COVID-19

Vaccine Locator Button - Amharic

 

 

የ COVID-19 መረጃ የስልክ መሥመር

ስለ COVID-19 ጥያቄዎች ካሉዎት፣ ወደ 1-800-525-0127 ይደውሉ እና 7 ይጫኑ።  መልስ ሲሰጥዎት፣ የትርጉም አገልግሎት እንዲያገኙ የቋንቋዎን ስም ይናገሩ። የስልክ መስመሩ ሰኞ ከ 6 a.m. እስከ 10 p.m.፣ እና ከማክሰኞ እስከ እሁድ (እና የሚከበሩ በዓላት) ደግሞ ከ 6 a.m. እስከ 6 p.m ይገኛል።

ከቤት መውጣት አልቻሉም እና የ COVID-19 ክትባት ይፈልጋሉ?

ለመመዝገብ ሶስት መንገዶች አሉ። "(በእንግሊዘኛ) ወይም ወደ COVID-19 የእርዳታ መስመር 1-800-525-0127 ይደውሉና 7 ን ይጫኑ።"

የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ክትባት

ስለ COVID-19 ክትባቶች ወቅታዊ እና ዝርዝር መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ ይህን ድረ ገጽ በቋንቋዎ ይጎብኙ፦ የ COVID-19 ክትባት መረጃ

የ COVID-19 የህመም ምልክቶች፣ ምልክቶች እና መከላከያዎች

የ COVID-19 ዋና ምልከቶች የሚከተሉት ናቸው፦

 • ትኩሳት ወይም ብርድ ብርድ ማለት፣ ሳል፣ የትንፋሽ ማጠር ወይም የመተንፈስ ችግር፣ ድካም፣ የጡንቻ ወይም የሰውነት ህመም፣ ራስ ምታት፣ አዲስ የሆነ የጣዕም ማጣት ወይም የሽታ ማጣት፣ የጉሮሮ መቁሰል፣ የአፍንጫ መጨናነቅ ወይም የአፍንጫ ፍሳሽ፣ ማቅለሽለሽ ወይም ማስታወክ፣ እና ተቅማጥ።
 • የሚከተሉትን የ COVID-19 ድንገተኛ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ካዩ ወደ 911 ይደውሉ፦
  • የመተንፈስ ችግር
  • ቋሚ የደረት ህመም ወይም ግፊት
  • በድንገት መደናገር
  • መልስ መስጠት አለመቻል
  • የከንፈር ወይም የፊት ገጽታ ሐምራዊ መሆን
 • ስጋት ውስጥ ያሉ ቡድኖች እነማን ናቸው?

እራሴን እና ቤተሰቤን እንዴት መጠበቅ እችላለሁ?

 • ይከተቡ፣ ብቁ ሲሆኑ ደግሞ ማጠንከሪያውን ይውሰዱ።
 • ካመምዎት በቤት ይቆዩ።
 • ማስክ ይጠቀሙ፣ ሕዝብ ወደ ተሰበሰበባቸው ቦታዎች ሲሄዱ ከሌሎች ስድስት ጫማ (ሁለት ሜትር) ይራቁ።
 • ሕዝብ የተሰበሰበባቸውን እና በቂ አየር የሌለባቸውን ቦታዎች ያስወግዱ።
 • በተደጋጋሚ እጆን ይታጠቡ ወይም የእጅ ማጽጃ ፈሳሽን ይጠቀሙ።
 • ሳልዎን እና ማስነጠስዎን በክርኖ ወይም በሶፍት ወረቀት ይሸፍኑ።
 • ፊትዎን፣ አፍዎን፣ አፍንጫዎን ወይም አይንዎን አይንኩ።
 • የቤትዎን ገጽታዎች ያጽዱ።
 • የ COVID-19 ምልክቶች ካሉዎት፣ ከጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ጋር ይነጋገሩ። አቅራቢ ከሌለዎት፣ በአቅራቢያዎ ከሚገኝ አስቸኳይ የእንክብካቤ ማዕከል ወይም የማኅበረሰብ የጤና ማዕከል ጋር ይማከሩ። ኢንሹራንስ ከሌልዎት፣ የአካባቢ ጤና መምሪያዎን ያነጋግሩ።​​​​​
የ COVID-19 ምርመራ

