሳይ ምንም ማስረጃ የለም። በ 45 ጤናማ ወንዶች ላይ በቅርቡ በተደረገ አነስተኛ ጥናት (እንግሊዝኛ) የ mRNA COVID-19 ክትባት በወሰዱ (ማለትም Pfizer-BioNTech ወይም Moderna) ላይ ከክትባት በፊት እና በኋላ የወንድ ዘር ባህሪያትን እንደ ብዛት እና እንቅስቃሴ ተመልክቷል። ተመራማሪዎቹ ከክትባት በኋላ በእነዚህ የወንዴ ዘር ባሕርያት ላይ የጎላ ለውጥ አላገኙም።

በህመም ምክንያት የሚመጣ ትኩሳት ከጤናማ ወንዶች የወንዴ ዘር ምርት የአጭር ጊዜ ዘር መቀነስ ምክንያት ጋር ሊገናኝ ይችላል። ትኩሳት የ COVID-19 ክትባት ጊዜያዊ የጎንዮሽ ጉዳት ሊሆን ቢችልም ከ COVID ክትባት በኋላ ትኩሳት በዘሩ ምርት ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የሚያሳይ ምንም ማስረጃ የለም።

ለበለጠ መረጃ የ CDC ን ልጅ መውለድ ለሚፈልጉ ሰዎች የ COVID-19 ክትባቶች መረጃ (ድረገጹ በእንግሊዘኛ ብቻ) ይመልከቱ። በተጨማሪም ስለ ክትባቶቹ የ CDC የ COVID-19 ክትባቶችን ድረ-ገፅ (ድረገጹ በእንግሊዘኛ ብቻ) መመልከት ይችላሉ።

ክትባቱን ከተቀበሉ በኋላ ምን ዓይነት ምልክቶች የተለመዱ ናቸው?

እንደ ሌሎቹ የተለመዱ ክትባቶች ሁሉ በጣም የተለመዱት የጎንዮሽ ጉዳቶችም የክንድ ህመም፣ ድካም፣ ራስ ምታትና የጡንቻ ሕመም ናቸው።

እነዚህ ምልክቶች ክትባቱ እየሠራ እንዳለ የሚጠቁሙ ምልክቶች ናቸው። በ Pfizer እና በ Moderna ምርመራዎች ላይ እነዚህ የጎንዮሽ ጉዳቶች አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰቱት ክትባቱን ከወሰዱ በሁለት ቀናት ውስጥ ሲሆን ለአንድ ቀን ያህል ይቆያሉ። ከሁለተኛው ክትባት በኋላ የጎንዮሽ ጉዳቶች ከመጀመሪያው ክትባት ይልቅ የተለመዱ ናቸው። በ Johnson & Johnson የሕክምና ምርመራ ላይ የጎንዮሽ ጉዳቶች በአማካይ ከአንድ እስከ ሁለት ቀን ሊቆዩ ይችላሉ።

ለሦስቱም ክትባቶች ከ 55 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሪፖርት የማድረግ አጋጣሚያቸው ከወጣቶች ያነሰ ነው።

በኢንተርኔት ወይም በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ ስለሚደርሰው የጎንዮሽ ጉዳት አንዳንድ ወሬዎች ይመለከቱ ይሆናል። የጎንዮሽ ጉዳት እንዳለ በሚያስቡበት ጊዜ ሁሉ የዚያ ወሬ ምንጭ ምን እንደሆነ ለማወቅ ጥረት ያድርጉ።

የ COVID-19 ክትባትን ከወሰድኩ በኋላ ብታመም ምን ይከሰታል?

