Care Connect Washington

ለ COVID-19 ምርመራ አዎንታዊ ውጤት ካገኙ እና ምግብ ከፈለጉ ወይም ሌላ እርዳታ ካስፈለግዎት ራስዎን በሚያገሉበት ጊዜ፣ የግዛቱን COVID-19 የመረጃ መስመር በ 1-800-525-0127 ላይ ይደውሉ፣ ከዚያ #ን ይጫኑ። የቋንቋ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

Care Connect Washington በ COVID-19 አወንታዊ ምርመራ ላደረጉ ወይም ለተጋለጡ እና ለማግለል ወይም በቤት ውስጥ ለይቶ ለማቆየት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች የሚሰጥ መርሃ-ግብር ነው። የግዛቱ የጤና መምሪያ፣ ከአካባቢው የጤና ስልጣኖች እና ከአጋሮቻቸው ጋር በመተባበር Care Connect Washington በክልል በክልሎች እየሰራ ነው። እያንዳንዱ ክልል እንደ የመድኃኒት አቅርቦት፣ የጤና እንክብካቤ፣ ለስራ አጥነት ማመልከት መርዳት፣ ሎካል የቤት ኤጀንሲዎች፣ የምግብ ባንኮች፣ የልጅ እንክብካቤ አቅራቢዎች እና ሌሎችም ያሉ ሰዎችን ብቁ ከሆኑባቸው አገልግሎቶች ጋር የሚያገናኙ ማኅበረሰብ ላይ መሰረት ያደረጉ አጋሮች ጋር ይሰራል። እርዳታ የሚደረገው በፍላጎት መሰረት ነው።

ራሳቸውን አግልለው ወይም ኳራንቲን ላይ ያሉ ሰዎች ቤት እንዲቆዩ ለማድረግ፣ Care Connect Washington እንደ ግላዊ የእንክብካቤ ኪቶች፣ የማይበላሹ የምግብ ኪቶች፣ እና በቤታቸው ትኩስ/ፍሬሽ የምግብ ትዕዛዞችን ማድረስ ያሉ ነገሮችን ያቀርባል። እንደ ሂሳቦች ለመክፈክ የገንዘብ እርዳታ ያሉ ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶች ከተለዩ፣ ሎካል የእንክብካቤ አስተባባሪ ሰዎች ብቁ ለሆኑባቸው ሎካል መርጃዎች ወይም አገልግሎቶች እንዲያመለክቱ ይረዳቸዋል፣ ወይም እንደ ኪራይ፣ ሞርጌጅ፣ እና መገልገያዎች ያሉ ቀጥተኛ ሂሳቦችን ለመክፈል ቀጥተኛ እርዳታ ያቀርብላቸዋል። ራስን ማግለል ወይም ኳራንቲን ሲያበቃ፣ የእንክብካቤ አስተባባሪው ሰዎችን ከረጅም ጊዜ ሎካል አገልግሎቶች ጋር በማገናኘት ቀጣይ የጤና እና የማኅበራዊ ፍላጎቶችን ይደግፋል። Care Connect Washington ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን መረጃ በሚመርጡት ቋንቋ ያቀርባል።

ለ COVID-19 ምርመራ አዎንታዊ ውጤት ካገኙ እና ምግብ ከፈለጉ ወይም ሌላ እድዳታ ራስዎን ለማግለል ካስፈለግዎት፣ የግዛቱን COVID-19 የመረጃ መስመር በ 1-800-525-0127 ላይ ይደውሉ፣ ከዚያ #ን ይጫኑ። የቋንቋ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ። የሚከተሉት የነጻ ስልክ ሰዓታት ናቸው፦

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

Care Connect regions map with services in these counties: Grays Harbor, Mason, Thurston, Pacific, Wahkiakum, Lewis, Cowlitz, Clark, Skamania, Clickitat, Yakima, Benton, Franklin, Adams, Lincoln, Ferry, Stevens, Pend Oreille, Spokane, King, Pierce, Snohomish, Skagit, Whatcom