የ COVID-19 ምርመራን በተመለከተ ወቅታዊ እና ዝርዝር መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ ይህን ድረ ገጽ በቋንቋዎ ይጎብኙ፦ የ COVID-19 ምርመራ መረጃ

ኳራንቲን እና ራስን ማግለል

የእነዚህን ስሞች ትርጉም፣ እና ለምን ያህል ጊዜ ራስን ማግለል ወይም ኳራንቲን ማድረግ እንደሚያስፈልግ በይበልጥ ለማወቅ፣ ራስን የማግለል እና ኳራንቲን የማድረግ ማስያ ድረ ገጽን ይጎብኙ።‘’

የማስኮች አጠቃቀም

ማስኮች አንድ COVID-19 ያለበት ሰው ሲናገር፣ ሲያስል፣ ወይም ሲያስነጥስ በአየር ላይ የሚበትናቸውን በዓይን የማይታዩ የቫይረሱን ስርጭቶች ወደ ሰውነት እንዳይገቡ ይቀንሳሉ። በ COVID-19 ተይዞ ነገር ግን ቀላል ወይም ምንም ምልክቶች ላይኖሩ ይችላሉ። ማስክ መጠቀም በ COVID-19 ተይዞ ሳያውቁ ለሌላ ሰው ከማስተላለፍ ይጠብቃል። ለእርስዎ ቀላል ኢንፌክሽን የሆነው ለሌላው ገዳይ ሊሆን ይችላል።

ከታች ስለ ማስክ አጠቃቀም ጠቃሚ ምክሮች ናቸው፦

 • ማስኮች አፍዎንና አፍንጫዎን መሸፈን እና የፊትዎ ጎንና ጎን ላይ በደንብ ግጥም ማለት አለባቸው።
 • ማስክዎን ያድርጉና የጆሮ ገመዱን በመያዝ ያውልቁት፣ እና የማስኩን የፊተኛ ክፍል ወይም ፊትዎን አይንኩ።
 • የሕክምና ማስኮችን ከተጠቀሙባቸው በኃላ ያስወግዷቸው ወይም በየዕለቱ የፊት መሸፈኛዎችን ይጠቡ፣ እንዲሁም እጅዎን ዘወትር ይታጠቡ።
 • ከሁለት ዓመት የሆኑ ልጆች በጭራሽ ማስክ ማድረግ የለባቸውም፣ እንዲሁም ከ 2 እስከ 4 ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆች ማስክ ሲያደርጉ በአዋቂ ተቆጣጣሪነት ስር መሆን አለባቸው።
 • የማስክ ህጎች አንዳንድ የጤና ችግር ላለባቸው ሰዎች አስተያየት ያደርጋሉ። ካሳሰብዎት፣ ለእርስዎ ምርጥ የሆነውን ለማወቅ ከሐኪምዎ ጋር ይማከሩ።
መደብሮችን እና ሕዝባዊ ቦታዎችን ይበልጥ ደህንነት ተጠብቆ መጎብኘት