እንደ ሌሎቹ የተለመዱ ክትባቶች ሁሉ፤ የ COVID-19 ክትባት አብዛኛውን ጊዜ የጎንዮሽ ጉዳት ያስከትላል። ለምሳሌ ያህል፡- የክንድ ህመም፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታት ወይም ከክትባት በኋላ የድካም ስሜት እና የመሳሰሉትን ሊያስከትል ይችላል። እነዚህ ክትባቱ በትክክል እየሠራ ለመሆኑ የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው። የ COVID-19 ክትባት ከወሰዱ በኋላ ሊኖሩ ስለሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች የበለጠ ይማሩ።

ክትባቱን ካገኙ በኋላ ከታመሙ ፤ ይህንን አሉታዊ ሁኔታ ለ Vaccine Adverse Event Reporting System (VAERS፣ የክትባት አሉታዊ ክስተት ሪፖርቲንግ ሲስተም) (በእንግሊዘኛ ብቻ) ሪፖርት ማድረግ ይኖርብዎታል። "አሉታዊ ክስተት" ከክትባት በኋላ የሚከሰት ማንኛውም የጤና ችግር ወይም የጎንዮሽ ጉዳት ነው። ስለ VAERS ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት "VAERS ምንድን ነው?" የሚለውን ከታች ይመልከቱ

VAERS ምንድን ነው?

VAERS የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (CDC) እና የምግብና የመድሀኒት አስተዳደር (FDA) የሚመሩበት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ዘዴ ነው። VAERS ከክትባት ጋር ግንኙነት ያላቸውን ችግሮች ለመለየት ሊረዱ ይችላሉ።

ማንኛውም ሰው (የጤና አገልግሎት አቅራቢ፣ ታካሚ፣ ተንከባካቢ) ሊፈጠሩ የሚችሉ አሉታዊ ምላሾችን በ VAERS ላይ ሪፖርት ማድረግ ይችላል (በእንግሊዘኛ ብቻ)።

ስርዓቱ ገደቦች አሉት። የ VAERS ሪፖርት ክትባቱ ምላሻውን ወይም ውጤቱን አስከትሏል ማለት አይደለም። ይህ ማለት በመጀመሪያ ክትባቱ ተከስቷል ማለት ብቻ ነው።

ሳይንቲስቶች አንድን ችግር መመርመር ያለባቸው አዝማሚያዎችን ወይም ምክንያቶችን እንዲያስተውሉ ለመርዳት ነው። በክትባቱ የተነሳ በዝርዝር የተረጋገጡ ውጤቶች አይደሉም።

ለ VAERS ሪፖርት በሚያደርጉበት ጊዜ፣ CDC እንዲሁም FDA የጤና ችግሮችን ለይተው እንዲያውቁና ክትባቶቹ አስተማማኝ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ይረዷቸዋል። ማንኛውም ጉዳይ ቢነሳ እርምጃ ይወስዳሉ እንዲሁም ሊነሱ ስለሚችሉ ጉዳዮች ለጤና ተቋማት ያሳውቃሉ።

በ COVID-19 ከተያዝኩ የ COVID-19 ክትባት ማግኘት እችላለሁ?

አዎ፣ የ Advisory Committee on Immunization Practices (ACIP፣ የክትባት ተግባራት አማካሪ ኮሚቴ) ከዚህ ቀደም በ COVID-19 ለተያዘ ማንኛውም ሰው ክትባቱን እንዲወስድ ይመክራል።

መረጃው በበሽታው ከተያዙ በኋላ ባሉት 90 ቀናት ውስጥ በ COVID-19 እንደገና መያዝ ያልተለመደ መሆኑን ያሳያል፣ ስለዚህ የተወሰነ ጥበቃ (ተፈጥሯዊ የበሽታ መከላከያ ይባላል) ሊኖርዎት ይችላል። ሆኖም የተፈጥሮ በሽታ መከላከያ ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ አናውቅም።

በአሁኑ ጊዜ COVID-19 ያለባቸው ሰዎች የተሻለ ስሜት እስኪሰማቸውና የብቸኝነት ጊዜያቸው እስኪጠናቀቅ ድረስ ክትባት እስኪያገኙ መጠበቅ ይኖርባቸዋል።

በቅርቡ ለ COVID-19 የተጋለጡ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች ርቀው በገለልተኝነት መቆየት ከቻሉ ራስን የማግለል ጊዜያቸው እስኪያልቅ ድረስ ክትባቱን ለማግኘት መጠበቅ አለባቸው። ሌሎችን የመበከል ከፍተኛ አደጋ ካለ፣ በሽታውን ከማሰራጨት ለመከላከል በገለልተኛነታቸው ወቅት ሊከተቡ ይችላሉ።

ለለይቶ ማቆያ እና ለኳራንታይን መመርያዎች እባክዎ የ COVID-19 ለይቶ ማቆያ እና ኳራንታይን ገጻችንን ይመልከቱ።

ባለፉት ጊዜያት ለክትባት አለርጂ ካለብኝ የ COVID-19 ክትባትን ማግኘት እችላለሁ?