ክልላዊ አቀራረብ ለ COVID-19 እርዳታ

የግዛቱ የጤና መምሪያ፣ ከአካባቢው የጤና ስልጣኖች እና ከአጋሮቻቸው ጋር በመተባበር Care Connect Washington በክልል በክልሎች እየሰራ ነው። እያንዳንዱ ክልል እንደ የመድኃኒት አቅርቦት፣ የጤና እንክብካቤ፣ ለስራ አጥነት ማመልከት መርዳት፣ ሎካል የቤት ኤጀንሲዎች፣ የምግብ ባንኮች፣ የልጅ እንክብካቤ አቅራቢዎች እና ሌሎችም ያሉ ሰዎችን ብቁ ከሆኑባቸው አገልግሎቶች ጋር የሚያገናኙ ማኅበረሰብ ላይ መሰረት ያደረጉ አጋሮች ጋር ይሰራል።

አገልግሎቶች የሚገኙት የት ነው?

ራሳቸውን ለማግለል ወይም በቤት ኳራንቲን ለማድረግ የተስማሙ ነገር ግን ይህን ለማደርግ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በአብዛኞቹ የግዛቱ ክፍሎች አገልግሎቶች ይገኛሉ።

ምስራቅ ክልል

Better Health Together (በእንግሊዝኛ ብቻ) ለ Adams፣ Ferry፣ Lincoln፣ Pend Oreille፣ Spokane፣ እና Stevens ካውንቲዎች እንደ Care Connect Washington Hub ያገለግላል።

ኪንግ ካውንቲ

DOH በአሁኑ ጊዜ ለዚህ ክልል አገልግሎቶችን በማስተባበር ላይ ነው። ተግባራዊ የሚሆነው ኤፕሪል 1፣ 2022፣ Action Health Partners (በእንግሊዝኛ ብቻ)ለ Chelan፣ Douglas፣ Grant እና Okanogan ካውንቲዎች እንደ Care Connect Washington Hub ያገለግላል።

ሰሜን ክልል

North Sound Accountable Community of Health (በእንግሊዝኛ ብቻ) ለ Island፣ San Juan፣ Skagit፣ Snohomish፣ እና Whatcom ካውንቲዎች እንደ Care Connect Washington Hub ያገለግላል።

ሰሜን ምዕራብ ክልል

DOH በአሁኑ ጊዜ በ Clallam County ከሚገኙ አገልግሎቶች ጋር የዚህ ክልል አገልግሎቶችን በማስተባበር ላይ ነው።

ፒየርሲ ካውንቲ

Elevate Health (በእንግሊዝኛ ብቻ) ለ Pierce County እንደ Care Connect Washington Hub ያገለግላል።

ደቡብ ማዕከላዊ ክልል

Providence St. Mary (በእንግሊዝኛ ብቻ) ለ Kittitas፣ Walla Walla፣ Whitman፣ Columbia፣ Garfield፣ Asotin፣ Yakima፣ Benton እና Franklin እንደ Care Connect Washington Hub ያገለግላል።

ደቡብ ምስራቅ ክልል

Southwest Washington Accountable Community of Health (SWACH) (በእንግሊዝኛ ብቻ)ለ Clark፣ Klickitat፣ እና Skamania ካውንቲዎች እንደ Care Connect Washington Hub ያገለግላል።

ምዕራብ ክልል

Cascade Pacific Action Alliance’s Community CarePort (በእንግሊዝኛ ብቻ) ለ Cowlitz፣ Wahkiakum፣ Pacific፣ Grays Harbor፣ Mason፣ Thurston፣ and Lewis ካውንቲዎች እንደ Care Connect Washington Hub ያገለግላል።

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

የ Care Connect Washington አገልግሎቶችን እኔ ማግኘት እችላለሁ?

ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ እና በቤት ውስጥ አሁን ራስዎን እያገለሉ ከሆነ ለአገልግሎቶች ብቁ ይሆናሉ። አዎንታዊ ከሆነ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ከነበርዎት እና በቤት ውስጥ ራስዎን በማግለል ላይ ከሆኑ እርስዎም ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

የግዛቱን COVID-19 የመረጃ መስመር በ 1-800-525-0127 ላይ ይደውሉ፣ ከዚያ #ን ይጫኑ። የቋንቋ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

 • ሰኞ ከ 6 a.m. እስከ 10 p.m.
 • ከማክሰኞ እስከ እሁድ ከ 6 a.m. እስከ 6 p.m. እንዲሁም የሚከበሩ የመንግስት በዓላት

የአካባቢ የእንክብካቤ አስተባባሪ የሚያነጋግሮት ሲሆን ራስን በማግለል ወቅት የሚያስፈልጉዎትን ነገሮች ለሟሟላት የእንክብካቤ እቅድ ለማውጣት ያነጋግርዎታል። ራስን የማግለል ጊዜዎ ሲያበቃ፣ አስፈላጊ ከሆነ የእርስዎ የእንክብካቤ አስተባባሪ ከረጅም ጊዜ የእንክብካቤ ትብብር ድጋፍ ጋር ያገናኞታል።

ምን ዓይነት እርዳታ ልጠብቅ?

በቤት ራስዎን አግልለው ወይም ኳራንቲን አድርገው እያለ ድጋፍ እንዲያገኙ የእርስዎ የአካባቢ እንክብካቤ አስተባባሪ ያሉ የአካባቢ መርጃዎችን ይለያል። በቤት ራስዎን አግልለው ወይም ኳራንቲን አድርገው እያለ የአካባቢ መርጃዎች ከሌሉ ምግብ፣ አቅርቦቶች፣ እና ለኪራይ፣ ሞርጌጅ እና የመገልገያ ሂሳቦች የገንዘብ እርዳታ በማቅረብም ይረዳዎታል። የእርስዎ የእንክብካቤ አስተባባሪ እንደ የመድኃኒት አቅርቦት አገልግሎቶች፣ የጤና እንክብካቤ፣ ለስራ አጥነት ማመልከት መርዳት፣ እና ሌሎችን ጨምሮ ከአስፈላጊ አገልግሎቶች ጋር እንዲሁ ያገናኞታል። ሌሎች አገልግሎቶች ከአካባቢ የቤት ኤጀንሲዎች ጋር ማገናኘትን፣ የምግብ ባንኮች፣ የጤና እንክብካቤ ማዕከላት፣ የአረጋውያን እንክብካቤ፣ የባሕሪ ጤና አቅራቢዎች፣ የልጅ እንክብካቤ አቅራቢዎች፣ እና ሌሎች ማኅበረሰብ ላይ ትኩረት ያደረጉ በባህሉ ተገቢ አገልግሎቶችን ያጠቃልላል። አገልግሎቶች እንደ ክልሉ ይለያያሉ። ራስን ማግለል ወይም ኳራንቲን ሲያበቃ፣ የእርስዎ የእንክብካቤ አስተባባሪ ቀጣይ ፍላጎቶችን ለመደገፍ ከረጅም ጊዜ ክልላዊ አገልግሎትች ጋር ያገናኞታል። Care Connect Washington የሚያስፈልጎትን መረጃ በሚመርጡት ቋንቋ ያቀርባል።

ለ Care Connect Washington ብቁ ነኝ?

ብቁ የሚሆኑት፦

 • ለ COVID-19 አዎንታዊ ውጤት ስለነበርዎት ወይም አዎንታዊ ውጤት ከነበረው ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ስለነበርዎት፤ እና
 • በአሁኑ ጊዜ ራስዎን አግልለው ወይም በቤት ኳራንቲን እያደረጉ ከሆነ።

ብቁ ለሆኑ ሰዎች የ Care Connect Washington አገልግሎቶች በነጻ ይሰጣሉ። እርዳታ የሚደረገው በፍላጎት መሰረት ነው።

የ Care Connect Washington አገልግሎቶችን ያሉት የት ነው?