ለእርስዎ እና ለሌሎች ጤና መጠበቅ ከቤት ከመውጣትዎ በፊት፣ በቤት እያሉ፣ እና ከወጡ ማድረግ የሚችሏቸው የተለያዩ ነገሮች አሉ።

ከመውጣትዎ በፊት፦

 • ከተቻለ፣ ካመምዎት ወደ መደብር ወይም ወደ ሌላ የሕዝብ ቦታ አይሂዱ። የሚያስፈልጉዎትን ነገሮች እንዲያመጡልዎት የቤተሰብ ዓባል ወይም ወዳጅዎን ይጠይቁ።
 • ግሮሰሪዎችን፣ መድኃኒቶችን፣ እና ሌሎች ነገሮችን ኦንላይን አዝዘው ቤትዎ እንዲመጣልዎት ለማድረግ ያስቡ።
 • ልዩ መርሀ ግብሮች መኖራቸውን ያጣሩ። መደብሮች ዕድሜያቸው ከ 65 በላይ ለሆኑ ሰዎች እና አንዳንድ የጤና ችግሮች ላሉባቸው ሰዎች ልዩ የመገበያያ ሰዓታት ሊኖራቸው ይችላል። ከተቻለ፣ ወደ መደብሮች በማይጨናነቅበት ሰዓታት ላይ ለመሄድ ያስቡ።
 • ከቤትዎ ከመውጣትዎ በፊት እጅዎትን ይታጠቡ።

ከቤትዎ ሲወጡ፦

 • አፍንጫና አፍዎትን የሚሸፍን ማስክ ያድርጉ።
 • የመክፈያ ሰልፍ ላይ እንኳን ቢሆንም፣ በእርስዎ እና በሌሎች መካከል የስድስት ጫማ (ሁለት ሜትር) ርቀት ይጠብቁ።
 • ሳልዎን እና ማስነጠስዎን ይሸፍኑ።
 • ፊትዎን አይንኩ።
 • እየተገበያዩ ከሆነ፣ የጋሪውን እጀታ ወይም የመገበያያ ቅርጫቱን ለማጽዳት የእጅ ማጽጃ ፈሳሽ ወይም አንቲሴፕቲክ መጥረጊያ ይጠቀሙ።
 • ቤት ሲደርሱ፦ማስክ አድርገው ከነበረ፣ ማጠብዎን እና አስተማማኝ ቦታ ማስቀመጥዎን፣ ወይም ተጠቅሞ የሚጣል ማስክ ከሆነ ማስወገድዎን እርግጠኛ ይሁኑ።
 • እጆችዎን ይታጠቡ።
 • የምግብ ደህንነት ልምዶችን ይተግብሩ። የሚበሉ ነገሮች ላይ ጸረ ለካፊ አይርጩ። እንደ ሁልጊዜው ፍራፍሬዎች እና አትክልቶችን ይጠቡ።
 • COVID-19 የግሮሰሪ ግብይት ጠቃሚ ምክሮች።
የከባድ ሕመም ስጋት ያለባቸው ሰዎች

የጨመረ የከባድ ሕመም ስጋት ያለባቸው ሰዎች እነዚህን ተጨማሪ ጥንቃቄዎች መውሰድ ይችላሉ፦

 • ምክር ሲያስፈልጎት የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያነጋግሩ። አንዳንድ ክሊኒኮች ግንኙነት ለማድረግ "የታካሚ ፖርታሎች" ይጠቀማሉ፣ እና ብዙዎቹ ጥሪዎችን የሚቀበሉ እና ምክር የሚሰጡ ሰራተኞች አሏቸው። ነገር ግን፣ በጣም ስራ ሊበዛባቸው እንደሚችል ልብ ይበሉ።
 • በአብዛኛው የሚያስፈልጉዎትን መድኃኒቶች ዝርዝር ያውጡና ተጨማሪ በሐኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶችን ሊሰጡዎት ይችሉ እንደሆነ የመድኃኒት መደብሮን ወይም የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያነጋግሩ። የሚወስዷቸውን ሌሎች መድኃኒቶች ወይም አጋዥ ኪኒኖች መዝግበው ይያዙና እንደ ታዘዘው ወቅታዊ ሁኔታዎን ይቆጣጠሩ።
 • ከሁሉም የሚመከሩ ክትባቶች ጋር ራስዎን ያዘምኑ። የ COVID-19 ክትባት መውሰድዎን እና ብቁ ሲሆኑ ደግሞ ማጠንከሪያውን መውሰድዎን እርግጠኛ ይሁኑ። አቅራቢያዎ ክትባት አቅራቢ ለማግኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ
 • ራስዎን ማግለል ወይም ኳራንቲን ማድረግ ያስፈልግት እንደሆነ በቂ ምግብ እና ግላዊ ንጽሕና መጠበቂያ ምርቶች እንዳሎት እርግጠኛ ይሁኑ።
 • ሊረዳዎት የሚችል አንድ ሰው ያስቡና ደህና መሆንዎን ለማረጋገጥ ስልክ እንዲደውልሎት ይጠይቁ። ይህ ሰው ጥሩ ባይሰማው ሊጎበኞት እንደማይችል ማወቁን ያረጋግጡ።
 • ጤናዎን ይቆጣጠሩ እንዲሁም ካስፈለገ የሕክምና ክትትል ይጠይቁ።
እርግዝና፣ ልጆች እና COVID-19