ክትባቱ ከባድ የአለርጂ ምላሽ የታወቀ ታሪክ ላለባቸው ሰዎች መሰጠት የለበትም፤ ለምሳሌ፡- አናፊላክሲስ፣ ቀደም ሲል ለነበረ የ mRNA ዶዝ ወይም የቫይራል ቬክተር ክትባት ወይንም ለማንኛውም የ Pfizer-BioNTech/comirnaty (እንግሊዝኛ ብቻ)፣ Moderna/Spikevax (እንግሊዝኛ ብቻ) ፣Novavax (ድረ ገጹ ውስጥ በእንግሊዘኛ ብቻ) ወይም Johnson & Johnson–Janssen (እንግሊዝኛ ብቻ) የ COVID-19 ክትባቶች ንጥረ-ነገሮች ።

ለሌሎች ክትባቶች ወይም በመርፌ ለሚሰጡ ሕክምናዎች ከባድ አለርጂ ያለባቸው ሰዎች ክትባቱን ማግኘት ይችሉ ይሆናል። ይሁን እንጂ፣ አቅራቢዎች የአደጋ ምዘናዎችን በማድረግ እና ሊከተሉ ስለሚችሉ አደጋዎች ምክር መስጠት ይኖርባቸዋል። በሽተኛው ክትባቱን ለመውሰድ ከወሰነ፣ አቅራቢው ለ 30 ደቂቃ ያህል ለአፋጣኝ ምላሾች ክትትል ማድረግ ይኖርበታል።

የ Advisory Committee on Immunization Practices (ACIP) ሌሎች ታካሚዎችን በሙሉ ክትባቱን ከወሰዱ በኋላ ቢያንስ ለ15 ደቂቃ ያህል ለአለርጂ ምላሽ እንዲመለከቱ ሐሳብ አቅርቧል። ለተጨማሪ መረጃ የ ACIP ን የ mRNA ክትባቶች ጊዜያዊ ክሊኒካዊ ጉዳዮች (በእንግሊዘኛ ብቻ) ይመልከቱ።

የክትባት መስፈርቶች

የ COVID-19 ክትባት አስፈላጊ ነው?

የ COVID-19 ክትባትን ማግኘት የእርስዎ ምርጫ ይሆናል ፤ ነገር ግን አንዳንድ አሠሪዎች, ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች የግድ ያስፈልጋቸዋል።

ዋሽንግተን በአሁኑ ጊዜ የ COVID-19 ክትባት የሚያስፈልገው ለ፡-

እነዚህ ሠራተኞች እስከ ኦክቶበር 18፣ 2021 ድረስ የ COVID-19 ን (ተከታታዩን ክትባት ከጨረሱ ቢያንስ ከሁለት ሳምንታት በኋላ) ክትባት ሙሉ በሙሉ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል። ይህ መስፈርት ኮንትራክተሮችን፣ ፈቃደኛ ሠራተኞችንና በእነዚህ ቦታዎች የሚሠሩ ሌሎች የሥራ ቦታዎችን ይጨምራል።

ከእነዚህ ቡድኖች በአንዱ ወይም በአሠሪዎ ወይም በትምህርት ቤት ውስጥ ከሆኑ የ COVID-19 ክትባት ያስፈልግዎታል። ምን ማድረግ እንዳለብዎ ለማወቅ ከመሥሪያ ቤትዎ የሰው ሀብት ክፍል፣ ከአሠሪዎ ወይም ከትምህርት ቤትዎ ጋር ይነጋገሩ። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በአሠሪው ወይም በኮሌጁ/በዩኒቨርሲቲው ፖሊሲ ውስጥ አይሳተፍም።

ክትባቱ እርስዎን እና በዙሪያዎ ያሉ ሌሎች ሰዎችን በ COVID-19 ከመያዝ ይጠብቅዎታል ፤ እንዲሁም ስለ ጥቅሞቹ ከሐኪምዎ ወይም ከክሊኒክዎ ጋር እንድትነጋገሩ እናበረታታዎታለን

ለ K-12 ሠራተኞች የ COVID-19 ክትባት መስፈርቱ ምንድን ነው?