የግዛቱ Department of Health፣ ከአካባቢው የጤና ስልጣኖች እና ከአጋሮቻቸው ጋር በመተባበር Care Connect Washington በክልሎች እየሰራ ነው። አሁን ላይ አገግልግሎቶቹ የት እንደሚገኙ የሚያሳይ ካርታ እነሆ፦

Care Connect regions map with services in these counties: Grays Harbor, Mason, Thurston, Pacific, Wahkiakum, Lewis, Cowlitz, Clark, Skamania, Clickitat, Yakima, Benton, Franklin, Adams, Lincoln, Ferry, Stevens, Pend Oreille, Spokane, King, Pierce, Snohomish, Skagit, Whatcom
ወጪው ስንት ነው?

ለዚህ አገልግሎት ክፍያ አይጠየቁም። Care Connect Washington በዋሺንግተን ግዛት የ COVID-19 ምላሾችን የሚደግፉ የተለያዩ ፈንዶችን አግኝቷል።

እርዳታ ከማግኘቴ በፊት ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

የክልል እንክብካቤ አቅራቢዎ ሪፈራል ባገኙ በአንድ ቀን ውስጥ እርዳታ ለማቅረብ የቻለውን ሁሉ ጥረት ያደርጋል።

እርዳታ ሳገኝ አሁንም ራሴን ማግለል ወይም ኳራንቲን ማድረግ አለብኝ?

አዎ። COVID-19 ን ለጎረቤቶቻችን፣ ለጓደኞቻችን፣ ለቤተሰቦቻችን፣ እና ለስራ ባልደረቦቻችን እንዳናስተላልፍ እና ማኅበረሰቦቻችን ላይ ሰፊ አሉታዊ ተጽዕኖዎቹን ለመቀነስ ራስን ማግለል እና ኳራንቲን ማድረግ ጥቅም ላይ የሚውሉ አስፈላጊ መሳሪያዎች ናቸው። ራስን ከማግለል ወይም ከኳራንቲን ጊዜዎ በኋላ እርዳታ የሚያስፈልጎት ከሆነ፣ የአካባቢ የእንክብካቤ አስተባባሪዎ ከረጅም ጊዜ ሎካል አገልግሎቶች ጋር በማገናኘት ቀጣይ የጤና እና የማኅበራዊ ፍላጎቶችዎን ይደግፋል።

እራስን በማግለል እና በኳራንቲን መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

ራስን ማግለል፦  አዎንታዊ የ COVID-19 ውጤት ወይም ምልክቶች ካለዎት፣ ወይም የምርመራ ውጤት እየጠበቁ ከሆነ፣ ስርጭቱን ለማቆም ራስዎን ማግለል አለብዎት።

ኳራንቲን፦ ለ COVID-19 ተጋልጠው ከነበረ ነገር ግን ምልክቶች ከሌሎት፣ እንደ ክትባት ሁኔታዎ ኳራንቲን ማድረግ ሊአስፈልጎት ይችላል። ይህ እንደታመሙ ሳያውቁ ቫይረሱን እንዳያስተላልፉ ያስችላል።

ኳራንቲን የሚያደርጉበት ጊዜ ምን ያህል መቆየት እንዳለበት ለማወቅ የ CDC፣  (በእንግሊዝኛ ብቻ)እና የ DOH፣  ን (በእንግሊዝኛ ብቻ)  የቅርብ ጊዜ መመሪያ (በእንግሊዝኛ ብቻ) ይከተሉ።

የ COVID-19 ምልክቶቼ እየተባባሱ ከሄዱ ምን ማድረግ አለብኝ?