አሁን ላይ ነፍሰ ጡር ከሆኑ ማወቅ ያለብዎት ነገር

 • ነፍሰ ጡር ካልሆኑ ሴቶች ጋር ሲተያይ ነፍሰ ጡር ሴቶች ወይም በቅርብ ነፍሰ ጡር የነበሩ ሴቶች ለ COVID-19 ከባድ ሕመም የጨመረ ስጋት ላይ ናቸው።
 • በእርግዝና ወቅት COVID-19 ይዟቸው የነበሩ ሴቶች እንዲሁ ያለ ጊዜው ለሚወለድ ጽንስ (ጽንሱን ከ 37 ሳምንታት በፊት መውለድ) እና የጽንስ መሞት፣ እንዲሁም ለሌሎች የእርግዝና ውስብስብ ችግሮች የጨመረ ስጋት ላይ ናቸው።
 • ነፍሰ ጡር ሴቶች ወይም በቅርብ ጊዜ ነፍሰ ጡር የነበሩ ሴቶች እና ከእነርሱ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ሰዎች COVID-19 እንዳይዛቸው የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ አለባቸው፦
  • መከተብ እና ማጠናከሪያ መውሰድ።
  • ማስክ ማድረግ።
  • ከሌሎች በ 6 ጫማ መራቅ፣ እና ሕዝብ የተሰበሰበባቸውን እና በቂ አየር የሌለባቸውን ቦታዎች ማስወገድ።
  • ለሌሎች ላለማሰራጨት ምርመራ ማድረግ።
  • እንጅዎን ዘወትር ይታጠቡ፣ ሳልዎን እና ማስነጠስዎን በክርኖ ወይም በሶፍት ወረቀት ይሸፍኑ።
  • ዘወትር ቤትዎን ያጽዱና ከጀርም ነጻ ያድርጉ።
  • ጤናዎን ዘወትር ይቆጣጠሩ።
  • ስለ እርግዝናዎ ማናቸውም አሳሳቢ ነገሮች ካጋጠሙዎት፣ ከታመሙ፣ ወይም COVID-19 ይዞኛል ብለው ካሰቡ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ጋር ወዲያው ይደውሉ።