በ ኦገስት18፣ 2021፣ የግዛቱ አስተዳዳሪ Inslee ሁሉም የህዝብና የግል K–12 የትምህርት ቤት ሠራተኞች የ COVID-19 ክትባትን ሙሉ በሙሉ እንዲያገኙ፣ ወይም እስከ ኦክቶበር 18፣ 2021 ድረስ ከሃይማኖታዊ ወይም ከሕክምና ነጻነትን እንዲያገኙ የሚያስገድድ መመሪያ አስታወቁ።

መመሪያው ለሁሉም በትምህርት አሰጣጡ ውስጥ ለሚገኙ ሰራተኞች (በእንግሊዘኛ ብቻ) ይሠራል፣ የሚከተሉትን ጨምሮ:-

  • የግል K-12 ትምህርት ቤቶች፣ የህዝብ K-12 ትምህርት ቤት አውራጃዎች፣ የቻርተር ትምህርት ቤቶች እና የትምህርት አገልግሎት አውራጃዎች ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች እና ተቋራጮች (ትዕዛዙ በመንግሥት-ጎሳ ትምህርት ኮምፓክት ትምህርት ቤቶች ወይም ተማሪዎች ላይ አይሰራም)፣
  • ከተለያዩ ቤተሰቦች ለተውጣጡ ልጆች አገልግሎት የሚሰጡ የሕፃናት እንክብካቤና የቅድመ ትምህርት ሰጪዎችን፣ እና
  • በከፍተኛ ትምህርት ውስጥ ያሉ ሠራተኞችን።

ለበለጠ መረጃ፣ ለ K -12 ትምህርት ቤት ሰራተኞች የ COVID-19 የክትባት ግዴታ ይመልከቱ፦ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች (PDF) (እንግሊዝኛ) (የህዝብ መመሪያ ተቆጣጣሪ ቢሮ) ይመልከቱ።

ከክትባት መስፈርቶች ነጻ መሆን የምችለው እንዴት ነው?

የእርስዎ አሠሪ ወይም ኮሌጅ/ዩኒቨርሲቲ የ COVID-19 ክትባት የሚጠይቅ ከሆነ ወይም በእያንዳንዱ አስተዳደር ክትባቱን ማግኘት ይጠበቅብዎታል። የ Jay Inslee ኦገስት 9 አዋጅ (እንግሊዘኛ) ወይም የኦገስት 18 አዋጅ (እንግሊዘኛ)፣ የክትባት ማስረጃ እንዴት እንደሚሰበስቡ፣ የፈቃደኛ ያለመሆን ፖሊሲ ያላቸው ከሆነ፣ እንዲሁም እርስዎም ላለመምረጥ ምን ማድረግ እንደሚያስፈልግዎት ለማወቅ አሠሪዎን ወይም ኮሌጅ/ዩኒቨርሲቲዎን ማነጋገር አለብዎት። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በአሠሪው ወይም በኮሌጁ/በዩኒቨርሲቲው ፖሊሲ ውስጥ አይሳተፍም።

ለ COVID-19 ክትባት ከ Department of Health (DOH፣ የጤና ጥበቃ መምሪያ) የነጻነት ቅጽ ማግኘት አያስፈልግዎትም። DOH ለ COVID-19 ክትባት የነጻነት ቅጾች የሉትም። የ Washington ግዛት Certificate of Exemption (COE፣ የነጻነት ሰርተፊኬት) በ K-12 ትምህርት ቤቶች፣ ቅድመ ትምህርት ቤቶች ወይም በህፃናት እንክብካቤ ውስጥ ለሚገኙ ህፃናት ከሚፈለገው በሽታ ነጻ ለማድረግ ለሚፈልጉ ወላጆች/ሞግዚቶች ብቻ ነው። በአሁኑ ጊዜ Washington ልጆች በትምህርት ቤት ወይም በልጆች እንክብካቤ እንዲማሩ COVID-19 ክትባት አይጠይቅም፤ ስለዚህ Certificate of Exemption (COE፣ የነጻነት ሰርተፊኬት) ላይ አይካተትም።

ትምህርት ቤት እና ህፃናት እንክብካቤ

ዕድሜያቸው ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች ክትባቱን ማግኘት ይችላሉን?