ምልክቶችዎ እየተባባሱ ከሄዱ በፍጥነት የህክምና እርዳታ ያግኙ። አንድ ሰው የሚከተሉትን ምልክቶች ካሳየ፣ ወዲያውኑ ድንገተኛ የህክምና እርዳታ ያግኙ፦

 • የመተንፈስ ችግር
 • በደረት ውስጥ የማያቋርጥ ህመም ወይም ክብደት
 • አዲስ ግራ መጋባት
 • መንቃት ወይም ነቅቶ መቆየት አለመቻል
 • ከንፈር ወይም ፊት ሰማያዊ መሆን

*ይህ ሙሉ ዝርዝር አይደለም። ከባድ ለሆኑ ወይም አሳሳቢ ለሆኑብዎት ሌሎች ማናቸውም ምልክቶች እባክዎ የሕክምና አቅራቢዎ ጋር ይደውሉ።

የሕክምና ድንገተኛ ሁኔታ ካለብዎ እና ወደ 911 ለመደወል ከፈለጉ ለላኪው COVID-19 እንዳለብዎት ወይም ደግሞ ሊኖርዎት እንደሚችል ይንገሩ። የሚቻል ከሆነ ድንገተኛ የሕክምና አገልግሎት ከመድረሱ በፊት የፊት ሽፋን ያድርጉ።

የ Care Connect Washington አገልግሎቶችን ለምን ያህል ጊዜ ማግኘት እችላለሁ?

የክልልዎ እንክብካቤ አስተባባሪ እስከ 21 ቀናት ድረስ ይረዳዎታል። በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ የእርስዎ የእንክብካቤ አስተባባሪ ቀጣይ የጤና እና ማኅበራዊ ፍላጎቶችን ለመደገፍ ከረጅም ጊዜ አገልግሎትች ጋር ያገናኞታል።

Care Connect Washington የሚሰራው እንዴት ነው?

Care Connect Washington ለተባበረ እንክብካቤ በግዛት የሚደገፍ፣ አካባቢ ላይ ትኩረት የሚያደርግ አቀራረብ ነው።

Washington State Department of Health ክልላዊ የእንክብካቤ ትብብር ምላሽ ያስተዳድራል፣ የስራ ቅጥር እና ስልጠና ይደግፋል፣ ግዛት አቀፍ እና አካባቢያዊ መርጃዎችን ያቀራርባል፣ እንዲሁም እንደ ፈንድ እና ቴክኒካዊ መዋቅር ያሉ የውህደት መርጃዎችን በማስተዳደር ውጤቶችን ያሻሽላል።

እያንዳንዶቹ ክልሎች እርዳታ ለማቅረብ እና ውጤታማ ራስን ማግለል እና ኳራንቲን ለመደገፍ ሰዎችን ከአካባቢያዊ መርጃዎች ጋር ለማገኘት ማኅበረሰብ ላይ መሰረት ያደረገ የስራ ግብር ይለያሉ እንዲሁም ይተገብራሉ። አስፈላጊ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ክልሎች ከአካባቢያዊ አቅራቢዎች ጋር አብረው ይሰራሉ፣ ይህም ለአካባቢያዊ የኢኮኖሚ ማገገም አስተዋጽዖ ያደርጋል።

የእንክብካቤ አስተብባሪዎች የሚመደቡት የእያንዳንዱ ሰው ልዩ የጤና እና ማኅበራዊ ፍላጎቶች ለመገምገም፣ ለመደገፍ፣ እና ለመከታተል፣ እንዲሁም የ COVID የእንክብካቤ ድርጊት እቅድ ለመፍጠር ነው። ፕሮግራሙ በተቻለው ሁሉ ሰዎችን በሚመርጡት ቋንቋ ከመርጃዎች ጋር ያገናኛል እንዲሁም ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ሂደቱ ላይ ይከታተላቸዋል።

መረጃዬን የምትጠብቁት እንዴት ነው?

የእርስዎ የእንክብካቤ አስተባባሪ ከነፃ የ COVID-19 መረጃ መስመር የሚያገኘውን መረጃ አረጋግጦ ስለ ፍላጎቶችዎ ይጠይቃል። ከእንክብካቤ አስተባባሪዎ ጋር የሚያጋሩት መረጃ ምስጢሩ ይጠበቃል። የእንክብካቤ አስተባባሪ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ ሰራተኞች እና Department of Health መረጃውን በመጠቀም የሚያስፈልጉዎትን መሰረታዊ አገልግሎቶች ይለያሉ። የግል ወይም ግላዊ የጤና መረጃን አያጋሩም።

Care Connect Washington የ COVID-19 ስርጭትን የሚከላከለው እንዴት ነው?