እርግዝና እና የ COVID-19 ክትባት

 • ነፍሰ ጡር ለሆኑ፣ ጡት ለሚያጠቡ፣ ነፍሰ ጡር ለመሆን እየሞከሩ ላሉ፣ ወይም ወደፊት ነፍሰ ጡር ሊሆኑ ለሚችሉ ሴቶች የ COVID-19 ክትባት ይመከራል።
 • በእርግዝና ወቅት የ COVID-19 ክትባት ደህንነት እና ውጤታማነት ማስረጃ እየጨመረ ነው። መረጃው እንደሚጠቁመው የ COVID-19 ክትባት የመውሰድ ጥቅም በእርግዝና ወቅት ማንኛውንም የሚታወቅ ወይም ሊከሰት የሚችል የክትባት ስጋት ይበልጣል።
 • ነፍሰ ጡር ሴቶች ብቁ ሲሆኑ የ COVID-19 ክትባት ማጠናከሪያ መውሰድ አለባቸው።
 • ነፍሰ ጡር የሆኑ ሴቶች እና ልጆቻቸው ላይ ጭምር የ COVID-19 ክትባቶች የ COVID-19 ኢንፌክሽን አያስከትሉም።
 • በአሁኑ ጊዜ የ COVID-19 ክትባቶችን ጨምሮ ማናቸውም ክትባቶች በሴቶችም ሆነ በወንዶች ላይ የመራባት ችግር እንደሚያስከትሉ የሚያሳይ ምንም ማስረጃ የለም።
 • ነፍሰ ጡር ኖት እና ስለ COVID-19 ተጨማሪ ጥያቄዎች አለዎት? የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ወይም በስልክ ወይም በቻት ጥያቄዎችን ለመመለስ ዝግጁ የሆኑ ባለሙያዎች ያሉትን MotherToBaby ያነጋግሩ። ነጻ ምስጢሩ የተጠበቀው አገልግሎት ከሰኞ እስከ ዐርብ፣ ከ 8 a.m. እስከ 5 p.m. ይገኛል። MotherToBaby (እናት ለልጇ) በመጎብኘት በቀጥታ ቻት ያድርጉ ወይም ኢሜይል ይላኩ፣ ወይም ወደ 1-866-626-6847 (እንግሊዘኛ እና ስፓኒሽ ብቻ) ይደውሉ።

COVID-19 ካለብዎት አዲስ ለተወለዱ ልጆች እንክብካቤ ማድረግ

 • ነፍሰ ጡር እያሉ COVID-19 ይዟቸው የነበሩ ሴቶች የወለዷቸው ልጆች አብዛኞቹ COVID-19 የለባቸውም።
 • አብዛኞቹ COVID-19 የተገኘባቸው አዲስ የተወለዱ ልጆች ቀላል ወይም ምንም ምልክቶች ያልነበረባቸው ሲሆን አገግመዋል። አንዳንድ አዲስ የተወለዱ ልጆች ከባድ የ COVID-19 ህመም እንዳጎለበቱ ዘገባዎች ያሳያሉ።
 • በ COVID-19 ራስውን አግልለው ከሆነ እና አዲስ የተወለደ ልጅ ካለዎት፣ ራስን የማግለል ጊዜዎ እስኪያበቃ ድረስ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ይውሰዱ፦
  • ከቤትዎ ውጪ ካሉ ሰዎች ራስዎን ለመለየት በቤት ይቆዩ።
  • ካልተያዙ ሌሎች የቤተሰብዎ ዓባላት ራስዎን ያግልሉ (ይራቁ) እና በጋራ ቦታዎች ላይ ማስክ ያድርጉ።
  • ሙሉ ለሙሉ የተከተበ እና ለከባድ ሕመም ከፍተኛ ስጋት ላይ ያልሆነ ጤናማ እንክብካቤ ሰጪ አዲስ ለተወለደው ልጅዎ እንክብካቤ እንዲሰጥ ያድርጉ። ከተቻለ፣ ሌላ እንክብካቤ ሰጪ ልጁን እንዲመግብ ጡትዎን ይለቡ። ፎርሙላ የሚመግቡ ከሆነ፣ ጤናማው እንክብካቤ ሰጪ እንዲያዘጋጀው ያድርጉ።
  • ራስን የማግለል ጊዜዎ ከማብቃቱ በፊት አዲስ ለተወለደው ልጅዎ እንክብካቤ ማድረግ ካለብዎት፣ ልጁን ሲመግቡ እና ሲይዙ ማስክ ማድረግን ጨምሮ የሚከተሉትን የሚመከሩ ጥንቃቄዎች ይከተሉ።
  • አዲስ የተወለደው ልጅ የ COVID-19 ምልክቶች ያሉበት እንደሆነ ይከታተሉ።
  • እርግዝና፣ ውልደት እና COVID-19 እንዳለበት ለተጠረጠረ ወይም ለተረጋገጠ ልጅ እንክብካቤ ማድረግ
 • ወቅታዊ ማስረጃ እንደሚጠቁመው የጡት ወተት ቫይረሱን ለልጆች አያስተላልፍም። የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የ COVID-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች ተከላካይ ፀረ እንግዳ አካላትን በጡት ወተት በኩል ወደ ሰውነታቸው ያስተላልፋሉ። COVID-19 ካለብዎት እና ጡት ለማጥባት ከመረጡ፦
  • ጡት ከማጥባትዎ በፊት እጆችዎን ይታጠቡ
  • ጡት ሲያጠቡ እና ከልጅዎ 6 ጫማ ርቀት ላይ በሚሆኑበት ጊዜ በሙሉ ማስክ ያድርጉ።