በዚህ ጊዜ፣ የ Pfizer-BioNTech (Pfizer) ክትባት እና የ Moderna የ COVID-19 ክትባት ስሪቶች እድሜያቸው 6 ወር እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ህጻናት ተፈቅዷል። በ Emergency Use Authorization (EUA፣ የድንገተኛ አጠቃቀም ፍቃድ) ስር ዕድሜያቸው ከ 12 ዓመት በላይ ለሆኑ የ Novavax ክትባት አለ።

ከ17 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች በህጋዊ መንገድ ከቤት ካልወጡ በስተቀር፣ ክትባቱን ለመውሰድ ከወላጅ ወይም ከአሳዳጊ ፈቃድ ሊያስፈልጋቸው ይችላል (በእንግሊዘኛ ብቻ)። ለበለጠ መረጃ በ Vaccinating Youth (የወጣቶች ክትባት) ላይ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ።

የወላጅ ፈቃድ ያላቸው ወይም ሕጋዊ በሆነ መንገድ መመረቅ የሚጠበቅባቸውን ለማወቅ ከክትባቱ ክሊኒክ ጋር ያረጋግጡ።

መንግሥት ለ K-12 ትምህርት ቤት መግቢያ የ COVID-19 ክትባት ያስፈልገዋል?

Department of Health (የጤና መምሪያ) ሳይሆን የ  Washington State Board of Health (የዋሽንግተን ግዛት የጤና ቦርድ) ከ K-12 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ላሉ ልጆች የክትባት መስፈርቶችን የማውጣት ስልጣን አለው Revised Code of Washington (RCW፣ የተሻሻለው የዋሽግተን ኮድ) 28A.210.140 ። በአሁኑ ሰዓት ለትምህርት ቤት ወይም ለህጻናት እንክብካቤ የ COVID-19 የክትባት መስፈርት አልተቀመጠም።

ልጄ COVID-19 ክትባታቸውን ሲያገኙ ሌሎች በሽታ ተከላካይ ሕዋሳትን ማግኘት ይችላልን?

በአሁኑ ጊዜ ሰዎች የ COVID-19 ክትባቱን በተመሳሳይ ቀን ጨምሮ ሌሎች ክትባቶች በ 14 ቀናት ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

በ COVID-19 ወረርሽኝ ምክንያት በ 2022-2023 የትምህርት ዓመት የትምህርት ቤት በሽታ የመከላከል መስፈርቶች ላይ እንደ ተለዋዋጭ ሁኔታ ይኖር ይሆን?

የግዛት የጤና ቦርድ በትምህርት ቤት በሽታ የመከላከል አቅም ላይ ለውጥ ማድረግ ይኖርበት እንደሆነና እንዳልሆነ ይወስናል። በዚህ ጊዜ በትምህርት ቤት በሽታየመከላከል የሚጠበቅባቸው ብቃቶችም ተመሳሳይ ይሆናሉ ። ልጆች በትምህርት ቤት የመጀመሪያ ቀን ላይ ከመገኘታቸው በፊት ክትባት የሚያስፈልጋቸውን ማሟላት ያስፈልጋቸዋል ።

ከክትባት በኋላ ያለው ሕይወት

ሙሉ በሙሉ ክትባት ሲባል ምን ማለት ነው?

የ COVID-19 ክትባት የመጀመሪያ ዙርን ካጠናቀቁ እንዲሁም በ CDC ለእርስዎ የሚመከረውን በጣም የቅርብ ጊዜ የማጠናከሪያ ዶዝ ከወሰዱ የ COVID-19 ክትባቶችዎ ላይ ወቅታዊ ኖት።

ሙሉ በሙሉ ክትባት ስለተከተብኩ አሁን ምን ማድረግ ይኖርብኛል?

አንዴ ሙሉ ለሙሉ ከተከተቡ በኋላ፡-

ለ COVID-19 ሙሉ ክትባት የወሰድኩ ከሆነ አሁንም ሌሎች ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይኖርብኛል?