መሰረታዊ ማኅበራዊ እና የጤና ፍላጎቶችን ለማሟላት እርዳታ የሚያገኙ ሰዎች በቤት ራስን ማግለል እና ኳራንቲን ማድረግን በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ይበልጥ እድል አላቸው። አዎንታዊ የ COVID-19 ውጤት ያላቸውን ወይም አዎንታዊ ውጤት ላለው ሰው ተጋላጭ የነበሩ ሰዎች ቤት ራሳቸውን እያገለሉ ወይም ኳራንቲን እያደረጉ መሆናቸውን በማረጋገጥ፣ Care Connect Washington የ COVID-19 ስርጭትን መቀነስ እና ኢኮኖሚያ ማገገምን መጨመር ይችላሉ። ስርዓቱ ትኩረት የሚያደርገው ያላቸው የጤና እና ማኅበራዊ ፍላጎቶች ለ COVID-19 ይበልጥ ተጋላጭ የሚያደርጋቸው ሰዎች ላይ ስለሆነ፣ የጤና ችግሮችን ለመድረስ እና በ COVID-19 ይበልጥ የተጎዱ ማኅበረሰቦችን ለመደገፍ ይረዳል።

ድጋፍ የሚያስፈልገው ሰው ካወቅኩ ከ Care Connect Washington የማናግረው ማንን ነው?

እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው በአሁኑ ጊዜ በቤት ውስጥ ራሳቸውን እያገለሉ ወይም ማቆያ ውስጥ ከሆኑ እና እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ፣ የግዛቱን ነፃ የ COVID-19 መረጃ መስመር ያግኙ።

ለስቴት COVID-19 የመረጃ መስመር፡ ወደ 1-800-525-0127 ይደውሉ፣ በመቀጠል # ይጫኑ። የቋንቋ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

 • ሰኞ ከ 6 a.m. እስከ 10 p.m.
 • ከማክሰኞ እስከ እሁድ ከ 6 a.m. እስከ 6 p.m. እንዲሁም የሚከበሩ የመንግስት በዓላት
Care Connect Washington የባህሪ ጤና አገልግሎቶችን ያጠቃልላል?

አዎ። የእርስዎ የእንክብካቤ አስተባባሪ የባሕሪ ጤና አገልግሎቶችን በማኅበረሰብዎ ውስጥ እንዲያገኙ ይረዳዎታል።

የእንክብካቤ ትብብር ድጋፍ አገልግሎቶች ለ Tribal Nations ዓባላት ይገኛሉ?

አዎ። የአለጠ ለማወቅ፣ ወደ COVID19.CareCoordination@doh.wa.gov ኢሜይል ያድርጉ ወይም ወደ 564-999-1565 ድደውሉ።

የትርጉም አገልግሎቶች አሉ?

አዎ። የግዛቱን COVID-19 የመረጃ መስመር በ 1-800-525-0127 ላይ ይደውሉ፣ ከዚያ #ን ሲጫኑ፣ የቋንቋ እርዳታ ይገኛል።

ከእንክብካቤ አስተባባሪ ጋር አንዴ ከተገኛኙ፣ Care Connect Washington የሚያስፈልጎትን መረጃ በሚመርጡት ቋንቋ ያቀርባል።

የመረጃ ምንጮች

የመረጃ ምንጮች እና የጥቆማዎች ድረገጽ፦ የፊት የልብስ መሸፈኛዎች፣ ኳራንቲን፣ ለቤተሰቦች እንክብካቤ መስጠት፣ ለ COVID-19 መጋለጥ፣ ምልክቶች፣ እና ሌሎችም ላይ መረጃ ያግኙ። ለሚመርጡት ቋንቋ መረጃውን ማስተካከል ይችላሉ።