የወላጅ ድጋፍ የእርዳታ መስመር ለሁሉም ነፍሰ ጡር ሴቶች እና አዲስ ወላጆች፣ ወይም ድጋፍ እና ስለ የአዕምሮ ጤና መረጃ ለሚያስፈልጋቸው ወዳጆቻቸው ክፍት ነው። ወደ 1-888-404-7763 ይደውሉ፣ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከ 9 a.m.- 4:30 p.m. (እንግሊዘኛ እና ስፓኒሽ ብቻ)። የእርዳታ መስመራችን ሰራተኞች የተዋቀሩት ከማኅበራዊ ሰራተኛ፣ ፈቃድ ያለው ቴራፒስት ወይም ከውልደት በኋላ የሚመጣ ድብርት/ጭንቀት ተሞክሮ ባላቸው ወላጆች ነው። ከስራ ሰዓታት በኋላ የሚመጡ ጥሪዎች በተቻለ ፍጥነት ይመለሳሉ። ይደውሉልን፣ አጭር የጽሑፍ መልዕክት ይላኩልን ወይም warmline@perinatalsupport.org ላይ ኢሜይል ያድርጉልን።

ራስዎንና ቤተሰብዎን መንከባከብ።

Washington Listens (ዋሺንግተን ታዳምጣለች)፦ በ COVID-19 ምክንያት ስለ ሚከሰት ጭንቀት ማውራት ካስፈለጎት፣ ወደ Washington Listens በ 1-833-681-0211 ይደውሉ። ሁሌም ቢሆን ከሰኞ እስከ ዐርብ ከ 9:00 a.m. እስከ 9:00 p.m. እና ቅዳሜና እሁድ ከ 9:00 a.m. እስከ 6:00 p.m. TTY ሊያናግሮት የሚችል ሰው ያለ ሲሆን የቋንቋ ተደራሽነት አገልግሎቶች ይኖራሉ። እንዲሁም ስለ አዕምሯዊ እና ስሜታዊ ደህንነት ተጨማሪ የመረጃ ምንጮች እዚህ (በእንግሊዘኛ) ያገኛሉ።