ምንም እንኳን ሙሉ ክትባት ቢወስዱም፤ አሁንም የሚከተሉትን ማድረግ አለብዎት፦

  • የሚቻለዉን ያህል የበለጠ ጥበቃ ለማግኘት ማጠናከርያዎን በመዉሰድ “ወቅታዊ” መሆን።
  • የክፍሉን ደንቦች ማክበር። ከተማዎች፣ ወረዳዎች፣ የንግድ ቦታዎች፣ ዝግጅቶች እና ቦታዎች አሁንም ጭንብል ወይም የክትባት/የኔጌቲቭ ምርመራ ማረጋገጫ ሊጠይቁ ይችላሉ።
  • የ COVID-19 ምልክቶችን እያጋጠሙዎት ከሆነ ይመርመሩ
  • እርስዎ ለ COVID-19 ተጋልጠው ሊሆን ይችል እንደሆነ እርስዎን ለማሳወቅ እና ፖዘቲቭ ከሆኑ በስም-አልባነት ሌሎችን ያሳውቁ ዘንድ WA Notify ን ወደ ስማርት ስልክዎ ያክሉ። WA Notify ሙሉ በሙሉ የግል ነው እና እርስዎ ማን እንደሆኑ አያውቅም ወይም የት እንደሚሄዱ አይከታተልም።
  • በተቻለ ዶዝ ጥሩ ጥበቃ ለማግኘት በተጨናነቀ የሕዝብ የቤት ውስጥ ቦታዎች ውስጥ በሚገባ የሚገጥም ጭንብል ያድርጉ።
  • የ Centers for Disease Control & Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል) እና የጤና መምሪያ የጉዞ ምክሮችን ይከተሉ።
  • ለ COVID-19 ተጋላጭነት ከነበረዎት በኋላ አስፈላጊዉን የጥንቃቄ እርምጃ ይዉሰዱ፡-
ሁላችንም ከተከተልን ከአንድ ትልቅ ቡድን ጋር መሰብሰብ እችላለሁን?

ሙሉ ለሙሉ የተከተቡ በተጨማሪ ማጠናከርያቸዉን በመዉሰድ ወቅታዊ የሆኑ ሰዎች ከ COVID-19 በደንብ የተጠበቁ ናቸዉ። ሙሉ ለሙሉ ለተከተቡ ሰዎች መሰባሰብ ደሕንነቱ የተጠበቀ ነዉ።

እባክዎ ያስታዉሱ አንዳንድ ሰዎች መሰባሰብ ምቾት አይሰጣቸዉም - ዝቅተኛ ስጋት በሚፈጥሩ ቦታዎች ዉስጥም ቢሆን። ሌሎች አሁንም መተቃቀፍ እና የእጅ ሰላምታን ላይፈልጉ ይችላሉ። እና ያ ጥሩ ነዉ። እያንዳንዱ ሰዉ ከአዲሱ መደበኛ ሁኔታ ጋር እየተላመደ ነዉ እና ሁላችንም ደሕንነታችን ተጠብቆ እንዲቆይ እና የምንወዳቸውን ሰዎች መጠበቅ እንፈልጋለን።

የክትባት ማስረጃ ማሳየት አለብኝ?

በተወሰኑ አካባቢዎቸ፣ የንግድ ቦታዎች ወይም በተወሰኑ ዝግጅቶች ላይ የ COVID-19 ን ክትባት እንደወሰዱ ማረጋገጥ ሊኖርብዎ ይችላል።

ስለዚህ የክትባት ወረቀት ካርድዎን እንደ የልደት የምስክር ወረቀት ወይም ሌላ ኦፊሴላዊ ሰነድ አድርገው ይያዙት! ፎቶ ካነሱ በኋላ በቤት ውስጥ ያስቀምጡት። ስለ ክትባት ካርዶች እና የክትባት መዛግብት ተጨማሪ ያንብቡ

በ COVID-19 ክትባቶቼ ላይ ወቅታዊ ካለሆነኩስ?

በ COVID-19 ክትባቶችዎ እስካሁን ላይ ወቅታዊ ካለሆኑ፡-

  • በአቅራቢያዎ ያለ ክፍያ የሌለበት የ COVID-19 ክትባትን ይፈልጉ።
  • በተጨናነቀ ህዝባዊ የቤት ዉስጥ ቦታዎች በደንብ የሚገጥም ጭንብል ማድረጉን ያስቡበት።
  • ምልክቶች እያጋጠሙዎት ከሆነ የ COVID-19 ን ምርመራ ያድርጉ።
  • የሚጓዙ ከሆነ ከመጓዝዎ በፊተ እና በኋላ የ COVID-19 ን ምርመራ ያድርጉ።
  • ምናልባት እርስዎ ለ COVID-19 ተጋልጠዉ ከሆነ ለማሳወቅ እና የምርመራ ዉጤትዎ ፖዘቲቭ ከሆነ ለሌሎች በሚስጥር ለማሳወቅ WA Notify ን ስማርት ስልክዎ ላይ ያክሉ። WA Notify ሙሉ በሙሉ የግል ነው እና እርስዎ ማን እንደሆኑ አያውቅም ወይም የት እንደሚሄዱ አይከታተልም።
ክትባት ከወሰድኩ በኋላ አሁንም ከ COVID-19 መታመም እችላለሁን?

በተለዋጮችም ቢሆን፣ ኢንፌክሽኖች የሚከሰቱት ሙሉ በሙሉ በተከተቡ ትንሽ የሰዎች ክፍል ውስጥ ብቻ ነው። ሆኖም፣ ቀደምት ማስረጃዎች እንደሚያመለክቱት  (በእንግሊዘኛ ብቻ) በ COVID-19 የተያዙ ሰዎችን ሙሉ በሙሉ ክትባት ቢከተቡም ቫይረሱን ለሌሎች ሊያሰራጭ ይችላል።

ለ COVID-19 ምርመራ መረጃ፣ እባክዎ  ን ይመልከቱ።

ክትባት ከወሰድኩ በኋላ COVID-19 ን ማሰራጨት እችላለሁን?

ኢንፌክሽኖች ሙሉ ለሙሉ በተከተቡ እና የማጠናከርያ ክትባት በወሰዱ ሰዎች ላይ በትንሽ መጠን ይከሰታል። ነገር ግን በ COVID-19 ክትባታቸው ላይ ወቅታዊ የሆኑ በ COVID-19 የተያዙ ሰዎች ቫይረሱን ወደ ሌሎች ሊያስተላልፉ ይችላሉ።

ለ COVID-19 ተጋልጬ ከነበረ ምን ማድረግ አለብኝ?

ለለይቶ ማቆያ እና ለኳራንታይን መመርያዎች እባክዎ የ COVID-19 ለይቶ ማቆያ እና ኳራንታይን ገጻችንን ይመልከቱ።

በ COVID-19 ዙሪያ ውጥረትን እና ጭንቀትን እንዴት መቆጣጠር እችላለሁ?

ወረርሽኙ በሁለቱም አካላዊ እና አእምሯዊ ጤንነትዎ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል እንረዳለን። ብቻዎትን አይደሉም። በ Washington ውስጥ ያሉ ብዙ ሰዎች ከገንዘብ እና ከሥራ ጭንቀት፣ ከትምህርት ቤት መዘጋት፣ ከማኅበራዊ መገለል፣ ከጤና አጠባበቅ፣ ከሐዘን እና ከኪሳራ፣ ወዘተ ጋር የሚዛመዱ ውጥረቶችን እና ጭንቀቶችን እያጋጠሟቸው ነው። ይህ ወደ ህዝባዊ ተግባራት በመመለስ ሊመጣ የሚችል ተጨማሪ ጭንቀትን ይጨምራል።

ጭንቀትን እና ጭንቀትን ለመቆጣጠር የሚያግዙ ጥቂት ሀብቶች እዚህ አሉ

የክትባት አጋዥዎች እና ተጨማሪ ዶዞች

በ COVID-19 ተጨማሪ ዶዝ እና አጋዥ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

ተጨማሪ ዶዝ (ሶስተኛ ዶዝ በመባል ይታወቃል) የበሽታ መቋቋም ለሌላቸው ሰዎች ነው። አንዳንድ ጊዜ የበሽታ መከላከል አቅም የሌላቸው ሰዎች በመጀመሪያ ሙሉ ክትባት ሲወስዱ በቂ ጥበቃ አይገነቡም። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሌላ የክትባት መጠን መውሰድ ከሽታው የበለጠ መከላከያ ይገነባሉ።