 • ስለ ወቅታዊ የወረርሺኝ ሁኔታ እና ተጨማሪ ጥቆማዎች ከታማኝ ሚዲያ፣ ሕዝባዊ እና አካባቢያዊ የጤና ኤጀንሲዎች፣ እና የሕዝብ የጤና ድረ ገጾች ማዘመኛዎች በሚገኝ መረጃ ራስዎን ያዘምኑ።
 • እንደ የስልክ ቁጥሮች፣ ድረ ገጾች እና ማኅበራዊ ሚዲያ መለያዎች ያሉ ማኅበራዊ የመረጃ ምንጮች ዝርዝር ያውጡ። ት/ቤቶችን፣ ሐኪሞችን፣ የሕዝብ ጤና ድርጅቶችን፣ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን፣ የአዕምሮ ጤና እና አደጋ የእርዳታ መስመሮች የማኅበረሰብ ማዕከላትን መጨመር ይችላሉ።
 • ከቤተሰብ ዓባላት እና ከወዳጆች ጋር በስልክ ወይም በኦንላይን አገልግሎቶች ግንኙነዎን ይቀጥሉ።
 • መሰረታዊ የጤና መገልገያዎች ቅርብዎ ይሁኑ (ለምሳሌ ሳሙና፣ አልኮል ያለው የእጅ ማጽጃ ፈሳሽ፣ ሶፍት፣ ሙቀት መለኪያ፣ ትኩሳት ማቅለያ መድኃኒቶች፣ እና በቤት COVID-19 መመርመሪያ መሳሪያዎች)።
 • እርስዎ እና የቤተሰብ ዓባላትዎ ዘወትር የሚወስዷቸው መድኃኒቶች አቅርቦት እንዲኖር ይሞክሩ።

ለወጣት የቤተሰብ ዓባላትዎ ድጋፍ

 • በስልክ፣ በጽሑፍ፣ በኢሜይል፣ ወይም በማህበራዊ ሚድያ በማዋራት የጓደኞቻቸውን እና የቤተሰብ ድጋፍ እና ቀጣይ ግንኙነት ይፈልጉ።
 • ዜናው ካስጨነቃቸው፣ እረፍት መውሰድ አይርሱ። ከኢንተርኔት ወይም ከሌሎች የመረጃ ምንጮች የሚያገኙትን መረጃ ለማጥራት ከልጆችዎ ጋር ያውሩ።
 • ልጆች ጥያቄዎች እንዲጠይቁ በማበረታታት እና ወቅታዊውን ሁኔታ እንዲያውቁ በመርዳት ድጋፍ ማድረጉ ላይ ያተኩሩ።
 • ስለሚሰሟቸው ስሜቶች ያውሩ፣ ያክብሯቸው።
 • ሥዕል በመሳል ወይም በሌሎች እንቅስቃሴዎች ስሜቶቻቸውን እንዲገልጹ እርዷቸው።
 • ምቾት ይስጧቸው፣ እንዲሁም ከሌላው ጊዜ ትንሽ የጨመረ ትዕግስት ያሳዩዋቸው።

የቤተሰብ እንቅስቃሴዎች

ቤተሰብዎ ራስን ማግለል ወይም ኳራንቲን ውስጥ ቢሆንም እንኳን፣ ጊዜያዊ እንደሆነ ልብ ይበሉ።

የመተኛ ሰዓት፣ ምግብ፣ እና እንቅስቃሴ በተመለከተ የቤተሰቡን መርኃ ግብር ቋሚ ያድርጉ።

ልጆችዎ በት/ቤታቸው ወይም በሌሎች ድርጅቶች በሚሰጡ የርቀት ትምህርት ዕድሎች ላይ የሚሳተፉ ከሆነ፣ ልጆችዎ ደህንነታችው ተጠብቆ ከእኩዮቻቸው ጋር ማኅበራዊ ግንኙነት እንዲያደርጉዕድሎችን ይፈልጉ።

እንደ ብቸኝነት፣ ድብርት፣ በበሽታው የመያዝ ፍራቻ፣ ጭንቀት፣ መጨናነቅ፣ እና ፍራቻ ያሉ ስሜቶች እንደ ወረርሺኝ ላለ አስጨናቂ ሁኔታ ዓይነተኛ ምላሾች ናቸው።

ቤተሰብዎን እና ባሕላዊ እሴቶችን ያማከለ አስደሳች እና ትርጉም ያላቸውን እቅስቃሴዎች እንዲያደርግ ቤተሰብዎን ይርዱ።

ተጨማሪ የመረጃ ምንጮች