አጋዥ የሚያመለክተው ከክትባት በኋላ በቂ ጥበቃ ለገነባ ሰው የሚሰጠው የክትባት መጠን ነው። ነገር ግን ያ ጥበቃ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይቀንሳል (ይህም የበሽታ መከላከያ መቀነስ ይባላል)። በየ 10 ዓመቱ ለቴታነስ አጋዥ የሚሰጥበት ምክንያት ይህ ነው፤ ምክንያቱም ከልጅነትዎ የቲታነስ ክትባት ተከታታይ ጥበቃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠፋ ይሄዳል።

በሽታ የመከላከል ችግር ላለባቸዉ ሰዎች እባክዎ የ Centers for Disease Control & Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል) መመርያዎችን ይመልከቱ ወይም የ DOH ን ድህረ ገፅ ይጎብኙ።

ተጨማሪ የ COVID-19 ክትባት መጠን መውሰድ ያለበት ማነው?

በሽታ የመከላከል ችግር ላለባቸዉ ሰዎች እባክዎ የ Centers for Disease Control & Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል) መመርያዎችን ይመልከቱ ወይም የ DOH ን ድህረ ገፅ ይጎብኙ።

የማጠናከሪያ መጠኖች ለምን ያስፈልጋሉ?

የማጠናከሪያ መጠኖች ለከባድ የ COVID-19 ህመም ከፍተኛ ተጋላጭነት ላላቸው ሰዎች ከከባድ በሽታ መጠበቅ እንዲቀጥል ይረዳሉ።

ከዚህ ቀደም ማጠናከሪያ ዶዞች ለከባድ COVID-19 ህመም ከፍተኛ ተጋላጭነት ላላቸው ሰዎች ብቻ ይመከር ነበር፣ ነገር ግን ምክሩ ከ COVID-19 በሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ ለማድረግ እንዲረዳ እድሜያቸው 6 ወር እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎችን ለማካተት ተስፋፍቷል።

ይህ በተለይ አስፈላጊ የሆነው በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ይበልጥ ተላላፊ የሆኑ የ COVID-19 ተለዋጭ ዝርያዎች እና ጉዳዮች እየጨመሩ በመምጣታቸው ነው።

በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ፈቃድ ያገኙ እና የጸደቁ የ COVID-19 ክትባቶች በከባድ ህመም የመያዝ፣ ሆስፒታል የመግባት እና በ COVID-19 የመሞት፣ እንዲሁም በተለዋጭ ዝርያዎች የመያዝ ስጋትን መቀነስ ላይ አሁንም በጣም ውጤታማ ናቸው። አሁንም፣ በዚህ ጊዜ ያሉት ክትባቶች ከጊዜ በኋላ የመከላከል መቀነስ ጋር ሊዛመዱ ይችላሉ። ማጠናከሪያ መጠኖች ከ COVID-19 በክትባት የሚገኝ መከላከልን የሚጨምሩ ሲሆን በሽታ የመከላከል አቅም እንዲቆይ ይረዳሉ።

ተጨማሪ ማጣቀሻ እና መረጃዎች

ለተወሰኑ ቡድኖች የ COVID-19 መርጃዎች

ልጆች እና ወጣቶች

ጡት ሚያጠቡ ወይም እርጉዝ ግለሰቦች

ስደተኛ እና ስደተኞች

የቤት ለቤት እንክብካቤ

የክትባት እኩልነት እና ተሳትፎ ገጽ ላይ ተጨማሪ የህብረተሰብ ልዩ ሀብቶችን እዚህ ማግኘት ይችላሉ (እንግሊዝኛ ብቻ)

ጥያቄዬ አልተመለሰም። የበለጠ ማወቅ የምችለው እንዴት ነው?

አጠቃላይ ጥያቄዎች ወደ covid.vaccine@doh.wa.gov ሊላኩ ይችላሉ።